2 ሳሙኤል 22 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

2 ሳሙኤል 22:1-51

የዳዊት የምስጋና መዝሙር

22፥1-51 ተጓ ምብ – መዝ 18፥1-50

1እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ዘመረ፤ 2እንዲህም አለ፤

እግዚአብሔር ዐለቴ ዐምባዬና ታዳጊዬ ነው፤

3አምላኬ፣ የምጠጋበት ዐለቴ፣

ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ22፥3 ቀንድ የጥንካሬ ወይም የኀይል ምልክት ነው። ነው።

እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤

ከኀይለኞች ሰዎች ታድነኛለህ።

4ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤

ከጠላቶቼም እድናለሁ።

5“የሞት ማዕበል ከበበኝ፤

የጥፋትም ጐርፍ አሰጠመኝ።

6የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤

የሞትም ወጥመድ ተጋረጠብኝ።

7በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤

ወደ አምላኬም ጮኽሁ።

እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤

ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ።

8ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤

የሰማያትም መሠረቶች22፥8 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ቩልጌትና ሱርስቱ ግን (እንዲሁም መዝ 18፥7 ይመ) ተራሮች ይላሉ። ተናጉ፤

እርሱ ተቈጥቷልና ራዱ።

9ከአፍንጫው የቍጣ ጢስ ወጣ፤

ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤

ከውስጡም ፍሙ ጋለ።

10ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤

ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።

11በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤

በነፋስም ክንፍ መጠቀ።22፥11 አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች (እንዲሁም መዝ 18፥10 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ እጅግ ብዙ የሆኑ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ተገለጠ ይላሉ።

12ጨለማው በዙሪያው እንዲከበው፣

ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ።

13በእርሱ ፊት ካለው ብርሃን፣

የመብረቅ ብልጭታ ወጣ።

14እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤

የልዑልም ድምፅ አስተጋባ።

15ፍላጻውን ሰድዶ ጠላቶቹን በተናቸው፤

መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።

16ከእግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫው

ከሚወጣው፣ ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣

የባሕር ሸለቆዎች ታዩ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።

17“ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤

ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ።

18ከብርቱ ጠላቶቼ፣

ከማልቋቋማቸውም ባላጋሮቼ ታደገኝ።

19በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤

እግዚአብሔር ግን ደገፈኝ።

20ሰፊ ወደ ሆነ ስፍራ አወጣኝ፤

በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ።

21እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መለሰልኝ፤

እንደ እጄም ንጹሕነት ብድራትን ከፈለኝ፤

22የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤

ከአምላኬም ዘወር ብዬ ክፉ ነገር አላደረግሁም።

23ሕጉ ሁሉ በፊቴ ነው፤

ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም።

24በፊቱ ያለ ነውር ነበርሁ፤

ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።

25እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣

በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና22፥25 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናትና የቩልጌት ትርጉሞች (እንዲሁም መዝ 18፥24 ይመ) ግን፣ እንደ እጄም ንጽሕና ይላሉ። ብድራትን ከፈለኝ።

26“ለታማኝ ሰው አንተም ታማኝ መሆንህን፣

ለቅን ሰው አንተም ቅን መሆንህን ታሳያለህ።

27ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣

ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።

28አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህ፤

ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፣ ትዕቢተኞችን ይመለከታል።

29እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴ ነህ፤

እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።

30በአንተ ርዳታ በጠላት ሰራዊት ላይ ወደ ፊት ገፍቼ እሄዳለሁ22፥30 ወይም በጋሬጣዎች ውስጥ እሮጣለሁ

በአምላኬም ኀይል ቅጥሩን እዘላለሁ።

31“የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤

የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው፤

ለሚታመኑበትም ሁሉ ጋሻ ነው፤

32ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን አለና፤

ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው?

33ኀይልን የሚያስታጥቀኝ22፥33 የሙት ባሕር ጥቅልል፣ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች፣ የቩልጌትና የሱርስት ቅጆች (እንዲሁም መዝ 18፥32 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ የማሶሬቱ ቅጅ ግን፣ ጠንካራ መሸሸጊያ የሚሆነኝ ይላል።

መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው።

34እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች ያበረታል፤

በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል።

35እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤

ክንዶቼም የናስ ቀስት ይገትራሉ።

36የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤

ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል።

37ርምጃዬን አሰፋህ፤

እግሮቼም አልተሰነካከሉም።

38“ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤

እስኪደመሰሱም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም።

39ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤

ከእግሬም ሥር ወድቀዋል።

40ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፣

ተቃዋሚዎቼንም ከእግሬ ሥር አንበረከክሃቸው።

41ጠላቶቼ ፊታቸውን አዙረው እንዲሸሹ አደረግሃቸው።

ባላንጣዎቼንም ደመሰስኋቸው።

42ለርዳታ ጮኹ፤ ያዳናቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን

አልመለሰላቸውም።

43በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አድቅቄ ፈጨኋቸው፤

በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም።

44“በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤

የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ።

የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ፤

45ባዕዳን ሊለማመጡኝ መጡ፤

እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል።

46ባዕዳን ፈሩ፤

ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ22፥46 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የቩልጌቱ ቅጅ (እንዲሁም መዝ 18፥32 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ማሶሬቱ ግን ራሳቸውን ጐዱ ይላል።

