1 ዜና መዋዕል 21 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 21:1-30

ዳዊት ተዋጊ ሰራዊቱን ቈጠረ

21፥1-26 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 24፥1-25

1ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሥቶ ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲቈጥር አነሣሣው። 2ዳዊትም ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች፣ “ሄዳችሁ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ያሉትን እስራኤላውያን ቍጠሩ፤ ከዚያም ምን ያህል እንደ ሆኑ ዐውቅ ዘንድ ንገሩኝ” አላቸው።

3ኢዮአብ ግን፣ “እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት አሁን ካለው በላይ በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ሁሉስ ቢሆኑ የጌታዬ ተገዦች አይደሉምን? ታዲያ ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ለምንስ በእስራኤል ላይ በደል ያመጣል?” አለ።

4ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል ኢዮአብን አሸነፈው፤ ስለዚህ ኢዮአብ ወጣ፤ በመላው እስራኤል ከተዘዋወረ በኋላ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። 5ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቍጥር ለዳዊት አቀረበ፤ እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺሕ ሲሆኑ፣ ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ።

6ኢዮአብ ግን የንጉሡ ትእዛዝ አስጸያፊ ነበረና፣ የሌዊንና የብንያምን ነገድ ጨምሮ አልቈጠረም። 7ይህ ትእዛዝ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር እስራኤልን ቀጣ።

8ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔርን፣ “ይህን በማድረጌ እጅግ በድያለሁ፤ የፈጸምሁትም የስንፍና ሥራ ስለሆነ፣ የባሪያህን በደል እንድታስወግድ እለምንሃለሁ” አለ።

9እግዚአብሔርም የዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤ 10“ሂድና ለዳዊት እንዲህ ብለው ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ እነሆ፣ ሦስት ምርጫ ሰጥቼሃለሁ፤ በአንተ ላይ እንዳደርስብህ አንዱን ምረጥ።’ ”

11ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ ‘በል እንግዲህ አንዱን ምረጥ፤ 12የሦስት ዓመት ራብ ወይስ የጠላቶችህ ሰይፍ ለሦስት ወር አይሎብህ መጥፋት ወይስ ሦስት ቀን የእግዚአብሔር ሰይፍ መቅሠፍት በምድሪቱ ላይ ወርዶ የእግዚአብሔር መልአክ እስራኤልን ሁሉ ያጥፋ?’ ለላከኝ ምን እንደምመልስ ቍርጡን ንገረኝ።”

13ዳዊትም ጋድን፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ታላቅ ስለሆነ፣ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል፤ በሰው እጅስ አልውደቅ” አለ።

14ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መቅሠፍት ላከ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺሕ ሰው ዐለቀ። 15እንዲሁም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲያጠፋ መልአክ ላከ፤ መልአኩ ሊያጠፋትም ሲል እግዚአብሔር አይቶ ስለሚደርሰው ጥፋት ዐዘነ፤ ሕዝቡን የሚያጠፋውንም መልአክ፣ “እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።

16ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት፣ የእግዚአብሔር መልአክ በሰማይና በምድር መካከል ቆሞ አየ፤ መልአኩም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ከዚያም ዳዊትና ሽማግሌዎቹ ማቅ እንደ ለበሱ በግምባራቸው ተደፉ።

17ዳዊት እግዚአብሔርን፣ “ተዋጊዎቹ እንዲቈጠሩ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? ኀጢአት የሠራሁትም ሆነ የበደልሁት እኔ ነኝ፤ እነዚህ እኮ በጎች ናቸው፤ ታዲያ እነርሱ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን እንጂ፣ መቅሠፍቱ በሕዝብህ ላይ አይውረድ” አለ።

18ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ እንዲነግረው ጋድን አዘዘው። 19ዳዊትም ጋድ በእግዚአብሔር ስም በነገረው ቃል መሠረት ለመፈጸም ወጣ።

20ኦርና ስንዴ በመውቃት ላይ ሳለ ዘወር ሲል መልአኩን አየ፤ አብረውት የነበሩት አራት ወንዶች ልጆቹም ተሸሸጉ። 21ዳዊት ወደ እርሱ እየቀረበ መጣ፤ ኦርና ቀና ብሎ ሲመለከት፣ ዳዊትን አየው፤ ከዐውድማውም ወጥቶ መሬት ላይ ለጥ ብሎ በመደፋት ለዳዊት እጅ ነሣ።

22ዳዊትም፣ “በሕዝቡ ላይ የወረደው መቅሠፍት እንዲወገድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ዐውድማህን ልውሰደው፤ ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ” አለው።

23ኦርናም ዳዊትን፣ “እንዲሁ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሥ ደስ ያለውን ያድርግ። እነሆ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፣ መውቂያ በትሮቹን ለማቀጣጠያ ዕንጨት፣ ስንዴውን ደግሞ ለእህል ቍርባን እንዲሆን እሰጣለሁ፤ ሁሉንም እኔ እሰጣለሁ” አለ።

24ንጉሥ ዳዊት ግን ለኦርና “አይደረግም፤ ሙሉውን ዋጋ እኔ እከፍላለሁ፤ የአንተ የሆነውን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ አልፈልግም፤ ዋጋ ያልከፈልሁበትንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” ሲል መለሰለት።

