2 ዜና መዋዕል 20 – New Amharic Standard Version NASV

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 20:1-37

ኢዮሣፍጥ ሞዓብንና አሞንን ድል ማድረጉ

1ከዚህ በኋላ ሞዓባውያንና አሞናውያን ከጥቂት ምዑናውያን20፥1 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ነገር ግን ዕብራይስጡ ምድያማውያን ይላል። ጋር ሆነው ኢዮሣፍጥን ለመውጋት መጡ።

2ሰዎችም መጥተው ኢዮሣፍጥን፣ “ግዙፍ ሰራዊት ሊወጋህ ከሙት20፥2 አንድ የዕብራይስጥ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን አራም ይላል። ባሕር ወዲያ ካለው ከኤዶም20፥2 ምንም እንኳ የሙት ባሕር መሆኑን ግልጽ ቢሆንም አንዳንድ ቅጆች ሙት የሚለውን ቃል አይጨምሩም። መጥቶብሃል፤ እነሆም፣ ሐሴሶን ታማር በተባለው በዓይንጋዲ ናቸው” አሉት። 3ኢዮሣፍጥም እጅግ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም ዐወጀ። 4የይሁዳ ሕዝብም የእግዚአብሔርን ርዳታ ይሻ ዘንድ በአንድነት ተሰበሰበ፤ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉም እግዚአብሔርን ለመፈለግ መጡ። 5ኢዮሣፍጥም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ከአዲሱ አደባባይ ፊት ለፊት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ጉባኤ መካከል ቆመ፤ 6እንዲህም አለ፤

“የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በሰማይ የምትኖር አምላክ አይደለህምን? የምድር ሕዝቦችን መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ ነህ፤ ኀይልና ሥልጣን በእጅህ ነው፤ ሊቋቋምህም የሚችል ማንም የለም። 7አምላካችን ሆይ፤ የዚህችን ምድር ነዋሪዎች ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት አሳድደህ ያስወጣህና ለወዳጅህ ለአብርሃም ዘሮች ለዘላለም የሰጠሃቸው አንተ አይደለህምን? 8እነርሱም ተቀመጡባት፤ ለስምህ መቅደስ ሠሩባት፤ እንዲህም አሉ፤ 9‘የፍርድ ሰይፍም ሆነ የቸነፈር ወይም የራብ መከራ ቢደርስብን፣ ስምህ በተጠራበት በዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት፣ በፊትህ ቆመን በጭንቀታችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ትሰማናለህ፤ ታድነናለህም።’

10“እስራኤል ከግብፅ በወጡ ጊዜ፣ ግዛታቸውን እንዳይወርሩባቸው በማድረግህ ከእነርሱ ተመልሰው ሳያጠፏቸው የቀሩት የአሞን፣ የሞዓብና የሴይር ተራራ ሰዎች እነሆ እዚህ አሉ። 11እነሆ፣ አንተ ርስት አድርገህ ከሰጠኸን ምድር እኛን በማፈናቀል ወሮታ ሊመልሱልን መጥተዋል። 12አምላካችን ሆይ፤ አንተ አትፈርድባቸውምን? የመጣብንን ይህን ታላቅ ሰራዊት እንቋቋም ዘንድ ዐቅም የለንምና የምናደርገውን አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወዳንተ ናቸው።”

13የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ከሚስቶቻቸው፣ ከልጆቻቸውና ከሕፃኖቻቸው ጋር በእግዚአብሔር ፊት ቆመው ነበር።

14በዚህ ጊዜ የአሳፍ ዘር በሆነው በሌዋዊው በዘካርያስ ልጅ፣ በየሕዚኤል ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ መጣ። ዘካርያስም የበናያስ ልጅ ሲሆን፣ በናያስም የማታን ልጅ የሆነው የይዒኤል ልጅ ነው።

15እርሱም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ኢዮሣፍጥ፣ እናንተም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ! እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፤ ‘ውጊያው የእግዚአብሔር እንጂ የእናንተ አይደለምና፣ ከዚህ ታላቅ ሰራዊት የተነሣ አትፍሩ፣ አትደንግጡ፣ 16ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ፤ እነርሱ በጺጽ መተላለፊያ ሽቅብ ይወጣሉ፣ እናንተም በይሩኤል ምድረ በዳ ውስጥ በሸለቆው መጨረሻ ላይ ታገኟቸዋላችሁ። 17ይህን ጦርነት የምትዋጉት እናንተ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁንም ማዳን እዩ። አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገውኑ ውጡና ግጠሟቸው፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል።’ ”

18ኢዮሣፍጥ በግንባሩ ወደ መሬት ተደፋ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ወደቁ፤ ሰገዱም። 19ከቀዓትና ከቆሬ ወገኖች ጥቂት ሌዋውያንም ቆመው፣ እጅግ ከፍ ባለ ድምፅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

