1 ዜና መዋዕል 29 – NASV & OL

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 29:1-30

ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የቀረቡ ስጦታዎች

1ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራው ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር አምላክ በመሆኑ፣ ሥራው ከባድ ነው። 2እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን፣ ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናሱ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ሥራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሚሆነውን መረግድ፣ ኬልቄዶን29፥2 የዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን የከበሩ ድንጋዮች፣ ማናቸውንም ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ። 3ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤ 4ይህም ሦስት ሺሕ መክሊት29፥4 100 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው የኦፊር ወርቅና ሰባት ሺሕ መክሊት29፥4 240 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው ንጹሕ ብር ለቤተ መቅደሱ የግድግዳ ግንብ ማስጌጫ 5እንዲሁም ለወርቁ ሥራ፣ ለብሩ ሥራ፣ በባለሙያዎች ለሚሠራው ሥራ ሁሉ የሚሆን ነው። ታዲያ ዛሬ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው?”

6ከዚያም የቤተ ሰብ መሪዎች፣ የነገዱ የእስራኤል ሹማምት፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም በንጉሡ ሥራ ላይ የተመደቡ ሹማምት በፈቃዳቸው ሰጡ፤ 7ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሰጡትም አምስት ሺሕ መክሊት29፥7 170 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው ወርቅ፣ ዐሥር ሺሕ ዳሪክ29፥7 84 ኪሎ ግራም ያህል ነው ወርቅ፣ ዐሥር ሺሕ መክሊት29፥7 345 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው ብር፣ ዐሥራ ስምንት ሺሕ መክሊት29፥7 610 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው ናስ አንድ መቶ ሺሕ መክሊት29፥7 345 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው ብረት ነው። 8የከበሩ ድንጋዮች ያለውም ሁሉ፣ በጌድሶናዊው በይሒኤል አማካይነት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አስገባ። 9ስጦታው በገዛ ፈቃድና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆቹ ስላደረጉት የበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።

የዳዊት ጸሎት

10ዳዊትም በመላው ጉባኤ ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል አመሰገነ፤

“የአባታችን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤

ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአንተ ምስጋና ይሁን።

11እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና

በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና፤

ታላቅነት፣ ኀይል፣ ክብርና ግርማ የአንተ ነው።

እግዚአብሔር ሆይ፤ መንግሥትም የአንተ ነው፤

አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።

12ባለጠግነትና ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤

አንተም የሁሉ ገዥ ነህ፤

ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም ብርታትን ለመስጠት፣

ብርታትና ኀይል በእጅህ ነው።

13አምላካችን ሆይ፤ አሁንም እናመሰግንሃለን፤

ለከበረው ስምህም ውዳሴ እናቀርባለን።

14“ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነውን ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናደርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው? 15እኛም እንደ ቀድሞ አባቶቻችን በፊትህ መጻተኞችና እንግዶች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤ ተስፋ ቢስም ነው። 16እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ለተቀደሰው ስምህ ቤተ መቅደስ እንሠራልህ ዘንድ ይህ በብዛት ያዘጋጀነው ሁሉ፣ ከእጅህ የተገኘና ሁሉም የአንተ ነው። 17አምላኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃድና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ። 18የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ሐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው። 19ትእዛዞችህን፣ ደንብህንና ሥርዐትህን እንዲጠብቅ፣ እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ታላቅ ሕንጻ ለመሥራት እንዲችል፣ ለልጄ ለሰሎሞን ፍጹም ፈቃደኝነት ስጠው።”

20ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን ወድሱት” አላቸው። ስለዚህ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ወደሱ፤ በእግዚአብሔር በንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ።

ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑ በይፋ ታወቀ

29፥21-25 ተጓ ምብ – 1ነገ 1፥28-53

21በማግስቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠዉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም አቀረቡ፤ ይህም አንድ ሺሕ ወይፈን፣ አንድ ሺሕ አውራ በግ፣ አንድ ሺሕ የበግ ጠቦት ሲሆን፣ ከመጠጥ ቍርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዋዕቶች ጋር ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ። 22በዚያችም ዕለት በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም።

ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ለሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንም በእግዚአብሔር ፊት ቀቡት፤ ሳዶቅንም ካህናቸው እንዲሆን ቀቡት። 23ሰሎሞንም ነግሦ በአባቱ በዳዊት ምትክ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ተከናወነለት፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት። 24የጦር አለቆቹና ኀያላኑ ሁሉ እንዲሁም የንጉሡ የዳዊት ወንዶች ልጆች በሙሉ ታማኝነታቸውን ለንጉሥ ሰሎሞን አረጋገጡለት።

25እግዚአብሔርም ሰሎሞንን በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ሁሉ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከእርሱ በፊት ለነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ያላጐናጸፋቸውን ንጉሣዊ ክብር ሁሉ ሰጠው።

የዳዊት መሞት

29፥26-28 ተጓ ምብ – 1ነገ 2፥10-12

26የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር። 27እርሱም በኬብሮን ሰባት ዓመት፣ በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በአጠቃላይ አርባ ዓመት ነገሠ። 28ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጐድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ልጁ ሰሎሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

29በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ድርጊት በባለ ራእዩ በሳሙኤል የታሪክ መጽሐፍ፣ በነቢዩ በናታን የታሪክ መጽሐፍ፣ በባለ ራእዩ በጋድ የታሪክ መጽሐፍ ተጽፏል። 30የተጻፈውም በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ዝርዝር ጕዳዮችና በዙሪያው ከከበቡት፣ ከእስራኤልና ከሌሎች አገር መንግሥታት ታሪክ ጋር ነው።

