1 ጢሞቴዎስ 5 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

1 ጢሞቴዎስ 5:1-25

ስለ መበለቶች፣ ስለ ሽማግሌዎችና ስለ ባሪያዎች የተሰጠ ምክር

1አረጋዊውን ሰው እንደ አባትህ ቈጥረህ ምከረው እንጂ በኀይለ ቃል አትናገረው። ወጣት ወንዶችን እንደ ወንድሞች ተቀበላቸው፤ 2እንዲሁም አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ወጣት ሴቶችን ደግሞ እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና አስተናግዳቸው።

3በርግጥ ችግረኛ የሆኑትን መበለቶች ተንከባከባቸው። 4አንዲት መበለት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሯት፣ እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ቤተ ሰብ በመርዳትና ለወላጆቻቸውም ብድራትን በመመለስ ከሁሉ በፊት እምነታቸውን በተግባር ለማሳየት መማር ይገባቸዋል፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነውና። 5በርግጥ መበለት የሆነች፣ ብቻዋንም የምትኖር ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ ታደርጋለች፤ ለጸሎትና የእግዚአብሔርን ርዳታ ለመለመን ሌሊትና ቀን ትተጋለች። 6ምድራዊ ደስታን የምትሻዋ መበለት ግን በሕይወት ብትኖርም የሞተች ናት። 7ማንም የሚነቀፍበት ነገር እንዳይኖር፣ ይህንም ትእዛዝ ለሕዝቡ ስጥ። 8አንድ ሰው ዘመዶቹን፣ በተለይም የቅርብ ቤተ ሰቡን የማይረዳ ከሆነ ሃይማኖቱን የካደ፣ ከማያምንም ሰው ይልቅ የባሰ ክፉ ነው።

9ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት ያነሰ መበለት በመዝገብ ላይ አትጻፍ፤ ደግሞም የአንድ ባል ሚስት የነበረች5፥9 ወይም ለባሏ ታማኝ የነበረች ልትሆን ይገባል፤ 10ልጆችን በማሳደግ፣ እንግዶችን በመቀበል፣ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ለበጎ ምግባር ሁሉ ራሷን በመስጠት በመልካም ሥራም የተመሰከረላት መሆን አለባት።

11ወጣት መበለቶችን ግን እንዲህ ባለው መዝገብ አትጻፋቸው፤ ምክንያቱም ሥጋዊ ፍላጎታቸው ለክርስቶስ በገቡት ቃል ላይ በሚያይልበት ጊዜ ለማግባት ይሻሉና። 12በዚህም ፍርድን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ፤ በመጀመሪያ የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና። 13በተጨማሪም ሥራ መፍታትንና ከቤት ቤት መዞርን ይለምዳሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን፣ የማይገባውን እየተናገሩ ሐሜተኞችና በሰው ጕዳይም ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ። 14ስለዚህ ባል የሞተባቸው ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ፣ ልጆች እንዲወልዱ፣ ቤታቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ጠላትም የሚነቅፍባቸውን ነገር እንዳያገኝ እመክራለሁ። 15በርግጥ ከዚህ በፊት አንዳንዶቹ ሰይጣንን ለመከተል ዘወር ብለዋል።

16አማኝ የሆነች ማንኛዋም ሴት በቤተ ሰቧ ውስጥ መበለቶች ቢኖሯት፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ መበለቶችን ብቻ መርዳት እንድትችል እርሷው ትርዳቸው እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሸክም እንዲሆኑ አትተዋቸው።

17ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ የሚያስተዳድሩ፣ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚተጉ ሽማግሌዎች ዕጥፍ ክብር ይገባቸዋል፤ 18መጽሐፍም፣ “እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር፤5፥18 ዘዳ 25፥4” ደግሞም፣ “ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል5፥18 ሉቃ 10፥7” ይላልና። 19በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ የሚቀርብ ክስ አትቀበል። 20ሌሎች አይተው እንዲጠነቀቁ ኀጢአት የሚሠሩትን በጉባኤ ፊት ገሥጻቸው።

21በእግዚአብሔርና በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በተመረጡትም መላእክት ፊት እነዚህን ትእዛዞች ያለ አድልዎ እንድትጠብቅና አንዳችም ነገር በማበላለጥ እንዳታደርግ ዐደራ እልሃለሁ።

22በማንም ላይ እጅ ለመጫን አትቸኵል፤ ከሌሎችም ጋር በኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ።

23ለሆድህና ደጋግሞ ለሚነሣብህ ሕመም፣ ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣበት እንጂ ከእንግዲህ ውሃ ብቻ አትጠጣ።

24የአንዳንድ ሰዎች ኀጢአት ግልጽ ነው፤ ከእነርሱም ቀድሞ ፍርድ ቦታ ይደርሳል፤ ሌሎችን ግን ኀጢአታቸው ይከተላቸዋል። 25መልካም ሥራም እንደዚሁ ግልጽ ነው፤ ግልጽ ያልሆነ ቢኖርም እንኳ ተሰውሮ አይቀርም።

Thai New Contemporary Bible

1ทิโมธี 5:1-25

คำแนะนำเกี่ยวกับแม่ม่าย ผู้อาวุโส และทาส

1อย่าตำหนิผู้อาวุโสอย่างรุนแรง แต่จงขอร้องเขาเสมือนว่าเป็นบิดาของท่าน จงปฏิบัติต่อชายหนุ่มที่อ่อนวัยกว่าเสมือนเป็นน้องชาย 2ต่อหญิงที่สูงวัยเสมือนเป็นมารดา และต่อหญิงสาวที่อ่อนวัยกว่าเสมือนเป็นน้องสาวด้วยความบริสุทธิ์อย่างแท้จริง