25ስለዚህ ዳዊት ለኦርና የቦታውን ዋጋ ስድስት መቶ ሰቅል21፥25 7 ኪሎ ግራም ያህል ነው ወርቅ ከፈለ። 26ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት21፥26 በትውፊት፣ የሰላም መሥዋዕት ይባላል አቀረበ። እግዚአብሔርንም ጠራ፤ እግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማይ በእሳት መለሰለት።

27ከዚያም እግዚአብሔር ለመልአኩ ተናገረ፤ መልአኩም ሰይፉን ወደ አፎቱ መለሰ። 28በዚያን ጊዜ ዳዊት፣ እግዚአብሔር በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ እንደ መለሰለት ሲያይ፣ በዚያው ቦታ መሥዋዕት ማቅረብ ጀመረ። 29ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳንና የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚያ ጊዜ በገባዖን ኰረብታ ላይ ነበረ። 30ዳዊት የእግዚአብሔርን መልአክ ሰይፍ ስለ ፈራ ወደዚያ ሄዶ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ አልቻለም።

Thai New Contemporary Bible

1พงศาวดาร 21:1-30

ดาวิดทรงนับไพร่พล

(2ซมอ.24:1-25)

1ซาตานลุกขึ้นเล่นงานอิสราเอล และดลใจให้ดาวิดทำสำมะโนไพร่พลอิสราเอล 2ดาวิดจึงตรัสกับโยอาบและเหล่าแม่ทัพนายกองว่า “จงไปนับไพร่พลอิสราเอลจากเมืองเบเออร์เชบาจดเมืองดานแล้วกลับมารายงาน เพื่อเราจะรู้ว่ามีคนอยู่เท่าไร”

3โยอาบทูลทัดทานว่า “ขอองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงเพิ่มพูนกำลังพลของพระองค์ร้อยเท่า ทั้งหมดก็เป็นคนของฝ่าพระบาทไม่ใช่หรือ? เหตุใดจึงทรงประสงค์ให้ทำเช่นนี้? ควรหรือที่จะนำความผิดมาสู่อิสราเอล?”

4แต่คำบัญชาของกษัตริย์ย่อมมีอำนาจเหนือโยอาบ โยอาบจึงเดินทางไปทั่วดินแดนอิสราเอลแล้วกลับมายังกรุงเยรูซาเล็ม 5โยอาบทูลรายงานดาวิดว่าจำนวนคนที่ออกรบได้ทั่วทั้งอิสราเอลมี 1,100,000 คน และ 470,000 คนในยูดาห์

6แต่โยอาบไม่ได้รวมจำนวนคนเลวีและเบนยามิน เพราะเขารู้สึกว่าคำบัญชานี้น่ารังเกียจ 7คำบัญชานี้ก็เป็นสิ่งที่ชั่วในสายพระเนตรของพระเจ้าด้วย ดังนั้นพระองค์จึงทรงลงโทษอิสราเอล

8ดาวิดกราบทูลพระเจ้าว่า “สิ่งที่ข้าพระองค์ทำนั้นบาปมาก บัดนี้ขอทรงโปรดยกโทษความผิดของผู้รับใช้ของพระองค์ ข้าพระองค์ได้ทำสิ่งที่โง่เขลามาก”

9องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับกาดผู้ทำนายของดาวิดว่า 10“จงไปบอกดาวิดว่า ‘องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสดังนี้ว่า เรามีข้อเสนอสามประการ ให้เจ้าเลือกอย่างหนึ่งแล้วเราจะจัดการกับเจ้าตามนั้น’ ”

11กาดจึงเข้าเฝ้าและทูลดาวิดว่า “องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสดังนี้ว่า ‘จงเลือกเอา 12ระหว่างการกันดารอาหารสามปี หรือถูกดาบของศัตรูของเจ้าล้างผลาญสามเดือน21:12 ฉบับ LXX. และ Vulg. ว่าเตลิดหนีจากการไล่ล่าฆ่าฟันของศัตรูสามเดือน(ดู2ซมอ.24:13) หรือถูกลงโทษด้วยดาบขององค์พระผู้เป็นเจ้าสามวันคือ โรคระบาดร้ายแรงซึ่งทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้าจะนำหายนะมาสู่อิสราเอลทุกหย่อมหญ้า’ ดังนั้นขอทรงแจ้งคำตอบเพื่อข้าพระบาทจะนำไปทูลพระองค์ผู้ทรงใช้ข้าพระบาทมา”

13ดาวิดตรัสตอบกาดว่า “เราลำบากใจมาก แต่ขอตกอยู่ในอุ้งพระหัตถ์ขององค์พระผู้เป็นเจ้าดีกว่าตกอยู่ในเงื้อมมือของมนุษย์ เพราะพระเมตตาคุณของพระองค์ใหญ่หลวงนัก”

