2 ሳሙኤል 4 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ሳሙኤል 4:1-12

ኢያቡስቴ ተገደለ

1አበኔር በኬብሮን መሞቱን የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በሰማ ጊዜ ወኔ ከዳው፤ መላው እስራኤልም ደነገጠ። 2በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም ከብንያም ነገድ የብኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ብኤሮት ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ትቈጠራለች። 3የብኤሮት ሕዝብ ወደ ጌቴም በመሸሽ እስከ ዛሬም በመጻተኝነት እዚያው ይኖራልና።

4የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር።

5በዚህ ጊዜ የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ለመሄድ ዐልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፣ ሙቀት ሲሆን እኩለ ቀን ላይ ደረሱ፤ 6ስንዴ እንደሚፈልግም ሰው ሆነው ወደ ቤቱ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ሆዱ ላይ ወጉት። ከዚያም ሬካብና ወንድሙ በዓና ሹልክ ብለው ወጡ።

7ወደ ቤቱ ውስጥ የገቡት ኢያቡስቴ በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ተኝቶ ሳለ ነበር፤ ወግተው ከገደሉትም በኋላ ራሱን ቈርጠው በመውሰድ፣ ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ መንገድ ተጓዙ። 8የኢያቡስቴንም ራስ ወደ ኬብሮን ዳዊት ዘንድ አምጥተው ንጉሡን፣ “አንተን ሊገድል ይፈልግ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ እነሆ እግዚአብሔር በዛሬው ቀን ስለ ጌታዬ ስለ ንጉሡ ሳኦልንና ዘሩን ተበቅሏል” አሉት።

9ዳዊትም ለብኤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን10የምሥራች ያመጣልኝ መስሎት፣ ‘እነሆ ሳኦል ሞተ’ ብሎ የነገረኝን ሰው ይዤ ጺቅላግ ላይ ገደልሁት፤ እንግዲህ ለዚያ ሰው ስላመጣው ምሥራች የሸለምሁት ይህን ነበር። 11ታዲያ በገዛ ቤቱ፣ በገዛ ዐልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፣ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?”

12ስለዚህም ዳዊት የራሱን ሰዎች አዘዘ፤ እነርሱንም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቈርጠው በኬብሮን ካለው ኵሬ አጠገብ ሰቀሏቸው። ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር አጠገብ ቀበሩት።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

撒母耳記下 4:1-12

伊施波設被殺

1掃羅的兒子伊施波設聽到押尼珥死在希伯崙,嚇得手腳發軟,整個以色列都震驚不已。 2那時,掃羅的兒子有兩個帶兵的將領,一個叫巴拿,一個叫利甲,他們是來自比錄便雅憫臨門的兒子。 3原來的比錄人逃到基他音,寄居在那裡,直到今日。

4掃羅的兒子約拿單有個兒子叫米非波設,雙腿是瘸的。掃羅約拿單耶斯列陣亡的時候,他才五歲。乳娘抱著他倉皇逃命,不慎把他掉在地上,摔成了瘸子。

5一天,伊施波設正在午睡,臨門的兩個兒子利甲巴拿來到他家。 6-7他們裝作是來取麥子,進入伊施波設的寢室,趁他正躺在床上熟睡,用刀刺透他的肚子殺了他,割下他的首級,拿著連夜穿過亞拉巴逃跑了。 8他們把伊施波設的首級帶到希伯崙獻給大衛王,說:「這便是掃羅的兒子伊施波設的首級。掃羅是你的仇敵,曾試圖殺害你,今天耶和華為我主我王懲罰了掃羅和他的子孫。」 9大衛比錄臨門的兒子利甲及其兄弟巴拿說:「我憑救我脫離一切危難的永活的耶和華起誓, 10洗革拉曾有人向我報信說掃羅死了,他以為是來報喜訊,我抓住他,把他殺了。那就是我給他的報酬。 11更何況你們這些惡徒在這個無辜人的家裡把他殺死在床上,我怎能不向你們討這血債,把你們從世上除掉?」 12於是,大衛命令部下殺了他們,斬斷他們的手腳,把屍體掛在希伯崙的池旁。他們把伊施波設的頭顱葬在希伯崙押尼珥的墳墓裡。