3จงนับถือเอาใจใส่หญิงม่ายผู้ขัดสนตามสมควร 4แต่ถ้าหญิงม่ายคนใดมีลูกหลาน ก่อนอื่นใดให้ลูกหลานเหล่านั้นพึงปฏิบัติตามหลักธรรมของศาสนา โดยการเอาใจใส่ดูแลครอบครัวของตนเองอันเป็นการตอบแทนคุณบิดามารดาปู่ย่าตายาย เพราะการทำเช่นนี้เป็นที่พอพระทัยพระเจ้า 5หญิงม่ายผู้ขัดสนจริงๆ และอยู่ลำพังคนเดียวนั้นก็ตั้งความหวังไว้ในพระเจ้า นางพร่ำอธิษฐานและทูลขอพระเจ้าทั้งวันทั้งคืนให้ทรงช่วยเหลือ 6แต่หญิงม่ายที่อยู่เพื่อหาความสนุกเพลิดเพลินก็ตายทั้งเป็น 7จงสั่งสอนสิ่งเหล่านี้ด้วยเพื่อจะไม่มีใครถูกตำหนิได้ 8ถ้าผู้ใดไม่จุนเจือญาติพี่น้องของตนโดยเฉพาะคนในครอบครัวของตนเอง ผู้นั้นก็ได้ปฏิเสธความเชื่อแล้วและเลวยิ่งกว่าผู้ไม่เชื่อ

9อย่าบันทึกชื่อหญิงม่ายคนใดในทะเบียนรับการอุปถัมภ์5:9 หรือทะเบียนแม่ม่าย เว้นแต่นางจะมีอายุเกินหกสิบปีและสัตย์ซื่อต่อสามีของนาง5:9 หรือมีสามีเพียงคนเดียว 10และเป็นผู้ที่มีชื่อเสียงในการทำความดีเช่น เลี้ยงดูลูกๆ มีน้ำใจรับรองแขก ล้างเท้าให้ประชากรของพระเจ้า ช่วยเหลือผู้ตกทุกข์ได้ยากและอุทิศตนในการทำดีทุกอย่าง

11ส่วนหญิงม่ายสาวๆ นั้น อย่ารับขึ้นทะเบียน เพราะเมื่อความปรารถนาทางร่างกายมีชัยเหนือการอุทิศตัวแด่พระคริสต์ พวกนางก็อยากแต่งงานอีก 12อันเป็นเหตุให้นางถูกพิพากษาเพราะละเมิดคำปฏิญาณที่ให้ไว้แต่แรก 13นอกจากนี้พวกนางจะกลายเป็นคนเกียจคร้านเที่ยวไปบ้านนั้นบ้านนี้ และไม่เพียงเกียจคร้านเท่านั้นแต่ยังชอบซุบซิบนินทาและยุ่งเรื่องชาวบ้าน พูดสิ่งที่ไม่ควรพูด 14ดังนั้นข้าพเจ้าจึงขอแนะนำหญิงม่ายสาวๆ ให้แต่งงาน ให้มีลูกหลาน ให้ดูแลบ้านช่องเพื่อปิดโอกาสไม่ให้ศัตรูว่าร้ายได้ 15อันที่จริงบางคนได้เตลิดตามซาตานไปแล้ว

16ถ้าหญิงผู้เชื่อคนใดมีคนในครอบครัวเป็นม่ายก็จงช่วยเหลือจุนเจือ อย่าปล่อยให้เป็นภาระของคริสตจักร คริสตจักรจะได้ช่วยเหลือหญิงม่ายอื่นๆ ซึ่งขัดสนจริงๆ

17คณะผู้ปกครองที่บริหารกิจการของคริสตจักรได้ดีควรได้รับเกียรติเป็นสองเท่า โดยเฉพาะบรรดาผู้ทำหน้าที่เทศนาและสั่งสอน 18เพราะพระคัมภีร์กล่าวว่า “อย่าเอาตะกร้อครอบปากวัวซึ่งนวดข้าวอยู่”5:18 ฉธบ.25:4 และ “คนงานสมควรได้รับค่าจ้างของตน”5:18 ลก.10:7 19อย่ารับพิจารณาคำกล่าวหาผู้ปกครองคนใดเว้นแต่จะมีพยานสองสามคน 20จงว่ากล่าวตักเตือนผู้ที่ทำบาปต่อหน้าคนทั้งหลายเพื่อคนอื่นๆ จะได้ไม่กล้าเอาอย่าง

21ข้าพเจ้าขอกำชับท่านในสายพระเนตรพระเจ้าและพระเยซูคริสต์และต่อหน้าเหล่าทูตสวรรค์ที่ทรงเลือก ให้ยึดถือข้อปฏิบัติเหล่านี้โดยไม่ลำเอียงและอย่าทำสิ่งใดโดยเลือกที่รักมักที่ชัง

22อย่าผลีผลามวางมือให้ใครและอย่ามีส่วนร่วมในบาปของผู้อื่น จงรักษาตัวให้บริสุทธิ์

23ตั้งแต่นี้ไปอย่าดื่มแต่น้ำ จงเจือเหล้าองุ่นเล็กน้อย เนื่องด้วยกระเพาะอาหารของท่านและความเจ็บป่วยที่ท่านเป็นอยู่บ่อยๆ

24บาปของบางคนก็ชัดแจ้งนำหน้าเขาไปสู่สถานพิพากษา ส่วนบาปของบางคนตามเขามาในภายหลัง 25ในทำนองเดียวกันการทำดีย่อมปรากฏชัด แม้ที่ไม่ปรากฏชัดก็ไม่อาจซ่อนได้