2 ነገሥት 19 – NASV & HTB

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 19:1-37

ኢየሩሳሌም ከጠላት እጅ እንደምትድን አስቀድሞ መነገሩ

19፥1-13 ተጓ ምብ – ኢሳ 37፥1-13

1ንጉሥ ሕዝቅያስ ይህን ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገባ። 2ከዚያም የቤተ መንግሥቱን አዛዥ ኤልያቄምን፣ ጸሓፊውን ሳምናስንና ዋና ዋናዎቹን ካህናት ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲሄዱ ሁሉንም ላካቸው። 3እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ የሚለው ይህ ነው፤ ‘እንግዲህ ይህች ዕለት የመከራ፣ የዘለፋና የውርደት ቀን ናት፤ ይህችም ቀን ልጆች ሊወለዱ ምጥ እንዳፋፋመበት፣ ነገር ግን ለመገላገል ዐቅም እንደታጣበት ሰዓት ናት። 4ሕያው እግዚአብሔርን ያንቋሽሽ ዘንድ በጌታው በአሦር ንጉሥ የተላከውን የጦር አዛዡን ቃል ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ሰምቶ ይሆናልና፣ ስለ ሰማውም ቃል እግዚአብሔር እንዲገሥጸው በሕይወት ስለ ተረፉት ወገኖቻችን እባክህ ጸልይ።’ ”

5የንጉሥ ሕዝቅያስ ሹማምት ወደ ኢሳይያስ በመጡ ጊዜ፣ 6ኢሳይያስ እንዲህ አላቸው፤ “ለጌታችሁ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ ‘እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች በእኔ ላይ የወረወሯቸውን የስድብ ቃላት በመስማትህ አትፍራ። 7እነሆ፣ አንድ ዐይነት መንፈስ አሳድርበታለሁ፤ የሆነ ወሬም ሲሰማ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ እዚያም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ።” ’ ”

8የጦር አዛዡም የአሦር ንጉሥ ለኪሶን ትቶ መሄዱን ሲሰማ ተመለሰ፤ ንጉሡንም ልብናን ሲወጋ አገኘው።

9በዚህም ጊዜ የግብፅ ንጉሥ ኢትዮጵያዊው ቲርሐቅ ሊወጋው በመገሥገሥ ላይ መሆኑን ሰናክሬም ሰማ፤ ስለዚህ ወደ ሕዝቅያስ እንደ ገና እንዲህ ሲል መልእክተኞች ላከ፤ 10“ሂዱና ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስ እንዲህ በሉት፤ ‘የምትመካበት አምላክ፣ “ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” በማለት እንዳያታልልህ። 11መቼም የአሦር ነገሥታት በአገሮች ሁሉ ላይ ምን እንዳደረጉ ሰምተሃል፤ ፈጽሞ አጥፍተዋቸዋል፤ ታዲያ አንተስ ከዚህ የምታመልጥ ይመስልሃልን? 12የቀድሞ አባቶቼ ያጠፏቸውን ሕዝቦች ማለትም ጎዛንን፣ ካራንን፣ ራፊስን እንዲሁም በተላሳር የነበሩትን የዔድንን ሰዎች አማልክታቸው አድነዋቸዋልን? 13ለመሆኑ የሐማትና የአርፋድ ነገሥታት የት አሉ? የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥስ የት አለ? ደግሞስ የሄና ወይም የዒዋ ነገሥታት የት አሉ?’ ”

የሕዝቅያስ ጸሎት

19፥14-19 ተጓ ምብ – ኢሳ 37፥14-20

14ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ከመልእክተኞቹ ተቀብሎ አነበበው፤ ከዚያም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወጥቶ ደብዳቤውን በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው። 15ከዚያም ሕዝቅያስ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ “በኪሩቤል ላይ በዙፋንህ የተቀመጥህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በምድር ነገሥታት ሁሉ ላይ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህም አንተ ነህ። 16እግዚአብሔር ሆይ፤ አሁንም ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይንህንም ክፈትና እይ፤ ሰናክሬም ሕያው እግዚአብሔርን ይሰድብ ዘንድ የላከውንም ቃል አድምጥ።

