1 ጢሞቴዎስ 1 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

1 ጢሞቴዎስ 1:1-20

1በአዳኛችን በእግዚአብሔር፣ ተስፋችንም በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ትእዛዝ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤

2በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነው ለጢሞቴዎስ፤

ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት፣ ሰላምም ይሁን።

ከሐሰተኛ የሕግ መምህራን ስለ መጠበቅ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

3ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ ዐደራ እንዳልሁህ፣ አንዳንድ ሰዎች ከእንግዲህ የሐሰት ትምህርት እንዳያስተምሩ ታዝዛቸው ዘንድ በዚያው በኤፌሶን ተቀመጥ፤ 4ደግሞም ለተረትና መጨረሻ ለሌለው የትውልዶች ታሪክ ራሳቸውን አሳልፈው እንዳይሰጡ እዘዛቸው። እነዚህ ነገሮች በእምነት ከሆነው ከእግዚአብሔር ሥራ ይልቅ ክርክርን ያነሣሣሉ። 5የዚህ ትእዛዝ ዐላማ ግን ከንጹሕ ልብ፣ ከበጎ ኅሊና እንዲሁም ከእውነተኛ እምነት የሚገኝ ፍቅር ነው። 6አንዳንዶች ከእነዚህ ነገሮች ዘወር ብለው ወደ ከንቱ ንግግር ተመልሰዋል። 7የሕግ መምህራን ለመሆን ይፈልጋሉ፤ ሆኖም ስለሚናገሩት ወይም አስረግጠው ስለሚሟገቱለት ነገር አያውቁም።

8ነገር ግን ሰው በአግባቡ ከተጠቀመበት፣ ሕግ መልካም መሆኑን እናውቃለን። 9ደግሞም ሕግ1፥9 ወይም ሕጉ የተሰጠው ለጻድቃን ሳይሆን፣ ለሕግ ተላላፊዎችና ለዐመፀኞች፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ለሌላቸውና ለኀጢአተኞች፣ ቅድስና ለሌላቸውና እግዚአብሔርን ለሚንቁ፣ አባትና እናታቸውን ለሚገድሉ፣ ለነፍሰ ገዳዮች መሆኑን እናውቃለን፤ 10እንዲሁም ለዘማውያን፣ ከወንድ ጋር ለሚተኙ ወንዶች፣ ሰውን ለሚሸጡና ለሚገዙ፣ ለውሸተኞች፣ በሐሰት ለሚምሉ፣ ጤናማ የሆነውን ትምህርት ለሚፃረሩ ሁሉ ነው። 11ይህ ጤናማ ትምህርት ቡሩክ የሆነው እግዚአብሔር ለእኔ በዐደራ ከሰጠኝ የክብር ወንጌል ጋር የሚስማማ ነው።

ለጳውሎስ የተሰጠው የጌታ ጸጋ

12በአገልግሎቱ በመሾም ታማኝ አድርጎ የቈጠረኝን፣ ብርታትም የሰጠኝን ጌታችንን ክርስቶስ ኢየሱስን አመሰግናለሁ። 13ምንም እንኳ ከዚህ በፊት ተሳዳቢ፣ አሳዳጅና ዐመፀኛ የነበርሁ ብሆንም፣ ባለማወቅና ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረት ተደርጎልኛል፤ 14በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑት እምነትና ፍቅር ጋርም የጌታችን ጸጋ ተትረፈረፈልኝ።

15“ክርስቶስ ኢየሱስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ። 16ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለምን ሕይወት ለሚቀበሉ ወሰን የሌለው ትዕግሥቱን ከኀጢአተኞች ዋና በሆንሁት በእኔ እንደ ምሳሌ አድርጎ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ። 17እንግዲህ ዘላለማዊ ለሆነው፣ ለማይሞተው፣ ለማይታየውና ብቻውን አምላክ ለሆነው ንጉሥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብርና ምስጋና ይሁን፤ አሜን።

18ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ፤ አስቀድሞ ስለ አንተ በተነገረው ትንቢት መሠረት ይህን ትእዛዝ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም እርሱን በመከተል መልካሙን ገድል እንድትጋደል ነው። 19እምነትና በጎ ኅሊናም ይኑርህ፤ አንዳንዶች ኅሊናቸውን ጥለው ባሕር ላይ አደጋ ደርሶበት እንደሚጠፋ መርከብ እምነታቸውን አጥፍተዋል። 20ከእነርሱም መካከል እንዳይሳደቡ ትምህርት ያገኙ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ይገኛሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

提摩太前书 1:1-20

1保罗奉我们救主上帝和赐我们盼望的基督耶稣的命令,做基督耶稣的使徒, 2写信给因信主而做我真儿子的提摩太

愿父上帝和我们的主基督耶稣的恩典、怜悯和平安临到你!

谨防异端邪说

3我去马其顿的时候,曾经劝你继续留在以弗所,好命令那几个人不要传讲异端邪说, 4也不要沉迷于虚构的神话和冗长的家谱,因为这些事只会引起无用的猜测和辩论,无法帮助人凭信心认识上帝的救赎计划。 5制止这些人的目的是为了爱,这爱来自于清洁的心、无亏的良心和真实无伪的信心。 6可惜有些人却偏离这些,转向空洞的谈论。 7他们想做律法教师,却不明白自己所谈论所主张的。

8我们知道,只要用得合宜,律法本是好的。 9因为律法并不是为义人设的,而是为了对付那些目无法纪、大逆不道、不敬畏上帝、犯罪作恶、不圣洁、贪恋世俗、谋杀父母、行凶害命、 10淫乱、同性恋、拐卖人口、说谎、起假誓的人,以及其他违反正道的人。 11这正道来自当受称颂的上帝托付我传扬的荣耀福音。

感谢上帝的怜悯

12我感谢赐我力量的主基督耶稣,因为祂视我忠心可靠,派我事奉祂。 13尽管我从前是个亵渎上帝、迫害和侮辱信徒的人,但我仍然蒙了怜悯,因为那时我无知,还没有信耶稣。 14主赐给我丰富的恩典,使我在基督耶稣里有信心和爱心。

15有句话千真万确、完全可信,就是“基督耶稣降世,为要拯救罪人。”在罪人中我是个罪魁, 16但我依然蒙了怜悯,因为耶稣基督要在我这个罪魁身上彰显祂无限的忍耐,使我做那些要信靠祂并得到永生之人的榜样。

17愿尊贵、荣耀归给那位不朽的、肉眼不能见的万世君王——独一无二的上帝,直到永远。阿们!

18我儿提摩太啊,我依照从前有关你的预言,把这命令托付给你,好使你借此打美好的仗。 19你要持守信心和无亏的良心。有些人丧掉良心,结果他们的信仰就像船触了礁, 20其中有许米乃亚历山大。我已经把他们交给撒旦,使他们受些教训,不敢再说亵渎的话。