2 ነገሥት 12 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 12:1-21

ኢዮአስ ቤተ መቅደሱን ዐደሰ

12፥1-21 ተጓ ምብ – 2ዜና 24፥1-1424፥23-27

1ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አርባ ዓመት ገዛ። እናቱ ሳብያ የተባለች የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ ነበረች። 2ካህኑ ዮዳሄ ያስተምረው በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ። 3ይሁን እንጂ የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በእነዚህ ቦታዎች መሠዋቱንና ማጠኑን እንደ ቀጠለ ነበር።

4ኢዮአስ ካህናቱን እንዲህ አላቸው፤ “ከሕዝብ ቈጠራ የተገኘውንና በስእለት የገባውን እንዲሁም በራስ ፈቃድ ለቤተ መቅደሱ የተሰጠውን የተቀደሰ ገንዘብ በሙሉ ሰብስቡ። 5እያንዳንዱም ካህን ገንዘቡን ከገንዘብ ያዡ እጅ ይቀበል፤ እንደ አስፈላጊነቱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ለማደስ ይዋል።”

6ይሁን እንጂ እስከ ሃያ ሦስተኛው የኢዮአስ ዘመነ መንግሥት ካህናቱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን አላደሱም ነበር። 7ስለዚህ ኢዮአስ ካህኑን ዮዳሄንና ሌሎቹን ካህናት ጠርቶ፣ “በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ያላደሳችሁት ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው፤ ቀጥሎም፣ “ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ለማደስ ይዋል እንጂ ከገንዘብ ያዦች አትቀበሉ” አላቸው። 8ካህናቱም ከእንግዲህ ከሕዝቡ ገንዘብ ላለመሰብሰብና ቤተ መቅደሱንም ራሳቸው ላለማደስ ተስማሙ።

9ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀለት፤ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚያስገባው በስተ ቀኝ በኩል በመሠዊያው አጠገብ አኖረው። በራፉን የሚጠብቁት ካህናትም ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣውን ገንዘብ በሙሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡ ነበር። 10በሣጥኑም ውስጥ ብዙ ገንዘብ መኖሩን በሚያዩበት ጊዜ ሁሉ፣ የንጉሡ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ መጥተው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የገባውን ገንዘብ ቈጥረው በየከረጢቱ በማስገባት ቋጥረው ያኖሩት ነበር። 11የገንዘቡ ልክም ተመዝኖ ከታወቀ በኋላ፣ የቤተ መቅደሱን ሥራ በኀላፊነት እንዲያሠሩ ለተመደቡት ሰዎች ገንዘቡን ያስረክቧቸዋል፤ ይህም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለሚሠሩ ዐናጢዎችና ግንበኞች፣ 12ለድንጋይ ጠራቢዎችና ለድንጋይ ቅርጽ አውጭዎች የሚከፈል፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለሚታደስበት ዕንጨትና ጥርብ ድንጋይ መግዣ የሚውል ነበር።

13ለቤተ መቅደሱ ከገባው ገንዘብ ግን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግልጋሎት ለሚውሉ የብር ጽዋዎች፣ መኰስተሪያዎች፣ ድስቶች፣ መለከቶችና ወይም ለሌሎች የወርቅም ሆነ የብር ዕቃዎች መሥሪያ አልዋለም፤ 14የተከፈለው ግን ቤተ መቅደሱን ለሚያድሱ ሠራተኞች ብቻ ነበር። 15ለሠራተኞቹ እንዲከፍሉ ገንዘቡ የተሰጣቸው ሰዎች ፍጹም ታማኞች በመሆናቸው ተቈጣጣሪ ማድረግ አላስፈለጋቸውም ነበር። 16ስለ በደል መሥዋዕትና ስለ ኀጢአት መሥዋዕት የሚቀርበው ገንዘብ ግን የካህናቱ በመሆኑ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አይገባም ነበር።

17በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል ወጣ፤ ጌትንም አደጋ ጥሎ ያዛት። ከዚያም በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ፊቱን አዞረ። 18የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስ ግን አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥ፣ ኢዮሆራም፣ አካዝያስ ለእግዚአብሔር ቀድሰው የለዩአቸውን የተቀደሱ ዕቃዎች በሙሉ፣ እርሱ ራሱ የቀደሳቸው ስጦታዎች እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤቶች የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ሰብስቦ ለሶርያ ንጉሥ ለአዛሄል ላከለት፤ አዛሄልም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ። 19ኢዮአስ በዘመነ መንግሥቱ ያከናወነው ሌላው ተግባርና የፈጸመው ሥራ ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 20ሹማምቱም በእርሱ ላይ ዐመፁበት፤ ቍልቍል ወደ ሲላ በሚወስደው መንገድ ላይ በቤት ሚሎ ገደሉት። 21ገዳዮቹ ሹማምትም የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ነበሩ። እርሱም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አሜስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

列王纪下 12:1-21

约阿施做犹大王

1以色列耶户执政第七年,约阿施登基,在耶路撒冷执政四十年。他母亲叫西比亚,是别示巴人。 2耶何耶大祭司的教导下,约阿施一生做耶和华视为正的事。 3但他没有拆毁丘坛,人们仍在那里献祭烧香。

4约阿施对祭司们说:“你们要收集那些奉献到耶和华殿的圣银,即人口普查时收取的银子、个人还愿的银子和自愿奉献的银子。 5每位祭司要从奉献的人手中收取银子,用来修殿。” 6可是,直到约阿施执政第二十三年,祭司仍未动工。 7约阿施召来耶何耶大祭司及其他祭司,对他们说:“你们为什么还不修殿呢?不要再向奉献的人收银子了,要把所收的银子交出来修殿。” 8祭司们答应不再向民众收钱,但也不动工修殿。

9耶何耶大祭司在耶和华殿的入口右边的祭坛旁放了一个箱子,箱盖上开了个洞。守门的祭司将奉献到耶和华殿的所有银子放进箱子里。 10箱子里的银子多了,王的书记和大祭司就把银子点好,装在袋子里。 11他们将称好的银子交给修耶和华殿的督工。督工把报酬转交给在殿里工作的木匠、建筑工人、 12泥水匠和石匠,购买修耶和华殿用的木料和凿好的石头,并支付其他的修殿费用。 13献到耶和华殿里的银子没有用于制造殿里的银碗、蜡剪、盆、号及其他金银器皿, 14只用于修殿。 15督工们办事忠诚可靠,不需要跟他们清算账目。 16赎过祭和赎罪祭的银子没有带到耶和华的殿里,而是归给祭司。

17那时,亚兰哈薛攻陷了迦特,准备进攻耶路撒冷18犹大约阿施把先王约沙法约兰亚哈谢和他自己奉献的圣物以及耶和华殿里和王宫库房里的所有金子都送给了亚兰哈薛哈薛便从耶路撒冷退兵。

19约阿施其他的事及其一切作为都记在犹大的列王史上。 20约阿施的臣仆谋反,在去悉拉途中的米罗宫杀了他。 21杀他的是示米押的儿子约撒甲朔默的儿子约萨拔约阿施葬在大卫城他的祖坟里。他儿子亚玛谢继位。