2 ነገሥት 15 – NASV & PCB

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 15:1-38

የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ

1፥1-7 ተጓ ምብ – 2ዜና 26፥3-421-23

1የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በሃያ ሰባተኛው፣ ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ ነገሠ። 2ሲነግሥም ዕድሜው ዐሥራ ስድስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ አምሳ ሁለት ዓመት ገዛ። እናቱም ይኮልያ የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። 3አባቱ አሜስያስ እንዳደረገው ሁሉ ዓዛርያስም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ። 4ይሁን እንጂ በየኰረብታው ላይ ያሉት የማምለኪያ ስፍራዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በዚያ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጤሱን እንደ ቀጠለ ነበር።

5እግዚአብሔርም ንጉሡን እስከሚሞትበት ቀን ድረስ በለምጽ15፥5 የዕብራይስጡ ቃል፣ ቈዳን የሚያጠቁትን ማንኛውንም ዐይነት በሽታዎች ያመለክታል። መታው፤ በተለየ ቤትም ይኖር ነበር። በዚያን ጊዜ ቤተ መንግሥቱን በኀላፊነት የሚመራውና የአገሩንም ሕዝብ የሚያስተዳድረው የንጉሡ ልጅ ኢዮአታም ነበር።

6በዓዛርያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 7ዓዛርያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ በአባቶቹ መቃብር አጠገብ ቀበሩት። ልጁ ኢዮአታምም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

የእስራኤል ንጉሥ ዘካርያስ

8የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት፣ የኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ስድስት ወርም ገዛ። 9አባቱ እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልተመለሰም።

10የያቤስ ልጅ ሰሎም በዘካርያስ ላይ አሤረበት፤ በሕዝቡ15፥10 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማምል። አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ግን፣ በኢብላም ይላሉ። ፊት አደጋ ጥሎ ገደለው፤ በእግሩም ተተክቶ ነገሠ። 11በዘካርያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቧል። 12በዚህም እግዚአብሔር ለኢዩ፣ “ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ”15፥12 2ነገ 10፥30 ይመ ሲል የተናገረው ቃል ተፈጸመ።

የእስራኤል ንጉሥ ሰሎም

13የይሁዳ ንጉሥ ዖዝያን በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የኢያቤስ ልጅ ሰሎም በእስራኤል ላይ ነገሠ። በሰማርያ ተቀምጦ አንድ ወር ገዛ። 14የጋዲ ልጅ ምናሔም ከቴርሳ ወጥቶ ወደ ሰማርያ በመሄድ አደጋ ጥሎ የኢያቤስን ልጅ ሰሎምን ገደለው፤ ከዚያም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

15በሰሎም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራና የጠነሰሰውም ሤራ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፏል።

16በዚያን ጊዜም ምናሔም ከቴርሳ ወጥቶ በቲፍሳና በከተማዪቱ ነዋሪዎች ላይ ሁሉ፣ በአካባቢዋም ጭምር አደጋ ጣለ፤ ይህን ያደረገውም የከተማዪቱን በሮች ለመክፈት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ነበር፤ ቲፍሳን መታት፤ የነፍሰጡሮችንም ሆድ ሁሉ ቀደደ።

የእስራኤል ንጉሥ ምናሔም

17የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት፣ የጋዲ ልጅ ምናሔም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በሰማርያ ተቀምጦም ዐሥር ዓመት ገዛ። 18በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ በዘመኑም ሁሉ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልተመለሰም።

19ከዚያም የአሦር ንጉሥ ፎሓ15፥19 ቴልጌልቴልፌልሶርም ይባላል። ምድሪቱን ወረረ፤ ምናሔም ርዳታውን ለማግኘትና በመንግሥቱ ላይ ያለውን ይዞታ ለማጽናት ሲል፣ አንድ ሺሕ መክሊት15፥19 34 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ብር ሰጠው። 20ምናሔም ገንዘቡ እንዲዋጣ ያደረገው ከእስራኤል ሲሆን፣ ይህንም ያደረገው ለአሦር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ እያንዳንዱ ሀብታም አምሳ፣ አምሳ ሰቅል15፥20 0.6 ኪሎ ግራም ያህል ነው። ብር እንዲያዋጣ በማስገደድ ነበር። ስለዚህ የአሦር ንጉሥ በዚያች አገር አልቈየም፤ ተመልሶ ሄደ።

21በምናሔም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 22ምናሔም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁ ፋቂስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