20በማግስቱም ጧት በማለዳ ተነሥተው ወደ ቴቁሔ ምድረ በዳ ሄዱ። መንገድ እንደ ጀመሩም ኢዮሣፍጥ ቆሞ፣ “ይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ፣ አድምጡኝ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፤ ትጸኑማላችሁ። በነቢያቱም እመኑ፤ ይሳካላችሁማል” አላቸው። 21ከሕዝቡም ጋር ከተመካከረ በኋላ ከሰራዊቱ ፊት ቀድመው በመሄድ፣

እግዚአብሔርን አመስግኑ፣

ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና”

እያሉ ለእግዚአብሔር የሚዘምሩና ስለ ቅድስናውም ክብር የሚያወድሱ ሰዎችን መደበ።

22መዘመርና ማወደስ እንደ ጀመሩም፣ እግዚአብሔር ይሁዳን በወረሩት በአሞን፣ በሞዓብና በሴይር ተራራ ሰዎች ላይ ድብቅ ጦር አመጣባቸው፤ ተሸነፉም። 23የአሞንና የሞዓብ ሰዎችም የሴይርን ተራራ ሰዎች ለማጥፋትና ለመደምሰስ ተነሡባቸው። ከሴይር የመጡትን ሰዎች ካጠፉ በኋላም፣ እርስ በርስ ተጠፋፉ።

24የይሁዳ ሰዎች ምድረ በዳውን ቍልቍል ወደሚያሳየው ቦታ መጥተው ግዙፉን ሰራዊት ሲመለከቱ፣ መሬቱ ሬሳ በሬሳ ሆኖ አዩ፤ አንድም ሰው አላመለጠም። 25ኢዮሣፍጥና ሰዎቹም ምርኳቸውን ለማጋዝ ሄዱ፤ በዚያም መካከል እጅግ ብዙ መሣሪያና ልብስ፣20፥25 አንዳንድ የዕብራይስጥና የቩልጌት ቅጆች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ነገር ግን አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ሬሳ ይላል። ሊሸከሙ ከሚችሉትም በላይ ውድ ዕቃዎችን አገኙ። ምርኮውም ከመብዛቱ የተነሣ ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀ። 26በአራተኛውም ቀን እግዚአብሔርን ባመሰገኑበት በበረከት20፥26 በዕብራይስጡ፣ በራካ ማለት በረከት ማለት ነው። ሸለቆ ተሰበሰቡ፤ ያም ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የበረከት ሸለቆ ተብሎ የተጠራው ከዚህ የተነሣ ነው።

27እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ እንዲደሰቱ ስላደረጋቸው፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ በኢዮሣፍጥ እየተመሩ፣ በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። 28ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ እንደ ገቡም በበገና፣ በመሰንቆና በመለከት ድምፅ ታጅበው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አመሩ።

29እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንዴት እንደ ተዋጋቸው በሰሙ መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርሀት ወደቀባቸው።

30አምላኩ በየአቅጣጫው ዕረፍት ስለ ሰጠው፣ የኢዮሣፍጥ መንግሥት ሰላም አግኝቶ ነበር።

የኢዮሣፍጥ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ

20፥31–21፥1 ተጓ ምብ – 1ነገ 22፥41-50

31ኢዮሣፍጥ በይሁዳ ላይ ነገሠ። መንገሥ በጀመረ ጊዜም ዕድሜው ሠላሳ አምስት ዓመት ሲሆን፣ በኢየሩሳሌም ተቀሞጦ ሃያ አምስት ዓመት ገዛ። እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች። 32እርሱም በአባቱ በአሳ መንገድ ሄደ፤ ከዚያም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔርም ፊት መልካም የሆነውን ነገር አደረገ። 33ያም ሆኖ ግን ማምለኪያ ኰረብታዎች ሙሉ በሙሉ አልተወገዱም፤ ሕዝቡም ገና ልቡን በአባቶቹ አምላክ ላይ አልጣለም ነበር።

34በኢዮሣፍጥ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወኑት ሌሎች ተግባራት የአናኒ ልጅ ኢዩ በዘገበው የእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቧል።

35ከዚህ በኋላ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሥራው እጅግ ክፉ ከሆነው ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝያስ ጋር የስምምነት ውል አደረገ፤ 36የንግድ መርከብ20፥36 ዕብራይስጡ፣ ወደ ተርሴስ ሊሄዱ የሚችሉ መርከቦች ይላል። ለመሥራትም ተስማሙ፤ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር አሠሩ። 37የመሪሳ ሰው የሆነው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር በኢዮሣፍጥ ላይ፣ “ከአካዝያስ ጋር የስምምነት ውል ስለ አደረግህ፣ እግዚአብሔር ሥራህን ያፈርሰዋል” ሲል ትንቢት ተናገረበት፤ መርከቦቹም ተሰበሩ፤ ለንግዱም ሥራ መንቀሳቀስ አልቻሉም።20፥37 ዕብራይስጡ፣ ወደ ተርሴስ መሄድ አልቻሉም ይላል።