2 ነገሥት 22 – NASV & PCB

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 22:1-20

የሕጉ መጽሐፍ ተገኘ

22፥1-20 ተጓ ምብ – 2ዜና 34፥1-28-28

1ኢዮስያስ ሲነግሥ ዕድሜው ገና ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም የባሱሮት አገር ሰው የአዳያ ልጅ ይዲዳ ነበረች። 2ኢዮስያስም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም፤ አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ።

3በዘመነ መንግሥቱ በዐሥራ ስምንተኛውም ዓመት ኢዮስያስ የሜሶላምን የልጅ ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ጸሓፊውን ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላከው፤ እንዲህም አለው፤ 4“ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ ውጣ፤ የበር ጠባቂዎች ከሕዝቡ ሰብስበው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የገባው ገንዘብ ምን ያህል እንደ ሆነ ራሱ እንዲቈጥረው አድርግ፤ 5ይህም የቤተ መቅደሱን ሥራ እንዲቈጣጠሩ ለተሾሙት ሰዎች ይሰጥ፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለሚያድሱት ይክፈሏቸው፤ 6የሚከፍሉትም ለዐናጺዎች፣ ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ነው። እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሥራ የሚሆኑ ሳንቃዎችና የተጠረቡ ድንጋዮች ይግዙበት። 7ሰዎቹ ታማኞች ስለ ሆኑም የተሰጣቸውን ገንዘብ መቈጣጠር አያስፈልግም።”

8ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ ጸሓፊውን ሳፋንን፣ “የሕጉን መጽሐፍ እኮ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አገኘሁት” ብሎ ሰጠው፤ እርሱም ተቀብሎ አነበበው። 9ከዚያም ጸሓፊው ሳፋን ሄዶ ለንጉሡ፣ “ሹማምትህ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የነበረውን ገንዘብ አውጥተዋል፤ ቤተ መቅደሱን እየተቈጣጠሩ ለሚያሠሩትም አስረክበዋል” አለው። 10ከዚያም ጸሓፊው ሳፋን ለንጉሡ፣ “ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ መጽሐፍ ሰጥቶኛል” ብሎ ነገረው። ሳፋንም ለንጉሡ ከመጽሐፉ አነበበለት።

11ንጉሡም የሕጉን መጽሐፍ ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ። 12ከዚያም ካህኑን ኬልቅያስን፣ የሳፋን ልጅ አኪቃምን፣ የሚክያስን ልጅ ዓክቦርን፣ ጸሓፊውን ሳፋንንና የንጉሡን የቅርብ አገልጋይ ዓሳያን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ 13“ሂዱና ስለ እኔ፣ ስለ ሕዝቡና ስለ ይሁዳም ሁሉ በተገኘው በዚህ መጽሐፍ የተጻፈው ምን እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ምክንያቱም አባቶቻችን ለዚህ መጽሐፍ ቃል ባለመታዘዛቸው፣ እኛን በተመለከተም በዚሁ ላይ የተጻፈውን ሁሉ ባለመፈጸማቸው፣ በእኛ ላይ የሚነድደው የእግዚአብሔር ቍጣ ታላቅ ነውና።”

14ካህኑ ኬልቅያስ፣ አኪቃም፣ ዓክቦርና፣ ሳፋን፣ ዓሳያም የሐርሐስ የልጅ ልጅ፣ የቲቁዋ ልጅ የአልባሳት ጠባቂውን የሴሌምን ሚስት ነቢዪቱን ሕልዳናን ለመጠየቅ ሄዱ። እርሷም የምትኖረው ኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው ሰፈር ነበር።

15ነቢዪቱም፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ 16እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ በዚህ ቦታና በሕዝቡ ላይ አመጣለሁ። 17እኔን ስለተውኝና ለሌሎች አማልክት ዕጣን ስላጠኑ፣ እጆቻቸው በሠሯቸውም አማልክት ሁሉ22፥17 ወይም፣ በሠሩት ሥራ ሁሉ ስላስቈጡኝ፣ ቍጣዬ በዚህ ቦታ ላይ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።’ 18እግዚአብሔርን እንድትጠይቁ ወደዚህ ቦታ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ ይህን ንገሩት፤ ስለ ሰማኸው ነገር የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ 19‘ለርግማንና ለጥፋት የተዳረጉ ስለ መሆናቸው በዚህ ቦታና በሕዝቡ ላይ የተናገርኩትን ስትሰማ ልብህ ስለ ተነካና ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ስላዋረድህ፣ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ ስላለቀስህ እግዚአብሔር ሰምቼሃለሁ ብሏል። 20ስለዚህ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ ወደ መቃብር በሰላም ትወርዳለህ፤ በዚህ ቦታም የማመጣውን መከራ ሁሉ ዐይኖችህ አያዩም።’ ”