የእስራኤል ንጉሥ ፋቂስያስ

23የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ በነገሠ በአምሳኛው ዓመት፣ የምናሔም ልጅ ፋቂስያስ በሰማርያ ከተማ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ ሁለት ዓመትም ገዛ። 24ፋቂስያስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም፣ እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልተመለሰም። 25ከጦር አለቆቹ አንዱ የሆነው የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ አሤረበት፤ አምሳ የገለዓድ ሰዎች ይዞ በመሄድ፣ ሰማርያ ቤተ መንግሥት ባለው ምሽግ ፋቂስያስን ከአርጎብና ከአርያ ጋር ገደለው፤ በእግሩም ተተክቶ ነገሠ።

26በፋቂስያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ የፈጸመውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፏል።

የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ

27የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ በነገሠ በአምሳ ሁለተኛው ዓመት የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በሰማርያ ከተማ፣ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ሃያ ዓመትም ገዛ። 28እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልተመለሰም።

29በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን፣ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮን፣ አቤልቤትመዓካን፣ ያኖዋን፣ ቃዴስንና ሐጾርን፣ ገለዓድንና ገሊላን፣ የንፍታሌምንም ምድር ጭምር ያዘ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ወደ አሦር ወሰደው። 30ከዚያም የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ ላይ አሤረበት፤ አደጋ ጥሎም ገደለው፤ የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም በነገሠ በሃያኛው ዓመትም ሆሴዕ በፋቁሔ እግር ተተክቶ ነገሠ። 31በፋቁሔ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ የፈጸማቸውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአታም

15፥33-38 ተጓ ምብ – 2ዜና 2፥1-47-9

32የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ የይሁዳ ንጉሥ የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም ነገሠ። 33ሲነግሥም ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ ኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም የሳዶቅ ልጅ ስትሆን፣ ኢየሩሳ ትባል ነበር። 34አባቱ ዖዝያን እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ። 35ይሁን እንጂ በየኰረብታው ላይ ያሉት የማምለኪያ ስፍራዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በዚያ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጤሱን እንደ ቀጠለ ነበር። ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር መልሶ ሠራ።

36በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 37በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔን ይሁዳን እንዲወጉ አደረገ። 38ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ አባቶቹ በተቀበሩበትም በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አካዝም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

Persian Contemporary Bible

دوم پادشاهان 15:1-38

عزيا، پادشاه يهودا

(دوم تواريخ 26‏:1‏-23)

1در بيست و هفتمين سال سلطنت يربعام دوم پادشاه اسرائيل، عُزيا (پسر امصيا) پادشاه يهودا شد. 2او شانزده ساله بود كه بر تخت سلطنت نشست و پنجاه و دو سال در اورشليم سلطنت كرد. (مادرش يكليا نام داشت و از اهالی اورشليم بود.) 3او مانند پدرش امصيا آنچه در نظر خداوند پسنديده بود، انجام می‌داد. 4ولی باز بتخانه‌های روی تپه‌ها كه مردم در آنجا قربانی می‌كردند و بخور می‌سوزانيدند، باقی ماند. 5خداوند او را به مرض جذام مبتلا كرد و تا روز وفاتش جذامی باقی ماند. او تنها، در يک خانه به سر می‌برد و پسرش يوتام امور مملكت را اداره می‌كرد. 6شرح بقيهٔ رويدادهای دوران سلطنت عزيا و كارهای او در كتاب «تاريخ پادشاهان يهودا» نوشته شده است. 7وقتی عزيا مرد او را در آرامگاه سلطنتی در شهر داوود دفن كردند و پسرش يوتام به جايش پادشاه شد.

زكريا، پادشاه اسرائيل

8در سی و هشتمين سال سلطنت عزيا پادشاه يهودا، زكريا (پسر يربعام دوم) پادشاه اسرائيل شد و شش ماه در سامره سلطنت نمود. 9او نيز مانند اجدادش نسبت به خداوند گناه ورزيد و از گناهان يربعام اول (پسر نباط) كه اسرائيل را به گناه كشاند، دست برنداشت. 10شلوم (پسر يابيش) بر ضد او توطئه كرد و او را در حضور مردم كشت و خود به سلطنت رسيد. 11شرح بقيهٔ رويدادهای دوران سلطنت زكريا در كتاب «تاريخ پادشاهان اسرائيل» آمده است. 12به اين ترتيب، آنچه كه خداوند دربارهٔ ييهو15‏:12 نگاه کنيد به 10‏:30.‏ فرموده بود، به وقوع پيوست كه خاندان او تا نسل چهارم بر تخت سلطنت اسرائيل خواهند نشست.

شلوم، پادشاه اسرائيل

13در سی و نهمين سال سلطنت عزيا پادشاه يهودا، شلوم (پسر يابيش) پادشاه اسرائيل شد و يک ماه در سامره سلطنت كرد.

14منحيم (پسر جادی) از ترصه به سامره آمده، او را كشت و خود به جای وی بر تخت سلطنت نشست. 15شرح بقيهٔ رويدادهای سلطنت شلوم و توطئهٔ15‏:15 نگاه کنيد به آيهٔ 10.‏ او در كتاب «تاريخ پادشاهان اسرائيل» نوشته شده است.

