1 ዜና መዋዕል 2 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 2:1-55

የእስራኤል ወንዶች ልጆች

2፥1-2 ተጓ ምብ – ዘፍ 35፥23-26

1የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ 2ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ አሴር።

ይሁዳ

2፥5-15 ተጓ ምብ – ሩት 4፥18-22ማቴ 1፥3-6

እስከ ኤስሮን ወንዶች ልጆች

3የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤

ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። 4የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤

ይሁዳም በአጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።

5የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤

ኤስሮም፣ ሐሙል።

6የዛራ ወንዶች ልጆች፤

ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ2፥6 አያሌ የዕብራይስጥ ቅጆች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አንዳንድ የዕብራይስጥ፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጆች (እንዲሁም 1ነገ 4፥31 ይመ) ግን፣ ዳርዳ ይላሉ።፤ በአጠቃላይ አምስት ናቸው።

7የከርሚ ወንድ ልጅ አካን2፥7 አካን ማለት፣ ችግር ወይም፣ መከራ ማለት ነው።

እርሱም ፈጽሞ መደምሰስ የነበረበትን ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት2፥7 የዕብራይስጡ ቃል አንድን ሰው ወይም ነገር ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠትን ያመለክታል። እንዲመጣ ያደረገ ነው።

8የኤታን ወንድ ልጅ፤

አዛርያ።

9የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤

ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።2፥9 ዕብራይስጡ፣ ከሉባይ ይላል፤ ይኸውም፣ ካሌብ ማለት ነው።

ከኤስሮም ልጅ ከአራም ጀምሮ ያለው የትውልድ ሐረግ

10አራም አሚናዳብን ወለደ፤

አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤

11ነአሶን ሰልሞንን2፥11 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም (እንዲሁም ሩት 4፥21) ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ሳልማ ወለደ፤

ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ።

12ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤

ኢዮቤድ እሴይን ወለደ።

13የእሴይ ወንዶች ልጆች፤

የበኵር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣

ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣ 14አራተኛ ልጁ ናትናኤል፣

አምስተኛ ልጁ ራዳይ፣ 15ስድስተኛ ልጁ አሳም፣

ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።

16እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ።

የጽሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣኤል ነበሩ።

17አቢግያ አሜሳይን ወለደች፤ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።

የኤስሮም ልጅ ካሌብ

18የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ ከዓዙባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ያሳር፣ ሶባብ፣ አርዶን።

19ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።

20ሆር ኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።

21ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።

22ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር።

23ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ስድሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት2፥23 ወይም፣ የኢያዕርን መኖሪያ ነጠቁ

እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።

24ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት2፥24 በዚህም ሆነ በቍጥር 42፡45፡49-52 ላይ፣ አባት ማለት፣ የአገር ሽማግሌ ወይም፣ የጦር መሪ ማለት ነው። አሽሑርን ወለደችለት።

የኤስሮም ልጅ ይረሕምኤል

25የኤስሮም የበኵር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤

የበኵር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም፣ አኪያ። 26ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናም እናት ነበረች።

27የይረሕምኤል የበኵር ልጁ የራም ወንዶች፤

መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር።

28የኦናም ወንዶች ልጆች፤

ሸማይና ያዳ።

የሸማይ ወንዶች ልጆች፤

ናዳብና አቢሱር።

29የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።

30የናባድ ወንዶች ልጆች፤

ሴሌድ፣ አፋይም፤ ሴሌድ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።

31የአፋይም ወንድ ልጅ፤

ይሽዒ። ይሽዒም ሶሳን ወለደ።

ሶሳን አሕላይን ወለደ።

32የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ዮናታን፤ ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።

33የዮናታን ወንዶች ልጆች፤

ፌሌት፣ ዛዛ።

እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።

34ሶሳን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።

እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው። 35ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓታይ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።

36ዓታይ ናታንን ወለደ፤

ናታንም ዛባድን ወለደ፤

37ዛባድ ኤፍላልን ወለደ፤

ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤

38ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤

ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤

39ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤

ኬሌስ ኤልዓሣን ወለደ፤

40ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤

ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤

41ሰሎም የቃምያን ወለደ፤

የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።

የካሌብ ጐሣዎች

42የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤

የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤

ዚፍም መሪሳን2፥42 የዚህ ቃል የዕብራይስጡ ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ።

43የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤

ቆሬ፣ ተፉዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።

44ሽማዕ ረሐምን ወለደ፤

ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ።

ሬቄም ሸማይን ወለደ፤

45ሸማይም ማዖንን ወለደ፤

ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ።

46የካሌብ ቁባት ዔፉ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች።

ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።

47የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤

ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።

48የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደችለት።

49እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች።

ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።

50እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ።

የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤

ሦባል የቂርያትይዓሪም አባት፤ 51ሰልሞን የቤተ ልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።

52የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤

የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤ 53እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጐሣዎች፤ ይትራውያን፣ ፉታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፣ ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ከእነዚህ የመጡ ጐሣዎች ነበሩ።

54የሰልሞን ዘሮች፤

ቤተ ልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኩሌታ፣ ጾርዓውያን። 55በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጐሣዎች2፥55 ወይም፣ ሶፍራውያን ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።

Thai New Contemporary Bible

1พงศาวดาร 2:1-55

เชื้อสายของอิสราเอล

(ปฐก.35:23-26)

1บุตรของอิสราเอล ได้แก่

รูเบน สิเมโอน เลวี ยูดาห์ อิสสาคาร์ เศบูลุน 2ดาน โยเซฟ เบนยามิน นัฟทาลี กาด และอาเชอร์

ยูดาห์

(นรธ.4:18-22; มธ.1:3-6)

ถึงบุตรของเฮสโรน

3บุตรของยูดาห์ ได้แก่

เอร์ โอนัน และเชลาห์ ทั้งสามคนเกิดจากธิดาของชูอาชาวคานาอัน เอร์บุตรหัวปีนั้นเป็นคนชั่วในสายพระเนตรขององค์พระผู้เป็นเจ้า พระองค์จึงทรงประหารเขา 4ทามาร์ลูกสะใภ้ของยูดาห์ให้กำเนิดลูกแฝด คือเปเรศกับเศราห์แก่ยูดาห์ ยูดาห์จึงมีบุตรชายทั้งหมดห้าคน

5บุตรของเปเรศ ได้แก่

เฮสโรนกับฮามูล

6บุตรของเศราห์ ได้แก่

ศิมรี เอธาน เฮมาน คาลโคล์ และดารดา2:6 สำเนาต้นฉบับภาษาฮีบรูส่วนใหญ่ว่าดารา(ดู1พกษ.4:31) รวมห้าคน

7บุตรของคารมี ได้แก่

อาคาร์2:7 แปลว่า ปัญหา ในพระธรรมโยชูวาเรียกอาคาร์ว่าอาคานผู้นำความทุกข์ร้อนมาสู่อิสราเอลโดยเก็บสิ่งที่พระเจ้าตรัสสั่งให้ทำลาย2:7 คำนี้ในภาษาฮีบรูหมายถึงสิ่งของหรือบุคคลที่ถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้าแล้ว ไม่อาจเรียกคืนได้ มักจะต้องทำลายให้หมดสิ้นไป

8บุตรของเอธาน ได้แก่

อาซาริยาห์

9บุตรของเฮสโรน ได้แก่

เยราห์เมเอล ราม และคาเลบ2:9 ภาษาฮีบรูว่าเคลุบัยเป็นอีกรูปหนึ่งของคาเลบ

จากรามบุตรของเฮสโรน

10รามเป็นบิดาของ

อัมมีนาดับ อัมมีนาดับเป็นบิดาของนาห์โชนผู้นำของตระกูลยูดาห์ 11นาห์โชนเป็นบิดาของสัลโมน2:11 ภาษาฮีบรูว่าสัลมา(ดูนรธ.4:21) สัลโมนเป็นบิดาของโบอาส 12โบอาสเป็นบิดาของโอเบด โอเบดเป็นบิดาของเจสซี