17እግዚአብሔር ሆይ፤ የአሦር ነገሥታት እነዚህን አሕዛብንና ምድራቸውን በርግጥ አጥፍተዋል። 18አማልክታቸውን በእሳት ውስጥ ጥለው አቃጥለዋቸዋል፤ በሰው እጅ የተሠሩ ዕንጨትና ድንጋይ ብቻ እንጂ አማልክት አልነበሩምና። 19አሁንም እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ የምድር መንግሥታት ሁሉ እግዚአብሔር አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን እንዲያውቁ፣ ከእጁ አድነን።”

ኢሳይያስ ስለ ሰናክሬም መውደቅ ትንቢት ተናገረ

19፥20-37 ተጓ ምብ – ኢሳ 37፥21-38

19፥35-37 ተጓ ምብ – 2ዜና 32፥20-21

20ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በአሦር ንጉሥ በሰናክሬም ላይ ወደ እኔ ያቀረብኸውን ልመና ሰምቻለሁ’ 21እንግዲህ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

“ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ፣

ትንቅሃለች፤ ታቃልልሃለችም፤

የኢየሩሳሌም ልጅ፣

አንተ በላይዋ ስትበርር ራሷን ትነቀንቅብሃለች።

22ለመሆኑ የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው?

ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው?

ዐይንህንስ በኵራት ያነሣኸው በማን ላይ ነው?

በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እንዴ?

23በመልእክተኞችህ አማካይነት፣

በአምላክ ላይ የስድብ መዓት አውርደሃል፤

እንዲህም ብለሃል፤

“በብዙ ሠረገሎቼ፣

የተራሮቹን ከፍታ፣

የሊባኖስንም የመጨረሻ ጫፍ ወጥቻለሁ፤

ረጃጅም ዝግባዎቹን፣

ምርጥ የሆኑ ጥዶቹንም ቈርጫለሁ፤

ወደ ሩቅ ዳርቻዎቹ፣

ወደ ውብ ደኖቹም ደርሻለሁ።

24በሌሎች አገሮችም የውሃ ጕድጓዶች ቈፍሬአለሁ፤

በዚያም ውሃ ጠጥቻለሁ፤

በእግሬ ጫማዎችም፣

የግብፅን ምንጮች ሁሉ ረግጬ አድርቄአለሁ።”

25“ ‘ከብዙ ጊዜ በፊት፣

ይህን እኔ እንዳደረግሁት አልሰማህም ነበርን?

ዕቅዱን ገና ድሮ አውጥቼ፣

አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤

ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣

አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።

26የሚኖሩባቸውም ሰዎች ኀይላቸው ተሟጥጦ ዐልቋል፤

ደንግጠውም የኀፍረት ማቅ ለብሰዋል፤

ሜዳ ላይ እንደ በቀለ ተክል፣

ገና እንዳልጠነከረ የቡቃያ ሥር፣

በቤት ጣራ ላይ በቅሎ፣

ገና ሳያድግ እንደ ጠወለገ ሣርም ሆነዋል።

27“ ‘የት እንደምትቀመጥ፣

መቼ መጥተህ መቼ እንደምትሄድ፣

በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቍጣ ዐውቃለሁ።

28በእኔ ላይ በመቈጣትህ፣

ንቀትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣

ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፤

ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤

በመጣህበትም መንገድ

እንድትመለስ አደርጋለሁ።’

29“ሕዝቅያስ ሆይ፤ ምልክቱ ይህ ነው፤

“በዚህ ዓመት በገዛ እጁ የበቀለውን፣

በሚመጣው ዓመት ደግሞ የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤

በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤

ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

30አሁንም ከዳዊት ቤት የተረፉት፣

ሥራቸውን ወደ ታች ይሰድዳሉ፤ ወደ ላይም ፍሬ ያፈራሉ።

31ከኢየሩሳሌም በሕይወት የተረፉት፣

ከጽዮን ተራራም ከሞት ያመለጡት ይወጣሉና።

የእግዚአብሔር ቅናት ይህን ታደርጋለች።

32“እንግዲህ እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፤

“ ‘ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባም፤

አንዲትም ፍላጻ አይወረውርባትም፤

ጋሻ አንግቦ ወደ እርሷ አይቀርብም፤

በዐፈርም ቍልል አይከብባትም።

33በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤

ተመልሶ ይሄዳታል እንጂ ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባም’