16منحيم شهر تفصح و حومهٔ آن را ويران نموده، اهالی آنجا را كشت و شكم زنان حامله را پاره كرد، چون مردم آنجا حاضر نبودند تسليم او شوند.

منحيم، پادشاه اسرائيل

17در سی و نهمين سال سلطنت عزيا پادشاه يهودا، منحيم (پسر جادی) پادشاه اسرائيل شد و ده سال در سامره سلطنت كرد. 18او نيز مانند يربعام (پسر نباط) نسبت به خداوند گناه ورزيد و اسرائيل را به گناه كشاند.

19در زمان او تغلت فلاسر، پادشاه آشور به سرزمين اسرائيل هجوم آورد، ولی منحيم پادشاه سی و چهار تن نقره به او باج داد و به كمک وی سلطنت خود را بر اسرائيل تثبيت نمود. 20منحيم اين پول را به شكل ماليات به زور از ثروتمندان وصول نمود. هر يک از آنها پنجاه مثقال نقره پرداختند. پس امپراتور آشور به سرزمين خود بازگشت.

21شرح بقيهٔ رويدادهای دوران سلطنت منحيم و كارهای او در كتاب «تاريخ پادشاهان اسرائيل» نوشته شده است. 22بعد از مرگ او پسرش فقحيا پادشاه شد.

فقحيا، پادشاه اسرائيل

23در پنجاهمين سال سلطنت عزيا پادشاه يهودا، فقحيا (پسر منحيم) پادشاه اسرائيل شد و دو سال در سامره سلطنت نمود، 24او نيز مانند يربعام (پسر نباط) نسبت به خداوند گناه ورزيد و اسرائيل را به گناه كشاند. 25فقح (پسر رمليا)، يكی از فرماندهان سپاه او، همراه پنجاه نفر ديگر از مردان جلعاد بر ضد او شورش كرد و او را در كاخ سلطنتی سامره كشت. (ارجوب و اريه نيز در اين شورش كشته شدند.) سپس فقح به جای او پادشاه شد.

26شرح بقيهٔ رويدادهای دوران سلطنت فقحيا و كارهای او در كتاب «تاريخ پادشاهان اسرائيل» نوشته شده است.

فقح، پادشاه اسرائيل

27در پنجاه و دومين سال سلطنت عزيا پادشاه يهودا، فقح (پسر رمليا) پادشاه اسرائيل شد و بيست سال در سامره سلطنت كرد. 28او نيز مانند يربعام (پسر نباط) نسبت به خداوند گناه ورزيد و اسرائيل را به گناه كشاند. 29در دورهٔ سلطنت فقح بود كه تغلت فلاسر، پادشاه آشور به اسرائيل حمله كرد و شهرهای عيون، آبل بيت‌معكه، يانوح، قادش، حاصور، جلعاد، جليل و تمام سرزمين نفتالی را به تصرف خود درآورد و مردم را اسير نموده، به آشور برد. 30آنگاه هوشع (پسر ايله) بر ضد فقح شورش كرد و او را كشت و خود بر تخت سلطنت نشست. هوشع در سال بيستم سلطنت يوتام (پسر عزيا) پادشاه يهودا، سلطنت خود را آغاز نمود.

31شرح بقيهٔ رويدادهای دوران سلطنت فقح و كارهای او در كتاب «تاريخ پادشاهان اسرائيل» نوشته شده است.

يوتام، پادشاه يهودا

(دوم تواريخ 27‏:1‏-9)

32در دومين سال سلطنت فقح پادشاه اسرائيل، يوتام (پسر عزيا) پادشاه يهودا شد. 33يوتام در سن بيست و پنج سالگی بر تخت سلطنت نشست و شانزده سال در اورشليم سلطنت نمود. (مادرش يروشا نام داشت و دختر صادوق بود). 34او مانند پدرش عزيا آنچه در نظر خداوند پسنديده بود، انجام می‌داد، 35ولی بتخانه‌های روی تپه‌ها را كه مردم در آنجا قربانی می‌كردند و بخور می‌سوزانيدند، خراب نكرد. يوتام دروازهٔ بالايی خانهٔ خداوند را بازسازی كرد.

36شرح بقيهٔ رويدادهای دوران سلطنت يوتام و كارهای او در كتاب «تاريخ پادشاهان يهودا» نوشته شده است. 37(در آن روزها خداوند، رصين پادشاه سوريه و فقح پادشاه اسرائيل را بر ضد يهودا برانگيخت.) 38وقتی يوتام مرد او را در آرامگاه سلطنتی در اورشليم دفن كردند و پسرش آحاز به جای او پادشاه شد.