47እግዚአብሔር ሕያው ነው፤ ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤

የድነቴ ዐለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል።

48የሚበቀልልኝ አምላክ፣

መንግሥታትንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤

49እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል።

አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤

ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ።

50ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤

በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም ምስጋና እዘምራለሁ።

51“ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤

ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፣

ለዘላለም የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳየዋል።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

撒母耳记下 22:1-51

大卫的颂歌

1耶和华从扫罗和所有仇敌手中拯救大卫那天,他向耶和华吟唱此诗:

2“耶和华是我的磐石,

我的堡垒,我的拯救者;

3我的上帝是保护我的磐石,

是我的盾牌,是拯救我的力量,

是我的堡垒,我的避难所,

我的救主。

你救我脱离残暴之徒。

4我求告当受颂赞的耶和华,

祂就从仇敌手中把我救出。

5“死亡的波涛环绕我,

罪恶的狂流淹没我。

6阴间的绳索捆绑我,

死亡的网罗笼罩我。

7“我在苦难中呼求耶和华,

向我的上帝求助,

祂从殿中垂听我的呼求,

我的声音达到祂耳中。

8“祂一发怒,大地震动,

穹苍的根基摇晃。

9祂的鼻孔冒烟,

口喷烈焰和火炭。

10祂拨开云天,

脚踩密云,亲自降临。

11祂乘着基路伯天使飞翔,

在风的翅膀上显现。

12祂藏身于黑暗中,

四围以密云作幔幕。

13祂面前的荣光中发出道道闪电。

14耶和华在天上打雷,

至高者发出声音。

15祂射出利箭驱散仇敌,

发出闪电击溃他们。

16耶和华斥责一声,

祂的鼻孔一吹气,

海底就显现,

大地也露出根基。

17“祂从高天伸手抓住我,

从深渊中把我拉上来。

18祂救我脱离强敌,

脱离我无法战胜的仇敌。

19他们在我危难之时攻击我,

但耶和华扶持我。

20祂领我到宽阔之地;

祂拯救我,因为祂喜悦我。

21“耶和华因我公义而善待我,

因我清白而赏赐我。

22因为我坚守祂的道,

没有作恶背弃我的上帝。

23“我遵守祂一切的法令,

没有把祂的律例弃置一旁。

24我在祂面前纯全无过,

没有沾染罪恶。

25耶和华因我公义、

在祂面前清白而奖赏我。

26“仁慈的人,你以仁慈待他;

纯全的人,你以纯全待他。

27纯洁的人,你以纯洁待他;

心术不正的人,你以计谋待他。

28你搭救谦卑的人,

鉴察、贬抑高傲的人。

29耶和华啊!你是我的明灯,

你使我的黑暗变为光明。

30我依靠你的力量迎战敌军,

靠着我的上帝跃过墙垣。

31“上帝的道完美,

耶和华的话纯全,

祂是投靠祂之人的盾牌。

32除了耶和华,谁是上帝呢?

除了我们的上帝,谁是磐石呢?

33上帝是我的坚固堡垒,

祂使我行为纯全。

34祂使我的脚如母鹿的蹄,

稳踏在高处。

35祂训练我的手怎样作战,

使我的手臂能拉开铜弓。

36你是拯救我的盾牌,

你的垂顾使我强大。

37你使我脚下的道路宽阔,

不致滑倒。

38我追赶仇敌,击溃他们,

不消灭他们决不回头。

39我打垮他们,

使他们倒在我的脚下,

再也站不起来。

40你赐我征战的能力,

使我的仇敌降服在我脚下。

41你使我的仇敌狼狈而逃,

我歼灭了恨我的人。

42他们求助,却无人搭救。

他们呼求耶和华,祂也不应允。

43我把他们打得粉碎,

如同地上的灰尘,践踏他们,

就像践踏街上的泥土。

44你救我脱离我百姓的攻击,

让我成为列国的元首,

素不相识的民族也归顺我。

45外族人望风而降,俯首称臣。

46他们闻风丧胆,

战战兢兢地走出他们的城池。

47“耶和华永远活着,

保护我的磐石当受颂赞,

拯救我的上帝当受尊崇。

48祂是为我申冤的上帝,

祂使列邦臣服于我。

49祂救我脱离仇敌,

使我胜过强敌,

救我脱离残暴之徒。

50因此,耶和华啊,

我要在列邦中赞美你,

歌颂你的名。

51你使你立的王大获全胜,

向你膏立的王,

就是大卫和他的后代广施慈爱,

直到永远。”