1 ጢሞቴዎስ 4 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

1 ጢሞቴዎስ 4:1-16

ለጢሞቴዎስ የተሰጠ መመሪያ

1በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጽ ይናገራል። 2እንዲህ ያለው ትምህርት የሚመጣው ኅሊናቸው በጋለ ብረት የተጠበሰ ያህል ከደነዘዘባቸው ግብዝ ውሸተኞች ነው። 3እነርሱ፣ ሰዎች እንዳያገቡ ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎች እግዚአብሔር የፈጠረውን፣ በምስጋናም የሚቀበሉትን እንዳይበሉ ያዝዛሉ። 4እግዚአብሔር የፈጠረው ማንኛውም ነገር መልካም ነውና፤ በምስጋና ከተቀበሉትም የሚጣል ምንም ነገር የለም፣ 5በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነውና።

6ይህን ትእዛዝ ለወንድሞች ብታሳስብ፣ በእምነት ቃልና በተቀበልኸው መልካም ትምህርት ታንጸህ የክርስቶስ ኢየሱስ በጎ አገልጋይ ትሆናለህ። 7እግዚአብሔርን ከማያከብር ርባና ቢስ አፈ ታሪክና ከአሮጊቶች ተረታ ተረት ራቅ፤ ይልቁንም ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስህን አሠልጥን። 8የአካል ብቃት ልምምድ ለጥቂት ነገር ይጠቅማልና፤ ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስን ማሠልጠን ግን ለአሁኑም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁለቱም ይጠቅማል።

9ይህ ቃል የታመነና ሙሉ ለሙሉ ሊቀበሉት የሚገባ ነው። 10ለዚህ ብለን እንጥራለን፤ እንደክማለንም፤ ይኸውም ለሰዎች ሁሉ፣ በተለይም ለሚያምኑት አዳኝ በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ተስፋ ስለምናደርግ ነው።

11እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም። 12ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው። 13እኔ እስክመጣ ድረስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሕዝብ ለማንበብ፣ ለመምከርና ለማስተማር ትጋ። 14ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ ሲጭኑ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

15ሰው ሁሉ ማደግህን ያይ ዘንድ በእነዚህ ነገሮች ላይ አትኵር፤ በትጋትም ፈጽማቸው። 16ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

提摩太前書 4:1-16

謹防偽君子

1聖靈明確地說,日後必有人離棄真道,去追隨那些迷惑人的邪靈和鬼魔的學說。 2這些學說是出自假冒偽善的騙子,他們良心喪盡,麻木不仁4·2 良心喪盡,麻木不仁」希臘文是「良心被烙鐵燙過」。3禁止人結婚和吃某些食物。其實那些食物是上帝創造的,為了讓相信並且明白真理的人存感恩的心領受。 4上帝所造的一切都是美好的,若以感恩的心去領受,就無需任何禁忌, 5因為上帝的道和人的禱告可以使食物聖潔。

6你要提醒弟兄姊妹這些事,這樣你就是基督耶穌的好僕人,會不斷地從你所信的真道和所遵行的美好教導上得到造就。

做信徒的榜樣

7但你要棄絕世俗、荒誕的傳說,要訓練自己做個敬虔的人。 8鍛煉體魄益處還少,敬虔生活受益無窮,擁有今生和永世的應許。 9這話真實可信,值得完全接受。 10我們努力奮鬥正是為了這個目的,因為我們的盼望在於永活的上帝。祂是全人類的救主,更是信徒的救主。 11你要吩咐和教導這些事。

12不要因為年輕而叫人小看你,總要在言語、行為、愛心、信心和純潔各方面做信徒的榜樣。 13在我來之前,你要專心宣讀聖經,勉勵會眾,教導真理。 14不要忽略你的恩賜,那是藉著預言在眾長老把手按在你身上時賜給你的。 15你要全心全意地做這些事,讓大家都看到你的長進。 16你要注意自己的言行和教導,要持之以恆。這樣,你不但能救自己,也能救那些聽你教導的人。