1 ዜና መዋዕል 24 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 24:1-31

የካህናት አመዳደብ

1የአሮን ልጆች አመዳደብ እንደሚከተለው ነበረ፤

የአሮን ልጆች ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር ነበሩ። 2ናዳብና አብዩድ ግን ዘር ሳይተኩ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ አልዓዛርና ኢታምር ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር። 3ዳዊትም የአልዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር የሆነው አቢሜሌክ እየረዱት እንደየአገልግሎታቸው ሥርዐት እየለየ መደባቸው። 4ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተ ሰብ አለቆች፤ ከኢታምርም ዘሮች ስምንት የቤተ ሰብ አለቆች። 5ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።

6የሌዋዊው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአቤሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፈ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተ ሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመውሰድ ነው፤

7የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሪብ፣

ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ፤

8ሦስተኛው ለካሪም፣

አራተኛው ለሥዖሪም፣

9አምስተኛው ለመልክያ፣

ስድስተኛው ለሚያሚን፣

10ሰባተኛው ለአቆስ፣

ስምንተኛው ለአብያ፣

11ዘጠነኛው ለኢያሱ፣

ዐሥረኛው ለሴኬንያ፣

12ዐሥራ አንደኛው ለኤሊያሴብ፣

ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣

13ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፖ፣

ዐሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፣

14ዐሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፣

ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፣

15ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፣

ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣

16ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣

ሃያኛው ለኤዜቄል፣

17ሃያ አንደኛው ለያኪን፣

ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣

18ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣

ሃያ አራተኛ ለመዓዝያ ወጣ።

19የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር።

የተቀሩት ሌዋውያን

20ከቀሩት የሌዊ ዘሮች ደግሞ፦

ከእንበረም ወንዶች ልጆች፣ ሱባኤል፤

ከሱባኤል ወንዶች ልጆች፣ ዬሕድያ።

21ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤

አለቃው ይሺያ።

22ከይስዓራውያን ወገን፣ ሰሎሚት፤

ከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፣ ያሐት።

23የኬብሮን ወንዶች ልጆች፣ የመጀመሪያው ይሪያ24፥23 ሁለት የዕብራይስጥ ቅጆችና ጥቂት የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም 1ዜና 23፥19 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ የይሪያ ወንዶች ልጆች ይላሉ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቀምዓም።

24የዑዝኤል ልጅ፣

ሚካ ከሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር።

25የሚካ ወንድም ይሺያ፤

ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።

26የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ሙሲ።

የያዝያ ወንድ ልጅ በኖ።

27የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤

ከያዝያ በኖ፣ ሾሃም፣ ዘኩር፣ ዔብሪ።

28ከሞሖሊ፤ አልዓዛር፤ ይህ ሰው ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።

29ከቂስ፤ የቂስ ወንድ ልጅ፤

ይረሕምኤል።

30የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔዳር፣ ለኢያሪሙት።

እነዚህ እንግዲህ እንደየቤተ ሰባቸው የተቈጠሩ ሌዋውያን ነበሩ።

31ወንድሞቻቸው የአሮን ዘሮች እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱና የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኵሩም ቤተ ሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተ ሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

歷代志上 24:1-31

祭司的職務

1下面是亞倫子孫的班次。亞倫的兒子是拿答亞比戶以利亞撒以他瑪2拿答亞比戶比父親先死,而且沒有留下兒子,因此以利亞撒以他瑪做了祭司。 3以利亞撒的子孫撒督以他瑪的子孫亞希米勒的協助下,大衛亞倫的子孫分成班次,讓他們各司其職。 4以利亞撒的子孫中做首領的比以他瑪的子孫中做首領的多,他們被分成班次,以利亞撒的子孫中有十六個族長,以他瑪的子孫中有八個族長。 5因為以利亞撒的子孫中和以他瑪的子孫中都有人在聖所做首領事奉上帝,他們便用抽籤的方法公平地分班,分別在以利亞撒以他瑪家族中抽籤。 6利未拿坦業的兒子示瑪雅是書記。他在君王、首領、撒督祭司、亞比亞他的兒子亞希米勒、眾祭司和利未人的族長面前把抽出的名字記錄下來。

7第一籤抽出來的是耶何雅立,第二籤是耶大雅8第三籤是哈琳,第四籤是梭琳9第五籤是瑪基雅,第六籤是米雅民10第七籤是哈歌斯,第八籤是亞比雅11第九籤是耶書亞,第十籤是示迦尼12第十一籤是以利亞實,第十二籤是雅金13第十三籤是胡巴,第十四籤是耶是比押14第十五籤是璧迦,第十六籤是音麥15第十七籤是希悉,第十八籤是哈辟悉16第十九籤是毗他希雅,第二十籤是以西結17第二十一籤是雅斤,第二十二籤是迦末18第二十三籤是第來雅,第二十四籤是瑪西亞19他們照這班次,按以色列的上帝耶和華藉他們的祖先亞倫所定的條例,在耶和華的殿裡司職。

20其他的利未人還有暗蘭的後代書巴業書巴業的後裔耶希底亞21利哈比雅的長子伊示雅22以斯哈的後代示羅摩示羅摩的後代雅哈23希伯崙的長子耶利雅、次子亞瑪利亞、三子雅哈悉、四子耶加緬24烏薛的後代米迦米迦的後代沙密25米迦的弟兄伊示雅伊示雅的後代撒迦利雅26米拉利的兒子抹利姆示雅西雅雅西雅的兒子比挪27米拉利的後代雅西雅的兒子比挪朔含撒刻伊比利28抹利的兒子以利亞撒——以利亞撒沒有兒子, 29基士的後代耶拉篾30姆示的兒子末力以得耶利摩。這些按宗族都是利未人的後代。 31他們也在大衛王、撒督亞希米勒、眾祭司和利未人的族長面前抽籤,不分長幼,正如他們的親族亞倫的後代所做的一樣。