1 ጢሞቴዎስ 6 – NASV & HHH

New Amharic Standard Version

1 ጢሞቴዎስ 6:1-21

1የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱም እንዳይሰደቡ፣ በባርነት ቀንበር ሥር ያሉ ሁሉ፣ ጌቶቻቸው ሙሉ ክብር እንደሚገባቸው አድርገው ይቍጠሩ። 2የሚያምኑ ጌቶች ያሏቸውም፣ ወንድሞች ስለ ሆኑ የሚገባቸውን ክብር አይንፈጓቸው፤ ይልቁንም በአገልግሎታቸው የሚጠቀሙ አማኞችና ወዳጆቻቸው ስለ ሆኑ የበለጠ ሊያገለግሏቸው ይገባል። እነዚህን ነገሮች አስተምር፤ ምከርም።

የገንዘብ ፍቅር

3ማንም የሐሰት ትምህርት ቢያስተምር፣ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጤናማ ቃልና እውነተኛ መንፈሳዊነትን ከሚያጐለብት ትምህርት ጋር የማይስማማ ቢሆን፣ 4ያ ሰው በትዕቢት ተወጥሯል፤ አንዳችም አያስተውልም። ስለ ቃላት ለመከራከርና ለመጣላት ክፉ ጕጕት አለው፤ እነዚህም ቅናትን፣ ጥልን፣ ስድብን፣ መጥፎ ጥርጣሬን ያስከትላሉ፤ 5እውነትን በተቀሙና መንፈሳዊው ነገር ትርፍ ማግኛ በሚመስላቸው፣ አእምሮ በጐደላቸው ሰዎችም መካከል የማያባራ ንትርክ ያመጣሉ።

6ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋር ትልቅ ትርፍ ነው። 7ምክንያቱም ወደ ዓለም ያመጣነው ምንም ነገር የለም፤ ምንም ነገር ይዘን መሄድም አንችልም። 8ነገር ግን ምግብና ልብስ ካለን፣ ያ ይበቃናል። 9ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ ግን ወደ ፈተናና ወደ ወጥመድ፣ እንዲሁም ሰዎችን ወደ መፍረስና ወደ ጥፋት ወደሚያዘቅጠው ወደ ብዙ ከንቱና ክፉ ምኞት ይወድቃሉ። 10ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው። አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጕጕት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።

ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የሰጠው ዐደራ

11የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል። 12መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ። 13ለሁሉም ሕይወትን በሚሰጥ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁም በጳንጥዮስ ጲላጦስ ፊት እውነትን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት ዐደራ የምልህ፣ 14ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ይህን ትእዛዝ ያለ ዕድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ እንድትጠብቅ ነው፤ 15ያም መገለጥ፣ የተባረከውና ብቻውን ገዥ የሆነው የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ የሚያሳየው ነው፤ 16እርሱ ብቻ ኢመዋቲ ነው፤ ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እርሱን ያየ ማንም የለም፤ ሊያየውም የሚችል የለም። ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤ አሜን።

17በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። 18መልካም እንዲሠሩ፣ ቸሮችና ለማካፈል ፈቃደኞች የሆኑ እንዲሆኑ እዘዛቸው። 19በዚህ ዐይነት እውነተኛ የሆነውን ሕይወት ያገኙ ዘንድ፣ ለሚመጣው ዘመን ጽኑ መሠረት የሚሆን ሀብት ለራሳቸው ያከማቻሉ።

20ጢሞቴዎስ ሆይ፤ በዐደራ የተቀበልኸውን ሁሉ ጠብቅ፤ እግዚአብሔርን ከማያስከብር ከከንቱ ልፍለፋና ለተቃውሞ በውሸት ዕውቀት ከተባለ ፍልስፍና ራቅ፤ 21የዚህ ዐይነት ዕውቀት አለን ሲሉ የነበሩ አንዳንዶች ይህን በማድረጋቸው ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል።

ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

Habrit Hakhadasha/Haderekh

אגרת פולוס הראשונה אל-טימותיוס 6:1-21

1על מאמינים שהם עבדים לעבוד קשה למען אדוניהם ולכבד אותם, כדי שישמשו דוגמה לחריצות, ולא יחללו את שם האלוהים ואת האמונה. 2אם אדונם הוא מאמין משיחי, אין זו סיבה להתעצל בעבודה, אלא להיפך – עליהם לעבוד בחריצות כפולה, שכן הם עוזרים לאח מאמין ואהוב.

