2 ነገሥት 16 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 16:1-20

የይሁዳ ንጉሥ አካዝ

16፥1-20 ተጓ ምብ – 2ዜና 28፥1-27

1የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት፣ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ ነገሠ። 2አካዝ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት ያደረገውን መልካም ነገር በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት አላደረገም። 3እርሱም የእስራኤልን ነገሥታት መንገድ ተከተለ፤ ይልቁንም እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ያሳደዳቸውን የአሕዛብን ርኩሰት ተከትሎ፣ ልጁን በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።16፥3 ወይም፣ ልጁን ገደለ 4እንዲሁም ኰረብታ ላይ ባሉ ማምለኪያ ስፍራዎች፣ በኰረብታ ዐናቶችና ቅጠሉ በተንሰራፋው ዛፍ ሥር ሁሉ ሠዋ፤ ዕጣንም አጤሰ።

5የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ለመውጋትና አካዝን ለመክበብ ወጡ፤ ይሁን እንጂ ሊያሸንፉት አልቻሉም። 6በዚያን ጊዜም የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የይሁዳን ሰዎች አሳድዶ፣ ኤላትን ወደ ሶርያ ግዛት መለሰ፤ ከዚያም ኤዶማውያን ወደ ኤላት መጥተው እስከ ዛሬ በዚያ ይኖራሉ።

7ከዚህ የተነሣም አካዝ፣ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር፣ “እኔ አገልጋይህም ልጅህም ነኝ፤ ስለዚህ መጥተህ ከሚወጉኝ ከሶርያ ንጉሥና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ” ሲል መልእክተኞች ላከበት። 8አካዝም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች የሚገኘውን ብርና ወርቅ አውጥቶ ለአሦር ንጉሥ ገጸ በረከት ላከለት። 9የአሦር ንጉሥም፣ የአካዝን ልመና በመቀበል፤ ደማስቆን አጥቅቶ ያዛት፤ ሕዝቧን ማርኮ ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለው።

10ከዚያም ንጉሥ አካዝ የአሦርን ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶርን ለመገናኘት ወደ ደማስቆ ሄደ። በደማስቆም ያለውን መሠዊያ አይቶ፣ ንድፉን ከዝርዝር ጥናቱ ጋር ለካህኑ ለኦርያ ላከለት። 11ካህኑ ኦርያም ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ በላከለት ዝርዝር ጥናት መሠረት መሠዊያ ሠራ፤ ንጉሡ አካዝ ከመመለሱም በፊት አጠናቀቀው። 12ንጉሡ ከደማስቆ ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ መሠዊያውን አየ፤ ቀርቦም በመሠዊያው ላይ ወጣ፤ 13ከዚያም የሚቃጠል መሥዋዕቱንና የእህል ቍርባኑን በመሠዊያው ላይ አቀረበ፤ የመጠጥ ቍርባኑን አፈሰሰ፤ የኅብረት መሥዋዕቱንም16፥13 በትውፊት፣ የሰላም መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ላይ ረጨ። 14በአዲሱ መሠዊያና በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መካከል፣ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ የነበረውን የናስ መሠዊያ፣ ከቦታው አስነሥቶ ከአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው።

15ከዚያም ንጉሥ አካዝ፣ ካህኑን ኦርያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “በዚህ በትልቁ አዲስ መሠዊያ ላይ የጧቱን የሚቃጠል መሥዋዕትና የማታውን የእህል ቍርባን፣ የንጉሡን የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እንዲሁም የመላውን የአገሪቱን ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህልና የመጠጥ ቍርባናቸውን አቅርብ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ደምና የሌላውን መሥዋዕት ደም ሁሉ በመሠዊያው ላይ እርጨው፤ የናሱ መሠዊያ ግን እኔ መመሪያ ለመጠየቅ የምጠቀምበት ይሆናል።” 16ካህኑ ኦርያም ንጉሡ አካዝ እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ።

17ንጉሡ አካዝም የጐንና የጐን ሳንቃዎቹን ነቅሎ ወሰደ፤ በተንቀሳቃሹ መቆሚያ ላይ ያሉትን የመታጠቢያ ሳሕኖች አስወገደ። የውሃ ማጠራቀሚያውን ክብ ገንዳ ከታች ተሸክመው ከያዙት ከዐሥራ ሁለቱ የናስ ቅርጽ ኮርማዎች ላይ አውርዶ በጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ አስቀመጠው። 18የአሦርንም ንጉሥ ለማስደሰት ሲል፣ በዕለተ ሰንበት ንጉሣዊ ዙፋን16፥18 የሰብዓ ሊቃናት መሥዋዕት ትርጕም፣ የዙፋኑ ሰሌዳ ይላል። እንዲዘረጋበት በቤተ መቅደሱ ውስጥ የተሠራውን ከፍ ያለ ስፍራና ነገሥታቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚገቡበትን በውጭ ያለውን መግቢያ አነሣ።

19በአካዝ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 20አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ከእነርሱ ጋር በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ ሕዝቅያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

列王纪下 16:1-20

亚哈斯做犹大王

1利玛利的儿子比加执政第十七年,犹大约坦的儿子亚哈斯登基。 2他二十岁登基,在耶路撒冷统治十六年。他没有效法他祖先大卫做耶和华视为正的事, 3反而步以色列诸王的后尘,效法耶和华在以色列人面前赶走的外族人的可憎行径,把自己的儿子焚烧献作祭物。 4他在丘坛、山冈和绿树下献祭烧香。

5亚兰利汛利玛利的儿子以色列比加前来攻打耶路撒冷,围住亚哈斯,但屡攻不下。 6当时,亚兰利汛收复以拉他,赶走城内的犹大人。亚兰人至今居住在那里。 7亚哈斯差遣使者去见亚述提革拉·毗列色,对他说:“我是你的仆人、你的儿子,现在亚兰王和以色列王攻打我,求你从他们手中拯救我。” 8亚哈斯把耶和华殿里和王宫库房里的金银送给亚述王。 9亚述王答应了他,起兵攻陷大马士革,杀了利汛,把城中的居民掳到吉珥

10亚哈斯王在大马士革亚述提革拉·毗列色的时候,看到一座坛,便派人将坛的模型和详细的制造方法送到乌利亚祭司那里。 11乌利亚祭司按照送来的模型,在亚哈斯王返回之前建造了一座坛。 12王从大马士革回来,看见那座坛,就到上面献祭。 13他在上面献上燔祭、素祭和奠祭,又将平安祭祭牲的血洒在坛上。 14他把献给耶和华的铜坛从耶和华的殿前搬到新坛的北边,铜坛原来放在殿和新坛之间。 15他吩咐乌利亚祭司:“要在这座大坛上献早晨的燔祭、晚上的素祭,王的燔祭、素祭,国中民众的燔祭、素祭和奠祭,燔祭牲和平安祭牲的血也要洒在上面,但铜坛要供我个人求问之用。” 16乌利亚祭司遵命而行。

17亚哈斯王拆掉盆座的镶板,搬走盆,将铜海从铜牛背上搬下来,放在铺石的地上。 18为了亚述王,他挪走耶和华殿里为安息日而盖的走廊,封闭了王从外面进耶和华殿的入口。

19亚哈斯其他的事都记在犹大的列王史上。 20亚哈斯与祖先同眠后,葬在大卫城他的祖坟里。他儿子希西迦继位。