1 ጢሞቴዎስ 3 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

1 ጢሞቴዎስ 3:1-16

እረኞችና ዲያቆናት

1“ማንም ኤጲስቆጶስነትን3፥1 ወይም ተመልካች፣ ጠባቂዎች ቢፈልግ፣ መልካም ሥራን ይመኛል” የሚለው ቃል የታመነ ነው። 2እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ኤጲስቆጶስ የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ ልከኛ፣ ራሱን የሚገዛ፣ በሥርዐት የሚኖር፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ማስተማር የሚችል፣ 3የማይሰክር፣ የማይጣላ ግን ጨዋ የሆነ፣ የማይጨቃጨቅ፣ ገንዘብንም የማይወድ ሊሆን ይገባዋል። 4ልጆቹን ታዛዥና አክባሪ አድርጎ በማሳደግ የገዛ ቤተ ሰቡን በአግባቡ የሚያስተዳድር ሊሆን ይገባል። 5አንድ ሰው የራሱን ቤት ማስተዳደር ካላወቀበት፣ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊጠብቅ ይችላል? 6በትዕቢት ተነፍቶ ዲያብሎስ በወደቀበት ፍርድ እንዳይወድቅ አዲስ ክርስቲያን አይሁን። 7ደግሞም ስሙ እንዳይነቀፍና በዲያብሎስ ወጥመድ ውስጥ እንዳይወድቅ፣ በውጭ ባሉት ዘንድ መልካም ምስክርነት ሊኖረው ይገባል።

8ዲያቆናትም እንደዚሁ የተከበሩ፣ ቃላቸውን የማይለዋውጡ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጐመጁ፣ ያለ አግባብ የሚገኝ ጥቅምንም የማያሳድዱ ሰዎች መሆን ይገባቸዋል፤ 9የእምነትንም ጥልቅ ምስጢር በንጹሕ ኅሊና መጠበቅ አለባቸው። 10እነርሱም አስቀድመው ይፈተኑ፤ ከዚያም፣ አንዳች ነቀፋ ካልተገኘባቸው በዲቁና ያገልግሉ።

11እንዲሁ ሴቶችም3፥11 ወይም ሚስቶቻቸው ወይም ዲያቆናውያት የተከበሩ፣ ሐሜተኞች ያልሆኑ ነገር ግን ልከኞችና በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባል።

12ዲያቆናት የአንዲት ሚስት ባል መሆን ይገባቸዋል፤ ደግሞም ልጆቻቸውንና ቤተ ሰቦቻቸውን በአግባቡ የሚያስተዳድሩ መሆን አለባቸው። 13በአግባቡ ያገለገሉ ለራሳቸው ትልቅ ክብርን፣ በክርስቶስ ኢየሱስም ባላቸው እምነት ብዙ ድፍረትን ያገኛሉ።

14ወደ አንተ ቶሎ ለመምጣት ተስፋ ባደርግም ይህን ትእዛዝ እጽፍልሃለሁ፤ 15ይህንም የምጽፍልህ ብዘገይ እንኳ ሰዎች በእግዚአብሔር ቤት እንዴት መኖር እንዳለባቸው እንድታውቅ ነው፤ ቤቱም የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፣ ይኸውም የእውነት ዐምድና መሠረት ነው። 16የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤

እርሱ3፥16 አንዳንድ ቅጆች አምላክ ይላሉ። በሥጋ3፥16 ወይም በአካል ተገለጠ፤

በመንፈስ ጸደቀ፤

በመላእክት ታየ፤

በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤

በዓለም ባሉት ታመነ፤

በክብር ዐረገ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

提摩太前書 3:1-16

監督與執事的資格

1「人若渴望做教會的監督,他是在愛慕尊貴的工作。」這句話千真萬確。 2作監督的人必須無可指責,只有一位妻子,為人節制自律、通情達理、受人尊敬、樂於接待客旅、善於教導, 3不酗酒、不好鬥、要溫和、不爭吵、不貪財, 4善於管理自己的家,受兒女的敬重和孝順。 5一個人要是不懂得管理自己的家,又怎能照顧上帝的教會呢? 6初信主的人不可作監督,免得他自高自大,遭受魔鬼所受的懲罰。 7作監督的在教會以外也必須有好名聲,以免被人指責,陷入魔鬼的圈套。

8同樣,做執事的也要品行端正,說話誠實,不好酒,不貪財, 9要存著清潔的良心持守奧妙的真道。 10他們要先接受考驗,倘若無可指責,就可以立他們為執事。 11執事的妻子3·11 執事的妻子」或譯「女執事」。也要品行端正,不搬弄是非,為人節制,做事忠心。 12執事只能有一位妻子,他要管好自己的兒女和自己的家。 13盡忠職守的執事能得到好聲譽,也會對基督耶穌有堅定的信心。

奧妙無比的信仰

14我希望能儘快去你那裡,但還是寫信告訴你這些事。 15這樣,如果我行期延誤,你也可以知道在上帝的家中該怎麼做。這家是永活上帝的教會,是真理的柱石和根基。 16毫無疑問,我們偉大的信仰奧妙無比:

祂以肉身顯現,

被聖靈證明為義,

被天使看見,

被傳揚到列邦,

被世人信奉,

被接到天上的榮耀中。