טימותיוס, למד אותם דברים אלה ועודד את כולם לקיימם. 3כל מי שילמד אתכם תורה אחרת, ויתכחש לדברי אדוננו ישוע המשיח ולתורתו הבריאה והקדושה, 4הוא טיפש וגאה. לאדם כזה יש נטייה חולנית להתפלפל בשאלות האמונה, ולעורר ויכוחי סרק הגורמים לקנאה, למריבות, לגידופים ולחשדות. 5אנשים כאלה הם חוטאים ורעים, מחוסרי אמונה שמעוררים ויכוחי סרק ומתייחסים אל הקדושה כאל אמצעי להתעשר. התרחקו מאנשים כאלה! 6אתה באמת רוצה להתעשר? אם אתה חי ביושר ושמח בחלקך, אתה כבר עשיר! 7הלא באנו לעולם בחוסר־כל, ואף כשנמות לא נוכל לקחת איתנו דבר. 8משום כך, אם יש לנו אוכל ולבוש עלינו להסתפק ולשמוח בחלקנו. 9אנשים שמשתוקקים להתעשר סוטים עד־מהרה מהדרך הישרה, ומשתמשים באמצעים לא־כשרים להשגת כסף. מעשים אלה מזיקים להם, משחיתים אותם ולבסוף שולחים אותם לגיהינום. 10כי אהבת הכסף היא שורש כל המעשים הרעים. אנשים רבים שלהוטים אחרי הכסף נטשו את האמונה, ובכך גרמו לעצמם צער וכאב.

11אולם אתה, טימותיוס, הינך איש אלוהים. ברח מכל הדברים האלה ועשה מעשים טובים; למד לבטוח באדוננו, לאהוב את הזולת ולהתייחס לכולם בסבלנות ובעדינות. 12המשך להילחם למען אלוהים. אחוז היטב במתנת חיי־הנצח שהעניק לך אלוהים, ושעליהם סיפרת לאנשים רבים כל־כך.

13אני מצווה עליך לפני האלוהים, שמעניק חיים לכל, ולפני ישוע המשיח, שללא פחד אמר את האמת לפונטיוס פילטוס: 14עליך לקיים את המצווה הזאת ללא כל דופי, עד בואו של ישוע המשיח אדוננו. 15וכשיגיע הזמן המתאים יתגלה המשיח אלינו מהשמים, על־ידי האלוהים המבורך והעליון, מלך המלכים ואדון האדונים; 16הוא לבדו בן־אלמוות, וחי באור נשגב שאיש אינו יכול לחזות בו. כל הכבוד, התפארת והגבורה לאלוהינו לעולמים. – אמן.

17אמור לעשירים שלא יתגאו ושלא יסמכו על עושרם אשר ייעלם בקרוב, אלא שיבטחו באלוהים חיים שמעניק לנו תמיד ברוחב לב כל מה שאנחנו צריכים. 18עודד אותם לעשות מעשים טובים, להעניק מכספם לנזקקים, ולשתף את האחרים בכל מה שהעניק להם אלוהים. 19אם כך ינהגו, הם יאגרו לעצמם אוצר אמיתי בשמים אשר יישמר לנצח, וגם יחיו חיים משיחיים פוריים כאן עלי אדמות.

20טימותיוס, שמור היטב את מה שאלוהים הפקיד בידך. התרחק מוויכוחי סרק עם אלה שמתפארים שהם יודעים הכול, ובכך מוכיחים את בורותם.

21רבים מאלה החטיאו את העיקר – את האמונה בישוע המשיח!

חסדו של אלוהים איתך. – אמן.