2 ሳሙኤል 9 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

2 ሳሙኤል 9:1-13

ዳዊትና ሜምፊቦስቴ

1ዳዊትም፣ “ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው ይኖር ይሆን?” በማለት ጠየቀ።

2በዚያን ጊዜ ከሳኦል ቤት ሲባ የሚባል አንድ አገልጋይ ስለ ነበር፣ ወደ ዳዊት እንዲሄድ ነገሩት። ንጉሡም፣ “ሲባ የምትባለው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው።

እርሱም፣ “አዎን እኔ አገልጋይህ ነኝ” አለ።

3ንጉሡም፣ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው።

ሲባም ለንጉሡ፣ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት።

4ንጉሡም፣ “የት ነው ያለው?” ብሎ ጠየቀ።

ሲባም፣ “ሎደባር በተባለ ስፍራ በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት ይገኛል” ብሎ መለሰለት።

5ስለዚህም ንጉሥ ዳዊት፣ ሜምፊቦስቴን ከዓሚኤል ከማኪር ቤት ከሎደባር ልኮ አስመጣው።

6የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፣ አክብሮቱን ለመግለጥ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።

ዳዊትም፣ “ሜምፊቦስቴ” ብሎ ጠራው።

እርሱም፣ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ።

7ዳዊትም፣ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል በርግጥ ቸርነት አደርግልሃለሁና። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።

8ሜምፊቦስቴ ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፣ “እንደ ሞተ ውሻ ለምቈጠር ለእኔ ይህን ያህል የምታደርግልኝ አገልጋይህ ኧረ ማን ነኝ?” አለ።

9ከዚያም ንጉሡ የሳኦልን አገልጋይ ሲባን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “የሳኦልና የቤተ ሰቡ የሆነውን ሁሉ ለጌታህ የልጅ ልጅ ሰጥቼዋለሁ። 10አንተ፣ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን ዕረሱለት፣ ምርቱንም አግቡለት። የጌታህ የልጅ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ምንጊዜም ከማእዴ ይበላል።” በዚያን ጊዜ ሲባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት።

11ከዚያም ሲባ ንጉሡን፣ “ጌታዬ ንጉሥ፣ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፣ አገልጋይህም ይፈጽመዋል” አለው። ስለዚህም ሜምፊቦስቴ ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ሆኖ ከዳዊት9፥11 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ከእኔ ይላል። ማእድ ይበላ ነበር።

12ሜምፊቦስቴ ሚካ የተባለ አንድ ትንሽ ልጅ ነበረው፤ የሲባ ቤተ ሰዎች በሙሉ ሜምፊቦስቴን ያገለግሉት ነበር። 13ሜምፊቦስቴም ሁልጊዜ ከንጉሥ ማእድ ስለሚበላ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነው፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ።

Japanese Contemporary Bible

サムエル記Ⅱ 9:1-13

9

ダビデとメフィボシェテ

1ある日、ダビデは、サウルの家系にまだ生き残っている者がいないか、気になり始めました。もしいれば、ヨナタンとの約束があったので、情けをかけてやりたいと思ったのです。 2かつてサウル王に仕えたツィバという男のことを耳にすると、さっそく召し出して尋ねました。

「ツィバとはおまえか。」

「そうでございます。」

3「サウル王の血筋で、だれか生き残った者はいないか。いれば、その者を手厚くもてなし、立てた誓いを果たしたいのだが。」

「ヨナタン様のお子で、足の不自由な方がご存命です。」

4「その子はどこにいるのだ。」

「今、ロ・デバルのマキルの屋敷においでです。」

5-6そこでダビデ王は、ヨナタンの息子で、サウルの孫に当たるメフィボシェテを迎えにやりました。メフィボシェテは恐れながらやって来て、ダビデの前にうやうやしくひれ伏しました。 7そんな彼に、ダビデは優しく声をかけました。「心配には及ばない。来てもらったのはほかでもない、父君ヨナタンとの誓いを果たしたいと思ったのだ。力になりたいのだ。あなたの祖父、サウル王の土地は全部返そう。よかったら、この宮殿で暮らしなさい。」

8メフィボシェテは王の前に深々と頭をたれ、「死んだ犬も同然の私に、なんというご親切を」と言いました。

9王はツィバを呼び出し、こう申し渡しました。「よいか、サウル王とその家の物はみな、主君サウルの孫に返した。 10-11おまえは自分の息子や召使たちとともに、地を耕し、彼の家族のために仕えなさい。しかし、メフィボシェテはここで、私といっしょに暮らす。」

ツィバには、息子が十五人と召使が二十人いました。そこで、「承知しました。ご命令のとおりにします」と答えました。以来、メフィボシェテは、ダビデ王の子ども同様に扱われ、いつも王といっしょに食事をしました。 12メフィボシェテには、ミカという幼い子がいました。ツィバの家の者はみなメフィボシェテのしもべになりましたが、 13メフィボシェテはエルサレムに移って、ダビデの宮殿で暮らしました。彼は両足が不自由でした。