2 ነገሥት 11 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 11:1-21

ጎቶልያና ኢዮአስ

11፥1-21 ተጓ ምብ – 2ዜና 22፥10–23፥21

1የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን በሰማች ጊዜ፣ ንጉሣዊውን ቤተ ሰብ በሙሉ አጠፋች። 2የንጉሥ ኢዮራም ልጅ፣ የአካዝያስ እኅት ዮሳቤት ግን የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሊገደሉ ከነበሩት ልዑላን መካከል ሰርቃ ወሰደችው። እንዳይገድሉትም ከጎቶልያ በመደበቅ እርሱንና ሞግዚቱን በአንድ እልፍኝ ሸሸገቻቸው። 3ጎቶልያ አገሩን በምትገዛበት ጊዜም ከሞግዚቱ ጋር ስድስት ዓመት በእግዚአብሔር ቤት ተሸሸገ።

4በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ ካራውያንንና ዘብ ጠባቂዎቹን የሚያዝዙትን የመቶ አለቆች እርሱ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አደረገ። ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን በማድረግ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አስማላቸው፤ ከዚያም የንጉሡን ልጅ አሳያቸው። 5እንዲህም ሲል አዘዛቸው፤ “እናንተ የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሦስት ምድብ ሆናችሁ በሰንበት ዕለት ዘብ ከምትጠብቁት መካከል አንዱ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ 6ሌላው ከሦስት አንዱ የሱርን በር ይጠብቅ፤ የቀረው ሌላው አንድ ሦስተኛው እጅ ደግሞ ቤተ መቅደሱን ተራ ገብቶ ከሚጠብቀው ከዘብ ጥበቃው ኋላ ያለውን በር ይጠብቅ። 7እናንተ እንደ ተለመደው በሰንበት ዕለት ከዘብ ጥበቃ ነጻ የምትሆኑት ሁለት ሦስተኛው እጅ ግን ንጉሡ ያለበትን ቤተ መቅደስ ጠብቁ። 8ሁላችሁም መሣሪያችሁን ይዛችሁ በንጉሡ ዙሪያ ሁኑ፤ የሚቀርባችሁ ቢኖር11፥8 ወይም፣ ወደ ቅጥራችሁ የሚደርስ ቢኖር ግን ይገደል። ንጉሡ በሚወጣበትም ሆነ በሚገባበት ጊዜ ሁሉ አትለዩት።”

9የመቶ አለቆቹም ካህኑ ዮዳሄ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ እያንዳንዳቸውም በሰንበት ዕለት ለዘብ ጥበቃ የሚገቡትንና ከዘብ ጥበቃ የሚወጡትን ጭፍሮቻቸውን ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ። 10ካህኑም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሥ ዳዊትን ጦርና ጋሻ ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው። 11ወታደሮቹም እያንዳንዳቸው መሣሪያቸውን ይዘው፣ ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ አንሥቶ እስከ ሰሜን ድረስ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አጠገብ በንጉሡ ዙሪያ ቆሙ።

12ዮዳሄም የንጉሡን ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነለት፤ የኪዳኑንም መጽሐፍ ሰጠው፣ መንገሡን ዐወጀ፤ ኢዮአስም ተቀብቶ ነገሠ። ከዚያም ሕዝቡ፣ “ንጉሡ ሺሕ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በማጨብጨብ ደስታቸውን ከፍ ባለ ድምፅ ገለጹ።

13ጎቶልያም የሰራዊቱንና የሕዝቡን ጩኸት በሰማች ጊዜ፣ ሕዝቡ ወዳለበት ወደ ቤተ መቅደሱ ሄደች። 14እነሆ፤ በወጉ መሠረት ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ፣ ሹማምቱና መለከት ነፊዎቹ ከአጠገቡ ሆነው አየች። የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ይፈነጥዝ፣ መለከትም ይነፋ ነበር። ጎቶልያም ልብሷን ቀድዳ፣ “ይህ ክሕደት ነው! ክሕደት ነው!” በማለት ጮኸች።