ይላል እግዚአብሔር

34‘ስለ ራሴና ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ስል፣

ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ።’ ”

35በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጥቶ ከአሦራውያን ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺሕ ሰው ገደለ። በማግስቱም ሰዎቹ ሲነቁ፣ ቦታው ሬሳ በሬሳ ሆኖ ተገኘ። 36የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከዚያ ተነሥቶ ሄደ፤ ወደ ነነዌም ተመልሶ በዚያ ተቀመጠ።

37አንድ ቀንም ናሳራክ በተባለው አምላኩ ቤተ ጣዖት ገብቶ በመስገድ ላይ ሳለ፣ አድራሜሌክና ሳራሳር የተባሉ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት፤ ከዚያም አምልጠው ወደ አራራት ሸሹ። ልጁ አስራዶንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

Het Boek

2 Koningen 19:1-37

Jesajaʼs boodschap aan Hizkia

1Na hun verslag te hebben aangehoord, scheurde koning Hizkia zijn kleren, trok rouwkleding aan en ging naar de tempel om te bidden. 2Daarna beval hij Eljakim, Sebna en enkele van de oudere priesters ook rouwkleding aan te trekken en met de volgende boodschap naar de profeet Jesaja, de zoon van Amoz, te gaan: 3‘Koning Hizkia zegt: “Dit is een dag van benauwdheid, belediging en vernedering. Het is net als wanneer een kind klaar is om te worden geboren, maar de moeder geen kracht heeft om het ter wereld te brengen. 4Toch heeft de Here, uw God, misschien gehoord hoe de opperbevelhebber de levende God beledigde en zal Hij hem daarvoor straffen. Bid voor ons die nog zijn overgebleven.” ’

5-6 De dienaren van koning Hizkia brachten deze boodschap aan Jesaja over. Jesaja antwoordde: ‘De Here zegt: “Maak u geen zorgen over de woorden waarmee deze Assyriërs Mij hebben beledigd. 7Ik zorg ervoor dat een geest de koning van Assyrië influistert dat er slecht nieuws van thuis is. Hij zal dan besluiten terug te keren. Ik zal ervoor zorgen dat hij thuis een gewelddadige dood sterft.” ’

8De opperbevelhebber ging terug naar Libna, waar de koning vanuit Lachis naartoe was gegaan om te vechten. 9Kort daarna kreeg de koning het bericht dat koning Tirhaka van Ethiopië onderweg was met de bedoeling hem aan te vallen. Voordat hij vertrok om die aanval af te slaan, stuurde hij koning Hizkia de volgende boodschap: 10‘Laat u niet misleiden door uw God, op wie u vertrouwt. Geloof Hem maar niet als Hij zegt dat ik Jeruzalem niet zal innemen. 11U weet heel goed wat de koningen van Assyrië altijd hebben gedaan, waar zij ook kwamen, zij verwoestten alles en iedereen. Waarom zou u een uitzondering op die regel zijn? 12Hebben de goden van de andere volken hen gered, volken als Gozan, Haran, Rezef en Eden in Telassar? De vorige koningen van Assyrië hebben hen allemaal verslagen. 13En wat is gebeurd met de koning van Hamath en de koning van Arpad? En met de koningen van Sefarvaïm, Hena en Ivva?’

