1 ዜና መዋዕል 9 – NASV & CST

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 9:1-44

1እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቈጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ።

የኢየሩሳሌም ከተማ ሕዝብ

9፥1-17 ተጓ ምብ – ነህ 11፥3-19

የይሁዳ ሕዝብ ከፈጸሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ። 2በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ የጕልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።

3በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣ የብንያም፣ የኤፍሬምና የምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤

4ከይሁዳ ልጅ፣ ከፋሬስ ዘሮች፣ የባኒ ልጅ፣ የአምሪ ልጅ፣ የዖምሪ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ።

5ከሴሎናውያን፦

የበኵር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ።

6ከዛራውያን፦

ይዑኤል፤

የሕዝቡ ቍጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበረ።

ከይሁዳ ነገድ የሰው ቍጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበር።

7ከብንያማውያን፦

የሐስኑአ ልጅ፣ የሆዳይዋ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ። 8የይሮሐም ልጅ ብኔያ፤ የሚክሪ ልጅ፣ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የይብንያ ልጅ፣ የራጉኤል ልጅ፣ የሰፋጥያ ልጅ ሜሱላም።

9በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቍጥር ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተ ሰብ አለቆች ነበሩ።

10ከካህናቱ፦

ዮዳኤ፣ ዮአሪብ፣ ያኪን፤

11የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።

12የመልክያ ልጅ፣ የጳስኮር ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ፣ የምሺላሚት ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የየሕዜራ ልጅ፣ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።

13የቤተ ሰብ አለቃ የነበሩት ካህናት ቍጥር አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ስድሳ ነበረ፤ እነዚህም በእግዚአብሔር ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።

14ከሌዋውያን ወገን፦

ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፣ 15በቅበቃር፣ ኤሬስ፣ ጋላልና የአሳፍ ልጅ፣ የዝክሪ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ።

16የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሰሙስ ልጅ አብድያ። እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቃና ልጅ፣ የአሳ ልጅ በራክያ።

17የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች፦

ሰሎም፣ ዓቁብ፣ ጤልሞን፣ አሒማንና ወንድሞቻቸው፤ አለቃቸውም ሰሎም ነበረ፤ 18እርሱም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በንጉሡ በር እስካሁን ድረስ ተመድቧል። እነዚህም የሌዋውያኑ ሰፈር በር ጠባቂዎች ነበሩ።

19የቆሬ ልጅ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ ሰሎምና ከእርሱም ቤተ ሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ9፥19 በዚህ በቍጥር 21 እና 23 ላይ ቤተ መቅደሱን ያመለክታል። የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣ እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።

20በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።

21ወደ መገናኛው ድንኳን የሚያስገባውን በር የሚጠብቀው ደግሞ የሜሱላም ልጅ ዘካርያስ ነበረ።

22መግቢያ በሮቹን እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቧቸው ዳዊትና ባለ ራእዩ ሳሙኤል ነበሩ። 23የማደሪያውን ድንኳን፣ ማለትም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠብቁትም እነርሱና ዘሮቻቸው ነበሩ። 24በር ጠባቂዎቹም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና፣ በደቡብ በሚገኙት በአራቱም ማእዘኖች ላይ ነበሩ። 25ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዟቸው ነበር። 26ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር። 27የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እነርሱ በመሆናቸው የሚያድሩትም በዚያው በእግዚአብሔር ቤት አካባቢ ነበረ፤ ጧት ጧትም ደጆቹን የሚከፍቱት እነርሱ ነበሩ።

28ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ይቈጥሩ ነበር። 29ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳት፣ ዱቄቱን፣ የወይን ጠጁን፣ የወይራ ዘይቱን፣ ዕጣኑን፣ የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር። 30ከካህናቱም አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅመማ ቅመም ይለውሱና ያዘጋጁ ነበር። 31የቆሬያዊው የሰሎም በኵር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቍርባኑን እንጀራ የመጋገር ኀላፊነት ተሰጥቶት ነበር። 32በየሰንበቱ ለሚዘጋጀው ገጸ ኅብስትም ኀላፊነቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።

33የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በቤተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።

34እነዚህ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣ በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት ተመዘገቡ፤ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።

የሳኦል ትውልድ ሐረግ

9፥34-44 ተጓ ምብ – 1ዜና 8፥28-38

35የገባዖን አባት9፥35 አባት ማለት፣ የማኅበረ ሰብ መሪ ወይም፣ የጦር መሪ ማለት ነው። ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤

የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል። 36የበኵር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ በኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣ 37ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩር፣ ሚቅሎት ነበሩ። 38ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።

39ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦል ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን9፥39 ኢሽጠቦሼት በመባልም ይታወቃል። ወለደ።

40የዮናታን ወንድ ልጅ፤

መሪበኣል9፥40 ሜፊቦስቴ በመባልም ይታወቃል። ነው፤ መሪበኣል ሚካን ወለደ።

41የሚካ ወንዶች ልጆች፤

ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።

42አካዝ የዕራን ወለደ፤ የዕራም ናሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ። 43ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁ ረፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤልዓሣ፣ ልጁ ኤሴል።

44ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦

ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሸዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን፤ እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።

Nueva Versión Internacional (Castilian)

1 Crónicas 9:1-44

1Todos los israelitas fueron registrados en las listas genealógicas e inscritos en el libro de los reyes de Israel.

Los que regresaron a Jerusalén

9:1-17Neh 11:3-19

Por causa de su infidelidad a Dios, Judá fue llevado cautivo a Babilonia.