O Livro

1 Crónicas 29:1-30

As ofertas para a construção do templo

1David voltou-se depois para toda a assembleia: “O meu filho Salomão, que Deus escolheu para ser o próximo rei de Israel, ainda é novo e inexperiente e a tarefa que está à sua frente é enorme, porque o templo que terá de construir não é uma edificação qualquer; é algo a ser dedicado ao Senhor Deus! 2Usando todos os recursos que estavam à minha disposição, juntei tudo o que me foi possível para essa construção: ouro, prata, bronze, ferro, madeira, grandes quantidades de ónix e outras pedras preciosas, joias e mármore. 3Visto que amo a casa do meu Deus, do meu tesouro pessoal dediquei também muita coisa para essa obra, além dos materiais de construção que estão armazenados. 4Essas contribuições pessoais consistem em 100 000 quilos de ouro de Ofir e 235 toneladas de prata pura, para ser usada na cobertura das paredes do edifício. 5Este ouro e prata também serão utilizados no fabrico de utensílios e nas decorações. Quem quer agora seguir o meu exemplo? Quem quer consagrar-se a si próprio e tudo o que tem ao Senhor?”

6Então os chefes dos clãs, os cabeças das tribos, os oficiais do exército, os responsáveis da administração da casa real 7ofereceram voluntariamente um total de 170 toneladas, mais 84 quilos de ouro, 340 toneladas de prata, 610 toneladas de bronze e 3400 toneladas de ferro. 8Também ofereceram grande quantidade de joalharia, que foi depositada no tesouro do templo, à guarda de Jeiel, descendente de Gerson. 9Toda a gente estava feliz com esta oportunidade de serviço, pois deram de coração ao Senhor. O rei David ficou profundamente comovido de alegria.

David louva o Senhor

10Ainda na presença de toda a assembleia, David expressou os seus louvores ao Senhor desta maneira:

Senhor, Deus do nosso pai Israel,

que o teu nome seja louvado sempre e sempre!

11Teu é o poder e a glória e a majestade e a vitória.

Tudo o que há nos céus e na Terra te pertence,

ó Senhor, e este reino é teu.

Adoramos-te porque tudo está sob o teu controlo.

12Riquezas e honra vêm apenas por ti;

tu és o juiz de toda a humanidade.

Teu é o poder e a força.

É por tua vontade que os homens se tornam grandes

e recebem força.

13Ó nosso Deus, nós te louvamos

e celebramos o teu nome glorioso!

14Quem sou eu e quem é o meu povo para te oferecermos tais coisas? Tudo o que temos vem de ti; nós apenas te damos aquilo que vem de ti! 15Nós vivemos aqui na Terra apenas por um curto espaço de tempo, como estrangeiros numa terra que era dos nossos pais. Os nossos dias na Terra são como uma sombra que passa rapidamente, sem deixar vestígios. 16Ó Senhor, nosso Deus, todos estes materiais que juntámos para construir um templo para o teu santo nome te pertencem! 17Eu sei, Deus meu, que provas os homens para veres se são retos, porque te agradas de homens sinceros. Sabes que fiz tudo isto com as mais puras intenções e que velei para que o povo oferecesse os seus donativos voluntariamente e com alegria. 18Senhor, Deus dos nossos pais Abraão, Isaque e Israel, faz com que o teu povo queira sempre obedecer-te e que o seu amor por ti nunca se altere! 19Dá ao meu filho Salomão um coração reto para contigo, para que queira obedecer às tuas leis, mandamentos e preceitos, e procure empenhadamente finalizar a construção do teu templo para o qual fiz estes preparativos.”

20Depois David disse a todo o povo: “Deem louvores ao Senhor, vosso Deus!” E todos louvaram o Senhor, Deus dos seus antepassados, inclinando-se diante do Senhor e do rei.

Salomão reconhecido como rei

21No dia seguinte trouxeram 1000 novilhos, 1000 carneiros e 1000 cordeiros e ofereceram-nos em holocausto ao Senhor. Também apresentaram ofertas de vinho e muitos outros sacrifícios em favor de todo o Israel. 22Seguidamente, comeram e beberam perante o Senhor, com grande alegria.

Novamente consagraram Salomão, o filho do rei David, como seu rei. Ungiram-no perante o Senhor como seu chefe e Zadoque como seu sacerdote. 23Desta forma, Salomão sucedeu ao seu pai David no trono do Senhor; prosperou grandemente e todo o Israel lhe obedeceu. 24Os líderes nacionais, os comandantes do exército e todos os seus irmãos submeteram-se ao rei Salomão.

25O Senhor deu-lhe grande popularidade junto de todo o povo de Israel. Conseguiu angariar mais riquezas e honra do que qualquer outro rei que reinou anteriormente em Israel.

A morte de David

(1 Rs 2.10-12)

26David, filho de Jessé, reinou em Israel 27durante 40 anos; 7 anos em Hebrom e 33 anos em Jerusalém. 28Morreu numa idade avançada, rico e honrado. O seu filho Salomão reinou em seu lugar.

29A história do rei David foi escrita nas crónicas do profeta Samuel, na história escrita pelo profeta Natã e na história do vidente Gad. 30Estas narrativas dizem respeito ao seu reino, ao seu poder e a tudo o que lhe aconteceu, a si e a Israel, assim como aos reis dos povos vizinhos.