2 ሳሙኤል 11 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

2 ሳሙኤል 11:1-27

ዳዊትና ቤርሳቤህ

1ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት፣ በጸደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን ከንጉሡ ሰዎችና ከመላው የእስራኤል ሰራዊት ጋር አዘመተው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ረባት የተባለችውንም ከተማ ከበቡ፤ በዚህ ጊዜ ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።

2አንድ ቀን ማታ፣ ዳዊት ከዐልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፣ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ በጣም ውብ ነበረች። 3ዳዊትም ሰው ልኮ ስለ ሴቲቱ አጠያየቀ። ሰውየውም፣ “ይህች የኤልያብ ልጅ፣ የኬጢያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን?” አለ። 4ከዚያም ዳዊት መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፤ እርሱ ወዳለበት ገባች፤ አብሯትም ተኛ። በዚህም ጊዜ ወርኃዊ የመንጻት ጊዜዋን ፈጽማ ነበር። ከዚያም ተመልሳ ወደ ቤቷ ሄደች። 5ሴቲቱ ፀነሰች፤ ለዳዊትም፣ “አርግዣለሁ” ብላ ላከችበት።

6ስለዚህም ዳዊት ለኢዮአብ፣ “ኬጢያዊውን ኦርዮን ወደ እኔ ስደደው” ሲል ላከበት፤ ኢዮአብም ወደ ዳዊት ላከው። 7ኦርዮን በመጣ ጊዜም፣ ዳዊት የኢዮአብንና የሰራዊቱን ሁሉ ደኅንነት እንዲሁም ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንዳለ ጠየቀው። 8ከዚያም ዳዊት ኦርዮን፣ “በል እንግዲህ ወደ ቤትህ ወርደህ እግርህን ታጠብ” አለው። ኦርዮን ከቤተ መንግሥት ተሰናብቶ ወጣ፤ ንጉሡም ማለፊያ ምግብ አስከትሎ ላከለት። 9ነገር ግን ኦርዮ ከጌታው አገልጋዮች ሁሉ ጋር በቤተ መንግሥቱ ቅጽር በር ተኛ እንጂ፣ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር።

10ዳዊት፣ “ኦርዮን ወደ ቤቱ አልሄደም” መባሉን ሲሰማ ኦርዮን፣ “ከመንገድ ገና አሁን መግባትህ አይደለምን? ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

11ኦርዮም ዳዊትን፣ “ታቦቱ፣ እስራኤልና ይሁዳ በድንኳን ሆነው፣ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ሰዎች አውላላ ሜዳ ላይ ሰፍረው፣ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋር ለመተኛት እንዴት ወደ ቤቴ እሄዳለሁ? እንዲህ ያለውን ነገር እንደማላደርገው በነፍስህ እምላለሁ” አለው።

12ከዚያም ዳዊት፣ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ ዕደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮን በዚያ ዕለትና በማግስቱም እዚያው ኢየሩሳሌም ቈየ። 13በማግስቱም ዳዊት ራሱ ባለበት ግብዣ አድርጎለት በላ፤ ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ሲመሽም ኦርዮን በምንጣፉ ላይ ለመተኛት የጌታው አሽከሮች ወዳሉበት ወጥቶ ሄደ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም።

14ሲነጋም ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጽፎ በኦርዮን እጅ ላከለት፤ 15በደብዳቤውም ላይ፣ “ኦርዮ ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም ተወግቶ እንዲሞት ትታችሁት ሽሹ” ብሎ ጻፈ።

16ስለዚህም ኢዮአብ ከተማዪቱን በከበባት ጊዜ፣ እጅግ ጠንካራ ተከላካዮች እንዳሉበት በሚያውቀው ግንባር ኦርዮን መደበው። 17የከተማዪቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ከዳዊት ሰራዊት ውስጥ ጥቂቶቹ ወደቁ፤ እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ።

18ኢዮአብም በጦርነቱ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት ላከ። 19መልእክተኛውንም እንዲህ አለው፤ “ይህን የጦርነቱን ወሬ ለንጉሡ ከነገርኸው በኋላ፣ 20ንጉሡ በቍጣ ቱግ ብሎ ‘ለመዋጋት ስትሉ ይህን ያህል ወደ ከተማዪቱ የተጠጋችሁት ስለ ምንድን ነው? ከግንቡ ቅጥር በላይ ፍላጻ እንደሚሰድዱባችሁ አታውቁም ኖሯል? 21የይሩቤሼትን11፥21 ጌዴዎን፣ ይሩበአል በመባልም ይታወቃል። ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቅቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በማለት ቢጠይቅህ፣ አንተም መልሰህ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”

22ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ሄደ፤ እዚያ እንደ ደረሰም፣ ከኢዮአብ የተቀበለውን መልእክት በሙሉ ለዳዊት ነገረው። 23መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ ዐየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወጥተው እስከ ሜዳው ድረስ መጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማዪቱ ቅጽር መግቢያ ድረስ አሳድደን መለስናቸው። 24ከዚያም ባለ ፍላጻዎቹ ከግንቡ ላይ ሆነው በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ ቀስት ስለ ለቀቁ፣ ከንጉሡ አገልጋዮች ጥቂቶቹን ገደሉ፤ አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ።”

25ዳዊትም፣ መልእክተኛውን፣ “እንግዲህ እንዲህ ብለህ ይህን ለኢዮአብ ንገረው፤ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፣ ሌላ ጊዜም ሌላውን ትበላለችና በዚህ አትዘን’ ” አለው።

26የኦርዮን ሚስት ባሏ መሞቱን በሰማች ጊዜ ዐዘነች፤ አለቀሰችለትም። 27የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፣ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ እግዚአብሔርን አላስደሰተውም ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

撒母耳记下 11:1-27

大卫犯罪

1第二年春天,诸王又要发动战争。大卫差遣约押率领众将领和以色列大军出征,自己却留在耶路撒冷。他们打败了亚扪人之后又围攻拉巴2一天黄昏,大卫从床上起来在王宫顶上散步,看见一个长得非常漂亮的女人在沐浴。 3大卫就派人去打听这个女人是谁,得知她是以连的女儿、乌利亚的妻子拔示芭4大卫差人把她接来,她来了,大卫就与她同寝,那时她的月经刚洁净。事后,她便回家去了。 5拔示芭怀孕了,就派人去告诉大卫

6大卫便传信给约押,说:“你派乌利亚来见我。”约押就派乌利亚去见大卫7乌利亚来了,大卫问他有关约押、士兵和战争的情况, 8然后吩咐他回家休息。乌利亚离开王宫后,收到大卫送的一份礼物。 9但他跟王的其他仆人一同睡在王宫门口,没有回家。 10大卫得知乌利亚没有回家,便对他说:“你远道而来,为什么不回家休息呢?” 11乌利亚答道:“约柜、以色列人和犹大人都在帐篷里,而我主约押及其军队也在田间扎营,我怎么可以回家吃喝快乐,与妻子同房呢?我敢在王面前起誓,我决不做这样的事!” 12大卫乌利亚说:“你再住一天,明天我会派你回去。”于是乌利亚那日就留在耶路撒冷13第二天,大卫邀请他一同吃饭,把他灌醉了。可是到了晚上,乌利亚还是不肯回家,仍然跟王的其他士兵一同住宿。

14第二天早上,大卫约押写了一封信,要乌利亚带去。 15大卫在信上吩咐约押:“你把乌利亚派到前线最险恶的地方,到时其他人都要撤退,好让敌人杀死他。” 16于是约押围攻城池时,便派乌利亚到最强悍的敌人那里。 17敌人出来迎战,大卫的军中有几位阵亡,乌利亚也死了。 18约押就派人去向大卫禀告战争的详情, 19并叮嘱信使:“你向王禀告战情后, 20他若发怒责问你,‘为什么还冒死逼近呢?你们难道不知道敌人会从城墙上射箭吗? 21难道你们不知道耶路·比设11:21 耶路·比设”又名“耶路·巴力”,参见士师记6:32的儿子亚比米勒是谁杀的吗?一个妇人从城墙上扔下一块磨石,把他砸死在提备斯。你们为什么还要逼近城墙呢?’你就对王说,‘你的仆人乌利亚也死了。’”

22于是,信使前来见大卫,照约押的吩咐向大卫禀告。 23他说:“敌军势力强大,在城外跟我们交战,但我们把他们追到城门口。 24敌军的弓箭手从城墙上射死了王的几个士兵,乌利亚也死了。” 25大卫便对信使说:“你去告诉约押不要为这事难过,因为刀剑无情。让他只管竭力攻陷城池。要这样勉励约押。”

26拔示芭听到丈夫乌利亚的死讯之后就为他守丧。 27守丧结束后,大卫便派人把她接进宫里,她就做了大卫的妻子,并给他生了个儿子。然而,大卫的所作所为令耶和华十分不悦。