13เจสซีเป็นบิดาของ

เอลีอับบุตรหัวปี บุตรคนที่สองคืออาบีนาดับ คนที่สามคือชิเมอา 14คนที่สี่คือเนธันเอล คนที่ห้าคือรัดดัย 15คนที่หกคือโอเซม และคนที่เจ็ดคือดาวิด 16เจสซีมีบุตรสาวสองคนคือเศรุยาห์กับอาบีกายิล บุตรชายสามคนของนางเศรุยาห์ได้แก่ อาบีชัย โยอาบ และอาสาเฮล 17อาบีกายิลมีบุตรชื่ออามาสา มีสามีชื่อเยเธอร์ชาวอิชมาเอล

จากคาเลบบุตรของเฮสโรน

18คาเลบบุตรเฮสโรนมีภรรยาสองคนคือ อาซูบาห์กับเยรีโอท บุตรของอาซูบาห์ได้แก่ เยเชอร์ โชบับ และอารโดน 19เมื่ออาซูบาห์สิ้นชีวิตแล้ว คาเลบแต่งงานกับเอฟรัทซึ่งให้กำเนิดบุตรชื่อเฮอร์ 20เฮอร์เป็นบิดาของอูรี อูรีเป็นบิดาของเบซาเลล

21เฮสโรนแต่งงานกับบุตรสาวของมาคีร์บิดาของกิเลอาด (เขาแต่งงานเมื่ออายุหกสิบปี) และนางให้กำเนิดบุตรชื่อเสกุบ 22เสกุบเป็นบิดาของยาอีร์ซึ่งครองเมือง 23 แห่งในแดนกิเลอาด 23(แต่เกชูร์และอารัมยึดเมืองฮัฟโวทยาอีร์2:23 หรือยึดบริเวณที่ตั้งถิ่นฐานของยาอีร์ ไปจากเขา และยึดเมืองเคนัทกับหมู่บ้านหกสิบแห่งโดยรอบไปด้วย) คนเหล่านี้ล้วนเป็นวงศ์วานของมาคีร์บิดากิเลอาด

24หลังจากที่เฮสโรนเสียชีวิตในคาเลบเอฟราธาห์ อาบียาห์ภรรยาของเฮสโรนให้กำเนิดบุตรชื่ออัชฮูร์ซึ่งเป็นบิดา2:24 คำว่าบิดาอาจจะมีความหมายว่า ผู้นำทางพลเรือน หรือ ผู้นำทางทหาร เช่นเดียวกับข้อ 42,45,49-52 และอาจจะมีหมายความอย่างนี้ในที่อื่นๆ ด้วยของเทโคอา

จากเยราห์เมเอลบุตรของเฮสโรน

25บุตรของเยราห์เมเอลบุตรหัวปีของเฮสโรน ได้แก่

รามผู้เป็นบุตรหัวปี บูนาห์ โอเรน โอเซม และ2:25 หรือโอเรน และโอเซม ซึ่งเกิดจากนางอาหิยาห์ 26อาทาราห์ภรรยาอีกคนหนึ่งของเยราห์เมเอลให้กำเนิดบุตรชื่อโอนัม

27บุตรของรามบุตรหัวปีของเยราห์เมเอล ได้แก่

มาอัส ยามีน และเอเคอร์

28บุตรของโอนัม ได้แก่

ชัมมัยกับยาดา

บุตรของชัมมัย ได้แก่

นาดับกับอาบีชูร์

29อาบีชูร์กับภรรยาชื่ออาบีฮายิลมีบุตรชื่อ อาห์บานกับโมลิด

30บุตรของนาดับ ได้แก่

เสเลดกับอัปปาอิม เสเลดสิ้นชีวิตโดยไม่มีบุตร

31บุตรของอัปปาอิม ได้แก่

อิชอีบิดาของเชชัน เชชันเป็นบิดาของอาห์ลัย

32บุตรของยาดาน้องชายชัมมัย ได้แก่

เยเธอร์กับโยนาธาน เยเธอร์เสียชีวิตโดยไม่มีบุตร

33บุตรของโยนาธาน ได้แก่

เปเลธกับศาซา

คนเหล่านี้คือวงศ์วานของเยราห์เมเอล

34เชชันมีแต่บุตรสาว ไม่มีบุตรชาย

เขามีคนใช้ชาวอียิปต์คนหนึ่งชื่อยารฮา 35เชชันยกบุตรสาวคนหนึ่งให้ยารฮา นางให้กำเนิดบุตรชื่ออัททัย

