2 ነገሥት 20 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 20:1-21

የሕዝቅያስ መታመም

20፥1-11 ተጓ ምብ – 2ዜና 32፥24-26ኢሳ 38፥1-8

1በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር። የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ ሄዶ፣ “እግዚአብሔር፣ ‘ትሞታለህ፤ ከእንግዲህ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል’ ብሎሃል” አለው።

2ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ 3እግዚአብሔር ሆይ፤ በታማኝነትና በፍጹም ልብ በፊትህ እንደ ሄድሁ፣ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ዐስብ፤” ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።

4ኢሳይያስ የመካከለኛውን አደባባይ ዐልፎ ከመሄዱ በፊት የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤ 5“ተመለስና የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፤ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፤ እፈውስሃለሁ። ከዛሬ ሦስት ቀን በኋላ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤ 6በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ ስለ ራሴና ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል ይህችን ከተማ እከላከልላታለሁ።’ ”

7ከዚያም ኢሳይያስ፣ “ትኵስ የበለስ ጥፍጥፍ አዘጋጁ” አላቸው፤ እነርሱም አዘጋጅተው ዕባጩ ላይ አደረጉለት፤ ተፈወሰም።

8ሕዝቅያስም፣ “እግዚአብሔር እኔን ስለ መፈወሱ፣ ከሦስት ቀን በኋላም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ስለ መውጣቴ ምልክቱ ምንድን ነው?” ሲል ኢሳይያስን ጠየቀው።

9ኢሳይያስም፣ “እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም ምልክቱ ይህ ነው፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይቅደምን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ?” ሲል ጠየቀው።

10ሕዝቅያስም መልሶ፣ “ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት መሄዱ ቀላል ነገር ነው፤ ይልቁን ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ” አለ።

11ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔርም አካዝ በሠራው ደረጃ ላይ የወረደውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው እንዲመለስ አደረገ።

ከባቢሎን የመጡ መልእክተኞች

20፥12-19 ተጓ ምብ – ኢሳ 39፥1-8

20፥20-21 ተጓ ምብ – 2ዜና 32፥32-33

12በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመም ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ገጸ በረከት ለሕዝቅያስ ላከለት። 13ሕዝቅያስም መልክተኞቹን ተቀብሎ በዕቃ ቤቱ ያለውን ሁሉ ብሩን፣ ወርቁን ቅመማ ቅመሙንና ከፍ ያለ ዋጋ ያለውን ዘይት የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤቱንና በቀረውም ግምጃ ቤት ያለውን በሙሉ አሳያቸው። በቤተ መንግሥቱም ሆነ በመላው ግዛቱ ሕዝቅያስ ሳያሳያቸው የቀረ ምንም ነገር አልነበረም።

14ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ሕዝቅያስ ሄዶ፣ “እነዚያ ሰዎች ምን አሉህ? የመጡትስ ከወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው።

ሕዝቅያስም መልሶ፣ “የመጡት ከሩቅ አገር ከባቢሎን ነው” አለው።

15ነቢዩም፣ “በቤተ መንግሥትህ ምን ምን አዩ?” ሲል ጠየቀው።

ሕዝቅያስም፣ “በቤተ መንግሥቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በግምጃ ቤቶቼ ሳላሳያቸው የቀረ ምንም ነገር የለም” አለ።

16ከዚያም ኢሳይያስ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ 17በቤተ መንግሥትህ ያለው ሁሉ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት በሙሉ ወደ ባቢሎን የሚወሰድበት ጊዜ በርግጥ ይመጣል፤ አንዳች የሚቀር ነገር የለም ይላል እግዚአብሔር18የሥጋህ ቍራጭ የዐጥንትህ ፍላጭ ከሚሆኑት፣ ከምትወልዳቸው ልጆችህ አንዳንዶቹ በምርኮ ይወሰዳሉ፤ በባቢሎንም ቤተ መንግሥት ጃንደረቦች ይሆናሉ።” 19ሕዝቅያስም፣ “የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው” ሲል መለሰ፤ “እኔ እስካለሁ ድረስ ሰላምና ጸጥታ ከተገኘ የሆነው ይሁን” ብሎ አስቧልና። 20በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ሁሉ ኵሬውንና ውሃውን ወደ ከተማዪቱ ያመጣበትን የመሬት ለመሬት ቦይ እንዴት አድርጎ እንደ ሠራው በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 21ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁ ምናሴም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

列王紀下 20:1-21

希西迦的病危與康復

1那些天,希西迦病危,亞摩斯的兒子以賽亞先知前來對他說:「耶和華說,『你要交待後事,因為你要死了,你的病不能康復。』」 2希西迦把臉轉向牆,向耶和華禱告,說: 3「耶和華啊,求你顧念我怎樣全心、忠誠地事奉你,做你視為善的事。」希西迦痛哭起來。 4當時,以賽亞還沒有走出中院,耶和華對他說: 5「回去告訴我子民的首領希西迦,『你祖先大衛的上帝耶和華說,我已聽見你的禱告,看見了你的眼淚。我要醫治你,三天後你就可以上耶和華的殿。 6我要使你的壽命增加十五年,我要從亞述王手中拯救你和這城。為我自己和我僕人大衛的緣故,我要保護這城。』」

7以賽亞說:「拿一塊無花果餅貼在王的瘡上,他就會痊癒。」

8希西迦以賽亞:「有什麼兆頭證明耶和華要醫治我,三天後我可以上耶和華的殿呢?」 9以賽亞說:「耶和華要給你一個兆頭,證明祂言出必行。你要日影前進十度還是後退十度呢?」 10希西迦說:「日影前進十度容易,讓日影後退十度吧。」 11以賽亞先知向耶和華祈求,耶和華就使亞哈斯日晷上的日影後退了十度。

巴比倫的使者來訪

12那時,巴拉但的兒子巴比倫米羅達·巴拉但聽說希西迦病了,便派人送去書信和禮物。 13希西迦接見使者,讓他們觀看國庫裡的金銀、香料、珍貴膏油、所有兵器和一切寶物。希西迦把宮中及國內的一切都給他們看。

14以賽亞先知來見希西迦王,問他:「這些人說了些什麼?他們從哪裡來?」希西迦答道:「他們來自遙遠的巴比倫。」 15以賽亞問:「他們在你宮裡看到了什麼?」希西迦答道:「他們看到了我宮中的一切。我把國庫裡的一切都給他們看了。」

16以賽亞希西迦說:「你聽著,耶和華說, 17『終有一天,你宮中的一切和你祖先積攢到現在的一切,必一件不留地被擄到巴比倫。這是耶和華說的。 18你的子孫當中必有人被擄去,在巴比倫王的宮中做太監。』」 19希西迦以賽亞說:「耶和華藉你說的話很好。」因為他想:「至少我有生之年將平安穩妥。」

20希西迦其他的事蹟和成就,包括怎樣建造水池和挖溝引水入城,都記在猶大的列王史上。 21希西迦與祖先同眠後,他兒子瑪拿西繼位。