2 ዜና መዋዕል 15 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 15:1-19

ንጉሥ አሳ ያደረገው ተሐድሶ

15፥16-19 ተጓ ምብ – 1ነገ 15፥13-16

1የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በአዛርያስ ላይ መጣ። 2እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን፣ ይተዋችኋል። 3እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል። 4በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው። 5በዚያን ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አልነበረም። 6እግዚአብሔር በተለያየ መከራ ያስጨንቃቸው ስለ ነበር፣ አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት፣ አንዱም ከተማ በሌላው ከተማ ይደመሰስ ነበር። 7እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።”

8አሳ ይህን ቃልና የነቢዩን የዖዴድን ልጅ15፥8 የቩልጌትና የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም ቍጥር 1) ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን የዖዴድን ልጅ የሚለውን አይጨምርም። የዓዛርያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ በረታ። ከመላው ይሁዳና ከብንያም ምድር፣ በኤፍሬምም ኰረብታዎች ላይ ከያዛቸው ከተሞች አስጸያፊዎቹን ጣዖታት አስወገደ። ከእግዚአብሔር መቅደስ ሰበሰብ ፊት ለፊት የነበረውንም የእግዚአብሔር መሠዊያ ዐደሰ።

9አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን ባዩ ጊዜ፣ ከእስራኤል ብዙ ሰዎች እርሱን ተጠግተው ነበር፤ እርሱም ይሁዳንና ብንያምን እንዲሁም ከኤፍሬም፣ ከምናሴና ከስምዖን መጥተው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ።

10እነርሱም በአሳ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። 11በዚያን ጊዜ በምርኮ ካመጡት ውስጥ ሰባት መቶ በሬ፣ ሰባት ሺሕ በግና ፍየል ለእግዚአብሔር ሠዉ። 12የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ። 13የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ሁሉ ግን፣ ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል አደረጉ። 14ይህንም በታላቅ ድምፅ፣ በእልልታ፣ በእንቢልታና በመለከት ድምፅ ለእግዚአብሔር ማሉ። 15በፍጹም ልባቸው ስለማሉም የይሁዳ ሕዝብ በመሐላው ደስ ተሰኙ። እግዚአብሔርን ከልብ ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጣቸው።

16እንዲሁም ንጉሥ አሳ አያቱን ማዓካን ለአስጸያፊዋ የአሼራ ጣዖት ዐምድ ስላቆመች ከእቴጌነት ክብሯ ሻራት። አሳም ዐምዱን ቈርጦ በመሰባበር በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው። 17ምንም እንኳ ማምለኪያ ኰረብታዎችን ሙሉ በሙሉ ከእስራኤል ባያስወግድም፣ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፈጽሞ ለእግዚአብሔር የተገዛ ነበር። 18እርሱና አባቱ የቀደሱትን ብሩን፣ ወርቁንና ልዩ ልዩ ዕቃ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገባ።

19እስከ ሠላሳ አምስተኛው የአሳ ዘመነ መንግሥት ድረስ ምንም ዐይነት ጦርነት አልነበረም።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

歷代志下 15:1-19

亞撒的改革

1上帝的靈降在俄德的兒子亞撒利雅身上, 2他便出來迎接亞撒,對他說:「亞撒啊,所有的猶大人和便雅憫人啊,請聽我說!你們若順從耶和華,祂必與你們同在。你們若尋求祂,祂必讓你們尋見。你們若背棄祂,祂必離棄你們。 3以色列人已經許久沒有真神,沒有祭司教導,也沒有律法。 4然而,他們在患難時歸向以色列的上帝耶和華,尋求祂,祂就讓他們尋見。 5那時,人們出入不得平安,因為各地都有動亂。 6邦國與邦國、城邑與城邑互相攻擊破壞,因為上帝用各樣的災難擾亂他們。 7但你們要剛強,不要雙手發軟,因為你們必因所行的而得獎賞。」

8亞撒聽了俄德的兒子亞撒利雅先知的預言,就鼓起勇氣在猶大便雅憫全境以及他在以法蓮山區奪取的各城邑剷除可憎的神像,並在耶和華殿的走廊前重修耶和華的祭壇。

9當時,有許多以法蓮人、瑪拿西人和西緬人看見亞撒的上帝耶和華與他同在,就從以色列來投奔他,寄居在猶大亞撒把他們和所有的猶大人與便雅憫人都招聚在一起。 10亞撒執政第十五年三月,他們聚集在耶路撒冷11當天,他們從擄物中取出七百頭牛和七千隻羊獻給耶和華。 12他們又與他們祖先的上帝耶和華立約,要全心全意地尋求祂。 13凡不尋求以色列的上帝耶和華的,無論男女老幼,一律處死。 14他們高聲向耶和華起誓,並吹響號角。 15猶大人都為所起的誓而歡喜快樂,因他們誠心起誓、誠意尋求耶和華,耶和華就讓他們尋見,並賜他們四境平安。

16亞撒王廢除了他祖母瑪迦的太后之位,因為她造了可憎的亞舍拉神像。亞撒將她的神像砍倒、打碎,燒毀在汲淪溪旁。 17儘管他還沒有把邱壇從以色列除去,但他一生對耶和華忠心。 18他將他父親和自己奉獻給上帝的金銀及器皿都帶到上帝的殿裡。

19從那時直到亞撒執政第三十五年,國中都沒有戰爭。