36อัททัยเป็นบิดาของนาธัน

นาธันเป็นบิดาของศาบาด

37ศาบาดเป็นบิดาของเอฟลาล

เอฟลาลเป็นบิดาของโอเบด

38โอเบดเป็นบิดาของเยฮู

เยฮูเป็นบิดาของอาซาริยาห์

39อาซาริยาห์เป็นบิดาเฮเลส

เฮเลสเป็นบิดาของเอเลอาสาห์

40เอเลอาสาห์เป็นบิดาของสิสะมัย

สิสะมัยเป็นบิดาของชัลลูม

41ชัลลูมเป็นบิดาของเยคามิยาห์ เยคามิยาห์เป็นบิดาของเอลีชามา

ตระกูลของคาเลบ

42บุตรของคาเลบน้องชายของเยราห์เมเอล ได้แก่

เมชาบุตรหัวปีซึ่งเป็นบิดาของศิฟ ศิฟเป็นบิดาของมาเรชาห์2:42 ในภาษาฮีบรูวลีนี้มีความหมายไม่ชัดเจนซึ่งเป็นบิดาของเฮโบรน

43บุตรของเฮโบรน ได้แก่

โคราห์ ทัปปูวาห์ เรเคม และเชมา 44เชมาเป็นบิดาของราฮัม ราฮัมเป็นบิดาของโยรเคอัม เรเคมเป็นบิดาของชัมมัย 45ชัมมัยมีบุตรชื่อมาโอน มาโอนเป็นบิดาของเบธซูร์

46เอฟาห์ภรรยาน้อยของคาเลบเป็นมารดาของฮาราน โมซา และกาเซส ฮารานเป็นบิดาของกาเซส

47บุตรของยาดัย ได้แก่

เรเกม โยธาม เกชาน เปเลท เอฟาห์ และชาอัฟ

48มาอาคาห์ภรรยาน้อยของคาเลบมีบุตรชื่อเชเบอร์และทีรหะนาห์ 49นางยังให้กำเนิดชาอัฟผู้เป็นบิดาของมัดมันนาห์ และเชวาผู้เป็นบิดาของมัคเบนาห์กับกิเบอา และคาเลบมีบุตรสาวชื่ออัคสาห์ 50คนเหล่านี้คือวงศ์วานของคาเลบ

บุตรของเฮอร์ผู้เป็นบุตรชายหัวปีของเอฟราธาห์ ได้แก่

โชบาลผู้เป็นบิดาของคีริยาทเยอาริม 51สัลมาผู้เป็นบิดาของเบธเลเฮม และฮาเรฟผู้เป็นบิดาของเบธกาเดอร์

52วงศ์วานของโชบาลผู้เป็นบิดาของคีริยาทเยอาริม ได้แก่

ฮาโรเอห์ซึ่งเป็นต้นตระกูลของชาวมานาฮาทครึ่งหนึ่ง 53และตระกูลต่างๆ ของคีริยาทเยอาริมได้แก่ ตระกูลอิทไรต์ ตระกูลปุไท ตระกูลชูมัท และตระกูลมิชรา ชาวโศราห์และชาวเอชทาโอลสืบเชื้อสายมาจากตระกูลเหล่านี้

54วงศ์วานของสัลมา คือ

เบธเลเฮม ชาวเนโทฟาห์ อัทโรทเบธ โยอาบ ชาวมานาฮาทอีกครึ่งหนึ่ง และชาวโศราห์ 55รวมทั้งตระกูลต่างๆ ของบรรดาอาลักษณ์2:55 หรือของชาวโสเฟอร์ ซึ่งอาศัยที่ยาเบสได้แก่ ตระกูลทิราไธต์ ตระกูลชิเมอัท และตระกูลสุคา คนเหล่านี้เป็นชาวเคไนต์ ซึ่งสืบเชื้อสายมาจากฮัมมัทต้นตระกูลเรคาบ2:55 หรือเป็นบิดาของเบธเรคาบ