14ฉะนั้นองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงให้เกิดโรคระบาดในอิสราเอล เป็นผลให้มีคนล้มตายเจ็ดหมื่นคน 15ในช่วงโรคระบาด พระเจ้าทรงใช้ทูตสวรรค์องค์หนึ่งมาทำลายล้างกรุงเยรูซาเล็ม แต่ขณะนั้นองค์พระผู้เป็นเจ้าทอดพระเนตรแล้วทรงทุกข์พระทัยเนื่องด้วยภัยพิบัตินั้น จึงตรัสแก่ทูตผู้ทำลายว่า “พอแล้ว! ยั้งมือเถิด” ขณะนั้นทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้ากำลังยืนอยู่ที่ลานนวดข้าวของอาราวนาห์21:15 ภาษาฮีบรูว่าโอรนันเป็นอีกรูปหนึ่งของอาราวนาห์เช่นเดียวกับข้อ 18-28ชาวเยบุส

16เมื่อดาวิดทอดพระเนตรเห็นทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้ายืนอยู่ระหว่างฟ้าสวรรค์กับแผ่นดินโลก และถือดาบอยู่เหนือกรุงเยรูซาเล็ม ดาวิดกับบรรดาผู้อาวุโสซึ่งสวมผ้ากระสอบอยู่จึงหมอบกราบซบหน้าลงกับพื้น

17ดาวิดกราบทูลพระเจ้าว่า “ข้าพระองค์ไม่ใช่หรือที่สั่งให้นับจำนวนไพร่พล ข้าพระองค์คือผู้ที่ทำผิดทำบาป ประชากรเหล่านี้เป็นแต่เพียงฝูงแกะ พวกเขาทำผิดอันใดเล่า? ข้าแต่พระยาห์เวห์พระเจ้าของข้าพระองค์ ขอทรงลงโทษข้าพระองค์กับครอบครัวเท่านั้นเถิด แต่อย่าให้ภัยพิบัตินี้ยังคงอยู่กับประชากรของพระองค์เลย”

18ทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้าจึงสั่งกาดให้ไปแจ้งดาวิดให้ขึ้นไปสร้างแท่นบูชาถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้าที่ลานนวดข้าวของอาราวนาห์ชาวเยบุส 19ดาวิดจึงไปปฏิบัติตามพระดำรัสซึ่งกาดได้กล่าวไว้ในพระนามของพระยาห์เวห์

20ขณะอาราวนาห์กำลังนวดข้าวสาลีอยู่ เขาเหลียวมาเห็นทูตสวรรค์ บุตรชายสี่คนของเขาที่อยู่ด้วยก็วิ่งหนีไปซ่อนตัว 21แล้วอาราวนาห์เห็นดาวิดเดินเข้ามาหา จึงวิ่งจากลานนวดข้าวมากราบซบหน้าลงถึงดินต่อหน้าดาวิด

22ดาวิดตรัสกับอาราวนาห์ว่า “เราขอซื้อลานนวดข้าวแห่งนี้จากเจ้าเต็มราคา แล้วเราจะสร้างแท่นบูชาถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้า พระองค์จะได้ทรงระงับโรคระบาดครั้งนี้”

23อาราวนาห์ทูลดาวิดว่า “ข้าแต่องค์กษัตริย์ ขอฝ่าพระบาททรงรับไปเถิด จะใช้ทำสิ่งใดก็ตามแต่จะโปรด ขอทรงรับวัวไปเป็นเครื่องเผาบูชา เลื่อนนวดข้าวสามารถใช้เป็นฟืน และข้าวสาลีสำหรับเป็นเครื่องธัญบูชา ข้าพระบาทขอถวายทั้งหมดนี้”

24แต่กษัตริย์ดาวิดตรัสตอบอาราวนาห์ว่า “เรายืนยันที่จะซื้อเต็มราคา เราไม่อาจรับสิ่งที่เป็นของเจ้าไปถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้า หรือจะถวายเครื่องเผาบูชาโดยไม่ลงทุนอะไรเลย”

25ดาวิดจึงทรงจ่ายทองคำหนักประมาณ 7 กิโลกรัม21:25 ภาษาฮีบรูว่า600 เชเขล ให้แก่อาราวนาห์เป็นค่าที่ดิน 26แล้วดาวิดสร้างแท่นบูชาขึ้นที่นั่นถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้า และถวายเครื่องเผาบูชากับเครื่องสันติบูชาด้วย ดาวิดร้องทูลองค์พระผู้เป็นเจ้าองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงตอบโดยให้ไฟจากฟ้าสวรรค์มาเผาเครื่องบูชาบนแท่นนั้น

27แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาให้ทูตองค์นั้นเก็บดาบเข้าฝัก 28เมื่อดาวิดเห็นว่าองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงตอบคำวิงวอนที่ลานนวดข้าวของอาราวนาห์ชาวเยบุส ก็ทรงถวายเครื่องบูชาที่นั่นอีก 29พลับพลาขององค์พระผู้เป็นเจ้าและแท่นบูชาซึ่งโมเสสได้สร้างขึ้นในถิ่นกันดารยังคงอยู่บนสถานบูชาบนที่สูงในกิเบโอน 30แต่ดาวิดไม่สามารถเสด็จไปทูลถามพระเจ้าที่นั่น เพราะกลัวดาบของทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้า