ሰዎቹም መልሱን ለንጉሡ ይዘውለት ሄዱ።

Persian Contemporary Bible

دوم پادشاهان 22:1-20

يوشيا، پادشاه يهودا

(دوم تواريخ 34‏:1‏-2)

1يوشيا هشت ساله بود كه پادشاه يهودا شد و سی و يک سال در اورشليم سلطنت نمود. (مادرش يديده، دختر عدايه، از اهالی بصقت بود.) 2يوشيا مانند جدش داوود مطابق ميل خداوند عمل می‌كرد و از دستورات خدا اطاعت كامل می‌نمود.

پيدا شدن كتاب تورات

(دوم تواريخ 34‏:8‏-28)

3‏-4يوشيای پادشاه در هجدهمين سال سلطنت خود، شافان (پسر اصليا و نوهٔ مشلام) کاتب را به خانهٔ خداوند فرستاد تا اين پيغام را به حلقيا، كاهن اعظم بدهد: «نقره‌ای را كه مردم به خانهٔ خداوند می‌آورند و به كاهنان محافظ در ورودی می‌دهند، جمع‌آوری كن 5‏-6و آن را به ناظران ساختمانی خانه خداوند تحويل بده تا با آن، نجارها و بناها و معمارها را به کار بگيرند و سنگها و چوبهای تراشيده را خريداری نمايند و خرابيهای خانهٔ خدا را تعمير كنند.»

7(از ناظران ساختمانی خانهٔ خداوند صورتحساب نمی‌خواستند، چون مردانی امين و درستكار بودند.)

8يک روز حلقيا، كاهن اعظم نزد شافان کاتب رفت و گفت: «در خانهٔ خداوند كتاب تورات را پيدا كرده‌ام.» سپس كتاب را به شافان نشان داد تا آن را بخواند.

9‏-10وقتی شافان گزارش كار ساختمان خانهٔ خداوند را به پادشاه می‌داد در مورد كتابی نيز كه حلقيا، كاهن اعظم در خانهٔ خداوند پيدا كرده بود با او صحبت كرد. سپس شافان آن را برای پادشاه خواند.

11وقتی پادشاه كلمات تورات را شنيد، از شدت ناراحتی لباس خود را پاره كرد 12‏-13و به حلقيا كاهن اعظم، شافان کاتب، عسايا ملتزم پادشاه، اخيقام (پسر شافان) و عكبور (پسر ميكايا) گفت: «از خداوند بپرسيد كه من و قومم چه بايد بكنيم. بدون شک خداوند از ما خشمگين است، چون اجداد ما مطابق دستورات او كه در اين كتاب نوشته شده است رفتار نكرده‌اند.»

14پس حلقيا، اخيقام، عكبور، شافان و عسايا نزد زنی به نام حُلده رفتند كه نبيه بود و در محلهٔ دوم اورشليم زندگی می‌كرد. (شوهر او شلوم، پسر تقوه و نوهٔ حرحس، خياط دربار بود.) وقتی جريان امر را برای حلده تعريف كردند، 15حلده به ايشان گفت كه نزد پادشاه بازگردند و اين پيغام را از جانب خداوند، خدای اسرائيل به او بدهند. 16«همانطور كه در كتاب تورات فرموده‌ام و تو آن را خواندی، بر اين شهر و مردمانش بلا خواهم فرستاد، 17زيرا مردم يهودا مرا ترک گفته، بت‌پرست شده‌اند و با كارهايشان خشم مرا برانگيخته‌اند. پس آتش خشم من كه بر اورشليم افروخته شده، خاموش نخواهد شد.

18‏-20«اما من دعای تو را اجابت خواهم نمود و اين بلا را پس از مرگ تو بر اين سرزمين خواهم فرستاد. تو اين بلا را نخواهی ديد و در آرامش خواهی مرد، زيرا هنگامی كه كتاب تورات را خواندی و از اخطار من در مورد مجازات اين سرزمين و ساكنانش آگاه شدی، متأثر شده، لباس خود را پاره نمودی و در حضور من گريه كرده، فروتن شدی.»

فرستادگان پادشاه اين پيغام را به او رساندند.