14Hizkia nam de brief van de boden aan, las hem, ging naar de tempel en legde hem neer voor de Here. 15Daarna bad hij: ‘Och Here, God van Israël, zittend op uw troon hoog boven de engelen, U alleen bent de God van alle koninkrijken op aarde. U hebt de hemel en de aarde geschapen. 16Here, luister naar mij. Open uw ogen, Here, en zie naar ons om. Luister naar de manier waarop Sanherib de levende God beledigt. 17Here, het is waar dat de koningen van Assyrië al die landen hebben veroverd 18en hun afgodsbeelden hebben verbrand. Maar dat waren ook helemaal geen goden, zij werden kapotgemaakt omdat het slechts voorwerpen waren die mensen hadden gemaakt van steen en hout. 19Och Here, onze God, wij vragen U ons uit hun macht te bevrijden. Dan zullen alle koninkrijken op aarde merken dat alleen U God bent.’

20Toen stuurde Jesaja, de zoon van Amos, de volgende boodschap aan Hizkia: ‘De Here, de God van Israël zegt: “Ik heb uw gebed om hulp tegen koning Sanherib van Assyrië gehoord. 21Dit is mijn antwoord aan koning Sanherib: de maagdelijke dochter van Sion is niet bang voor u. De dochter van Jeruzalem veracht en bespot u. 22Wie hebt u beledigd en belasterd? En tegenover wie hebt u zich zo arrogant gedragen? Het is de Heilige van Israël! 23U hebt Mij beledigd en bij monde van uw boodschappers gezegd: mijn strijdwagens hebben de hoogste bergen veroverd, zelfs de toppen van de Libanon. Ik heb de hoogste ceders en mooiste cipressen omgehakt en ben tot in de verste uithoeken van het woud en het open veld doorgedrongen. 24Ik heb mij opgefrist bij zelfgeslagen putten en heb zo alle rivieren van Egypte drooggelegd!

25Waarom hebt u zich niet al lang geleden gerealiseerd dat Ik u deze dingen laat doen? Ik alleen besloot dat u al die versterkte steden mocht veroveren. 26Daarom hadden de volken die u veroverde, geen kracht zich tegen u te verzetten. Zij waren als groene grassprieten in het veld en op de daken die verschroeien in de felle zon, als koren dat verdort nog voor het halfrijp is. 27Ik weet alles van u. Ik ken al uw plannen en Ik weet precies wat u het volgende moment gaat doen, Ik weet ook welke slechte dingen u over Mij hebt gezegd. 28Omdat u zo overmoedig tegen Mij bent opgetreden, zal Ik een haak door uw neus slaan en een bit in uw mond leggen. Daarmee zal Ik u laten wenden en terugsturen op de weg die u bent gekomen.” ’

29En aan Hizkia liet God Jesaja het volgende zeggen: ‘Dit is het bewijs dat Ik zal doen wat Ik heb gezegd: mijn volk zal dit jaar eten van wat in het wild groeit en ook het jaar daarop. En in het derde jaar zult u weer zaaien, oogsten, wijngaarden planten en de vruchten daarvan eten. 30O mijn volk Juda, degenen van u die de verschrikkingen van het beleg hebben overleefd, zullen weer uitgroeien tot een groot volk, uw wortels zullen diep in de grond dringen en veel vrucht dragen. 31Een overblijfsel van mijn volk zal in Jeruzalem weer op krachten komen. De Here, die alle macht heeft en trouw is, zal dat zo laten gebeuren. 32Mijn bevel aangaande de koning van Assyrië luidt dat hij deze stad niet zal binnenkomen. Hij zal niet voor de stad staan met een schild, geen wal tegen de stadsmuur opwerpen en zelfs geen pijl de stad inschieten. 33Hij zal terugkeren langs dezelfde weg waarlangs hij kwam, 34want Ik zal deze stad verdedigen en bevrijden omwille van Mijzelf en omwille van mijn dienaar David.’

35Diezelfde nacht doodde de Engel van de Here honderdvijfentachtigduizend man van het Assyrische leger en de volgende morgen lag de hele omgeving vol met lijken. 36Koning Sanherib keerde daarop terug naar Ninevé en hij kwam nooit meer terug. 37Terwijl hij zich op een keer in aanbidding neerboog in de tempel van zijn god Nisroch, werd hij door zijn zonen Adrammelech en Sarezer gedood. Zij vluchtten naar het oostelijk deel van het land Ararat en zijn zoon Esarhaddon volgde hem op.