2Los primeros en ocupar nuevamente sus posesiones y ciudades fueron israelitas, sacerdotes, levitas y servidores del templo. 3Algunos de los descendientes de Judá, Benjamín, Efraín y Manasés habitaron en Jerusalén.

4De los judíos: Utay hijo de Amiud, descendiente en línea directa de Omrí, Imrí, Baní y Fares hijo de Judá.

5De los silonitas: Asaías, el primogénito, con sus hijos.

6De los zeraítas: Jeuel y el resto de sus parientes; en total seiscientas noventa personas.

7De los benjaminitas: Salú hijo de Mesulán, hijo de Hodavías, hijo de Senuá;9:7 Senuá. Alt. Hasenuá. 8Ibneías hijo de Jeroán; Elá hijo de Uzi, hijo de Micri; Mesulán hijo de Sefatías, hijo de Reuel, hijo de Ibnías, 9con sus parientes. Según sus registros genealógicos, eran en total novecientos cincuenta y seis, todos ellos jefes de sus familias patriarcales.

10De los sacerdotes: Jedaías, Joyarib, Jaquín, 11Azarías hijo de Jilquías, que era descendiente en línea directa de Mesulán, Sadoc, Merayot y Ajitob, que fue jefe del templo de Dios; 12Adaías hijo de Jeroán, hijo de Pasur, hijo de Malquías; Masay hijo de Adiel, que era descendiente en línea directa de Jazera, Mesulán, Mesilemit e Imer, 13y sus parientes, en total mil setecientos sesenta jefes de familias patriarcales y hombres muy capacitados para el servicio en el templo de Dios.

14De los levitas: Semaías hijo de Jasub, que descendía en línea directa de Azricán, Jasabías y Merari; 15Bacbacar, Heres, Galal y Matanías hijo de Micaías, hijo de Zicrí, hijo de Asaf; 16Abdías hijo de Semaías, hijo de Galal, hijo de Jedutún; Berequías hijo de Asá, hijo de Elcaná, que habitó en las aldeas de los netofatitas.

17Los porteros: Salún, Acub, Talmón y Ajimán, y sus parientes; Salún era el jefe. 18Hasta ahora custodian la puerta del rey, que está al oriente, y han sido porteros de los campamentos levitas. 19Además, Salún hijo de Coré, hijo de Ebiasaf, hijo de Coré, y sus parientes coreítas de la misma familia patriarcal estaban encargados de custodiar la entrada de la Tienda de reunión, tal como sus antepasados habían custodiado la entrada del campamento del Señor. 20En el pasado, Finés hijo de Eleazar fue su jefe, y el Señor estuvo con él. 21Zacarías hijo de Meselemías era el portero de la Tienda de reunión.

22Los escogidos como porteros fueron un total de doscientos doce. En sus aldeas se encuentran sus registros genealógicos. David y Samuel el vidente les asignaron sus funciones. 23Los porteros y sus hijos estaban encargados de custodiar la entrada de la tienda de campaña que se usaba como templo del Señor. 24Había porteros en los cuatro puntos cardinales. 25Cada siete días, sus parientes que vivían en las aldeas se turnaban para ayudarlos. 26Los cuatro porteros principales estaban en servicio permanente. Eran levitas y custodiaban las salas y los tesoros del templo de Dios. 27Durante la noche montaban guardia alrededor del templo, y por la mañana abrían sus puertas.

28Algunos de ellos estaban encargados de los utensilios que se usaban en el servicio del templo, y debían contarlos al sacarlos y al guardarlos. 29Otros estaban a cargo de los utensilios, de todos los vasos sagrados, de la harina, el vino, el aceite, el incienso y los perfumes. 30Algunos de los sacerdotes preparaban la mezcla de los perfumes. 31El levita Matatías, primogénito del coreíta Salún, estaba encargado de hacer las tortas para las ofrendas. 32Algunos de sus parientes coatitas preparaban el pan consagrado para cada sábado.

33También había cantores que eran jefes de familias patriarcales de los levitas, los cuales vivían en las habitaciones del templo. Estos estaban exentos de cualquier otro servicio, porque de día y de noche tenían que ocuparse de su ministerio.

34Según sus registros genealógicos, estos eran jefes de las familias patriarcales de los levitas y vivían en Jerusalén.

Genealogía de Saúl

9:34-441Cr 8:28-38

35En Gabaón vivía Jehiel, padre de Gabaón. Su esposa se llamaba Macá, 36y sus hijos fueron Abdón, el primogénito; Zur, Quis, Baal, Ner, Nadab, 37Guedor, Ajío, Zacarías y Miclot, 38que fue padre de Simán. Estos también vivían en Jerusalén con sus parientes.

39Ner fue el padre de Quis, Quis lo fue de Saúl, y Saúl lo fue de Jonatán, Malquisúa, Abinadab y Esbaal. 40Jonatán fue el padre de Meribaal, y Meribaal lo fue de Micaías.

41Los hijos de Micaías fueron Pitón, Mélec, Tarea y Acaz.9:41 y Acaz (mss. de LXX, Siríaca, Targum y Vulgata; véase 8:35); TM no incluye esta frase. 42Acaz fue el padre de Jará, y este lo fue de Alemet, Azmávet y Zimri. Zimri fue el padre de Mosá; 43Mosá fue el padre de Biná, y este lo fue de Refaías; Refaías fue el padre de Elasá, y este lo fue de Azel.

44Azel tuvo seis hijos, cuyos nombres fueron Azricán, Bocrú, Ismael, Searías, Abdías y Janán. Estos fueron los hijos de Azel.