15ካህኑ ዮዳሄም ጭፍሮቹን የሚያዝዙትን የመቶ አለቆች፣ “በረድፍ በተሰለፉት ጭፍሮች መካከል አውጧት፤11፥15 ወይም፣ ከቅጥራችሁ መካከል የሚከተላትንም ሁሉ በሰይፍ በሉት” ሲል አዘዘ፤ ይህ የሆነውም ካህኑ አስቀድሞ፣ “በእግዚአብሔር ቤት መገደል የለባትም” በማለቱ ነበር። 16ስለዚህ ፈረሶች ወደ ቤተ መንግሥቱ በሚገቡበት ስፍራ ስትደርስ፣ ይዘው እዚያው ገደሏት።

17ዮዳሄም የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔርና በንጉሡ በሕዝቡም መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ፤ እንደዚሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን መሠረተ። 18የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በኣል ቤተ ጣዖት ሄደው አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት።

ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ። 19ከዚያም መቶ አለቆቹን፣ ካራውያንንና ዘበኞቹን እንዲሁም የአገሩን ሕዝብ በሙሉ በመያዝ ሁሉም በአንድነት ሆነው፣ ንጉሡን ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወስደው በዘብ ጠባቂዎች ቅጥር በር በኩል ታች ወዳለው ቤተ መንግሥት ይዘውት ገቡ፤ ንጉሡም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ 20የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አለው፤ ጎቶልያ ቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሰይፍ ተገድላ ስለ ነበር፣ ከተማዪቱ ጸጥ አለች። 21ኢዮአስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

列王紀下 11:1-21

耶何耶大立約阿施為王

1亞哈謝的母親亞她利雅見兒子死了,便決定除掉王室後裔。 2約蘭王的女兒、亞哈謝的妹妹約示芭把亞哈謝的兒子約阿施從被殺的王子中偷出來,將他和乳母藏在一間臥室裡,才躲過亞她利雅,使約阿施沒有被殺。 3約阿施和他的乳母在耶和華的殿裡藏了六年,那時亞她利雅篡位當政。

4第七年,耶何耶大派人召迦利11·4 迦利人」指雇來保護王的外族衛兵。和衛兵的百夫長們到耶和華的殿裡,與他們立約,讓他們在耶和華的殿裡起誓,然後把約阿施王子帶到他們面前。 5耶何耶大吩咐他們說:「你們在安息日值班的,三分之一要守衛王宮, 6三分之一要守衛蘇珥門,三分之一要守住衛兵院後門。你們要輪流守衛。 7安息日沒有值班的兩隊要在耶和華的殿裡保護王, 8各人要手持兵器護衛在王周圍。凡擅自闖入者,都要處死。無論王去哪裡,你們都要緊隨左右。」 9眾百夫長依令而行,各自率領安息日值班和休班的隨從來見耶何耶大10耶何耶大把耶和華殿中大衛王的矛槍和盾牌交給百夫長。 11從殿右到殿左,在祭壇和殿周圍,衛兵都手持兵器護衛王。 12耶何耶大祭司領王子出來,給他戴上王冠,把律法書交給他,膏立他為王。眾人都鼓掌高呼:「願王萬歲!」

13亞她利雅聽見衛兵和眾人的歡呼聲,便走進耶和華的殿,眾人都聚集在那裡。 14她看見王照例站在柱旁,百夫長和吹號的人侍立在王左右,眾人都歡呼吹號,便撕裂衣服喊叫:「反了!反了!」 15耶何耶大祭司認為不可在耶和華的殿裡處死亞她利雅,便命令領兵的百夫長:「把她帶出去。凡跟隨她的,都要殺掉。」 16他們抓住她,把她帶到馬匹進出王宮的入口,在那裡殺了她。

17耶何耶大讓王及民眾與耶和華立約,做耶和華的子民,也讓王與民眾立約。 18於是,民眾出去拆毀了巴力廟,砸碎祭壇和偶像,在壇前殺了巴力的祭司瑪坦耶何耶大派守衛保護耶和華的殿, 19然後率領百夫長、迦利人、衛兵和民眾,護送王從耶和華的殿下來,經過衛兵院的門進入王宮。這樣,約阿施坐上了王位。 20民眾都歡喜快樂,城裡安定,因為亞她利雅已在王宮那裡被處死。 21約阿施七歲登基。