1 ዜና መዋዕል 22 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 22:1-19

1ከዚያም ዳዊት፣ “ከእንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ቤት በዚህ ይሆናል፤ እንዲሁም ስለ እስራኤል የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚሁ ይቆማል” አለ።

ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የተደረገ ዝግጅት

2ስለዚህ ዳዊት በእስራኤል የሚኖሩ መጻተኞች እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ ከመካከላቸውም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚሠራበትን ጥርብ ድንጋይ እንዲያዘጋጁ ጠራቢዎችን መደበ። 3ለቅጥር በሮቹ ምስማርና ማጠፊያ የሚሆን ብዙ ብረትና ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስ አዘጋጀ። 4እንዲሁም ሲዶናውያንና ጢሮሳውያን በብዛት አምጥተውለት ስለ ነበር፣ ስፍር ቍጥር የሌለው የዝግባ ዕንጨት አሰናዳ።

5ዳዊትም፣ “ልጄ ሰሎሞን ወጣት ነው፤ ልምዱም የለውም፤ ለእግዚአብሔር የሚሠራው ቤተ መቅደስ ደግሞ እጅግ የሚያምር፣ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ ዝናው የተሰማና እጅግ የተዋበ መሆን አለበት፤ ስለዚህ ሁሉንም እኔ አዘጋጃለሁ” አለ። እንዳለውም ዳዊት ከመሞቱ በፊት በብዛት አዘጋጀ።

6ከዚያም ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሠራ አዘዘው።

7ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፤ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ለመሥራት በልቤ ዐስብ ነበር፤ 8ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል መጣልኝ፤ ‘አንተ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ብዙ ጦርነትም አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ያፈሰስህ ስለሆነ፣ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም፤ 9ነገር ግን የሰላምና የዕረፍት ሰው የሆነ ልጅ ትወልዳለህ፤ በየአቅጣጫው ካሉ ጠላቶቹ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙም ሰሎሞን ይባላል። በዘመኑም ለእስራኤል ሰላምንና ጸጥታን እሰጣለሁ። 10ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋኑንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’

11“አሁንም ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ እንድትፈጽመው በተናገረውም መሠረት፣ ተሳክቶልህ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ያብቃህ። 12በእስራኤል ላይ አለቃ ባደረገህ ጊዜ፣ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትፈጽም ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ። 13እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጉንና ሥርዐቱን ተጠንቅቀህ ብትጠብቅ ይሳካልሃል፤ አይዞህ ጠንክር፤ በርታ፤ ተስፋም አትቍረጥ።

14ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺሕ መክሊት22፥14 3,450 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት22፥14 34,500 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጀት በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት። 15ድንጋይ ጠራቢዎች፣ ግንበኞች፣ ዐናጢዎች የሆኑ ብዙ ሠራተኞች፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ ሙያ የተጠበቡ ሰዎች አሉህ፤ 16እነዚህም ቍጥራቸው እጅግ የበዛ የወርቅ፣ የብር፣ የናስና የብረት ሠራተኞች ናቸው። በል ሥራህን ጀምር፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን።”

17ከዚያም ዳዊት የእስራኤል መሪዎች ሁሉ ልጁን ሰሎሞንን እንዲረዱት አዘዘ፤ 18እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር አምላካችሁ እስካሁን ከእናንተ ጋር አይደለምን? በየአቅጣጫውስ ዕረፍትን ሰጥቷችሁ የለምን? የምድሪቱን ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል፤ ምድሪቱም ለእግዚአብሔርና ለሕዝቡ ተገዝታለች። 19አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁን ለመፈለግ ልባችሁንና ነፍሳችሁን ሰብስቡ። የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦትና ንዋያተ ቅድሳቱን ለእግዚአብሔር ስም ወደሚሠራው ቤተ መቅደስ አምጥታችሁ የአምላክን የእግዚአብሔርን መቅደስ ሥሩ።”

New International Reader’s Version

1 Chronicles 22:1-19

1David announced, “The house of the Lord God will be built here. Israel’s altar for burnt offerings will also be here.”

David Makes Plans for Building the Temple

2David gave orders to bring together the outsiders who were living in Israel. He appointed some of them to cut stones. He wanted them to prepare blocks of stone for building the house of God. 3David provided a large amount of iron to make nails. They were for the doors of the gateways and for the fittings. He provided more bronze than anyone could weigh. 4He also provided more cedar logs than anyone could count. The people of Sidon and Tyre brought large numbers of logs to David.

5David said, “My son Solomon is young. He’s never done anything like this before. The house that will be built for the Lord should be very grand and wonderful. All the nations should consider it to be famous and beautiful. I’ll get things ready for it.” So David got many things ready before he died.

6Then he sent for his son Solomon. He told him to build a house for the Lord, the God of Israel. 7David said to Solomon, “My son, with all my heart I wanted to build a house for the Lord my God. That’s where his Name will be. 8But a message from the Lord came to me. It said, ‘You have spilled the blood of many people. You have fought many wars. You are not the one who will build a house for my Name. That is because I have seen you spill the blood of many people on the earth. 9But you are going to have a son. He will be a man of peace. And I will give him peace and rest from all his enemies on every side. His name will be Solomon. I will give Israel peace and quiet while he is king. 10He will build a house for my Name. He will be my son. And I will be his father. I will make his kingdom secure over Israel. It will last forever.’

11“My son, may the Lord be with you. May you have success. May you build the house of the Lord your God, just as he said you would. 12May the Lord give you good sense. May he give you understanding when he makes you king over Israel. Then you will keep the law of the Lord your God. 13Be careful to obey the rules and laws the Lord gave Moses for Israel. Then you will have success. Be strong and brave. Don’t be afraid. Don’t lose hope.

14“I’ve tried very hard to provide for the Lord’s temple. I’ve provided 3,750 tons of gold and 37,500 tons of silver. I’ve provided more bronze and iron than anyone can weigh. I’ve also given plenty of wood and stone. You can add to it. 15You have a lot of workers. You have people who can cut stones and people who can lay the stones. You have people who can work with wood. You also have people who are skilled in every other kind of work. 16Some of them can work with gold and silver. Others can work with bronze and iron. There are more workers than anyone can count. So begin the work. May the Lord be with you.”

17Then David ordered all Israel’s leaders to help his son Solomon. 18He said to them, “The Lord your God is with you. He’s given you peace and rest on every side. He’s handed over to me the people who are living in the land. The land has been brought under the control of the Lord and his people. 19So be committed to the Lord your God with all your heart and soul. Start building the temple of the Lord God. Then bring the ark of the covenant of the Lord into it. Also bring in the sacred objects that belong to God. The temple will be built for the Name of the Lord.”