1 ዜና መዋዕል 16 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 16:1-43

1ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትም16፥1 በዚህና በቍጥር 2 ላይ በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል። በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ። 2ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ከሠዋ በኋላ፣ ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም ባረከ። 3ከዚያም ለእስራኤል ሁሉ ለወንዱም ለሴቱም አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ፣ አንዳንድ ጥፍጥፍ ተምር፣ ሙዳ ሙዳ ሥጋና አንዳንድ ጥፍጥፍ ዘቢብ ሰጠ።

4በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እንዲያገለግሉና ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ልመና፣ ምስጋናና ውዳሴ እንዲያቀርቡ ከሌዋውያን ሰዎች ሾመ፤ 5አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱ ቀጥሎ ዘካርያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ ከዚያም ይዒኤል፣ ሰሚራሞት፣ ይሒኤል፣ መቲትያ፣ ኤልያብ፣ በናያስ፣ ዖቤድኤዶም፣ ይዒኤል ተሾሙ፤ እነርሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፤ አሳፍ ደግሞ ጸናጽል የሚጸነጽል ሆኖ ተመደበ። 6እንዲሁም ካህናቱ በናያስና የሕዚኤል ዘወትር በእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ፊት መለከት እንዲነፉ ተመደቡ።

የዳዊት የምስጋና መዝሙር

16፥8-22 ተጓ ምብ – መዝ 105፥1-15

16፥23-33 ተጓ ምብ – መዝ 96፥1-13

16፥34-36 ተጓ ምብ – መዝ 106፥147-48

7በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህን የእግዚአብሔር ምስጋና መዝሙር ሰጠ፤

8ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ ስሙንም ጥሩ፤

ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤

9ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤

ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤

10በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤

እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ።

11ወደ እግዚአብሔርና ወደ ኀይሉ ተመልከቱ፤

ዘወትር ፊቱን ፈልጉ።

12ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣

ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤

13እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣

እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች።

14እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤

ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፤

15ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣

ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል።

16ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣

ለይስሐቅ የማለውን መሐላ።

17ይህንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤

ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤

18እንዲህ ሲል፣ “የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣

የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ።”

19ቍጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፣

በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፣

20ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ፣

ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ።

21ማንም እንዲጨቍናቸው አልፈቀደም፤

ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤

22እንዲህ ሲል፤ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤

በነቢያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።”

23ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤

ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።

24ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤

ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።

25እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ምስጋናውም ብዙ ነው፤

ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው።

26የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤

እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።

27በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤

ብርታትና ደስታም በማደሪያው ስፍራ።

28የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤

ክብርና ኀይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።

29ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤

መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤

በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር16፥29 ወይም፣ ከክብሩ ጋር ለእግዚአብሔር ስገዱ።

30ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤

ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም።

31ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድር ሐሤት ታድርግ፤

በአሕዛብም መካከል፤ “እግዚአብሔር ነገሠ!” ይበሉ።

32ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ይናወጥ፤

ሜዳዎችና በእርሷ ላይ ያሉ ሁሉ ሐሤት ያድርጉ።

33ያን ጊዜ የዱር ዛፎች በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል፤

በደስታ ይዘምራሉ፤

በምድረ በዳ ላይ ሊፈርድ ይመጣልና።

34ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤

ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

35“አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ ታደገን፤

ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣ በምስጋናህም እንድንከብር ሰብስበን፤

ከአሕዛብም መካከል ታደገን”

ብላችሁ ጩኹ።

36ከዘላለም እስከ ዘላለም፣

ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ “አሜን፤ እግዚአብሔር ይመስገን” አሉ።

37ዳዊትም ለእያንዳንዱ ቀን በተመደበው መሠረት፣ ዘወትር እንዲያገለግሉ አሳፍንና የሥራ ባልደረቦቹን በዚያው በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው። 38እንዲሁም ዖቤድኤዶምና ስድሳ ስምንቱ የሥራ ባልደረቦቹ አብረዋቸው እንዲያገለግሉ በዚያው ተዋቸው። የኤዶታም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ሆኑ።

39ዳዊት ካህኑን ሳዶቅንና የሥራ ባልደረቦቹን ካህናት በገባዖን ከፍተኛ ቦታ ላይ በሚገኘው በእግዚአብሔር ድንኳን ተዋቸው፤ 40የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው። 41እንዲሁም “ፍቅሩ ለዘላለም ነውና” እያሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና እንዲያቀርቡ ኤማንና ኤዶታም እንዲሁም ተመርጠውና ስማቸው ተመዝግቦ የተመደቡ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ። 42ድምፀ መለከቱንና ጸናጽሉን ለማሰማት፣ ደግሞም መንፈሳዊ መዝሙር ሲዘመር ለሚጠቀሙባቸው ሌሎች መሣሪያዎች ኀላፊዎቹ ኤማንና ኤዶታም ነበሩ፤ የኤዶታምም ልጆች በሩን እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።

43ከዚያም ሕዝቡ ተነሣ፤ እያንዳንዱም ወደየቤቱ ሄደ። ዳዊትም ቤተ ሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

King James Version

1 Chronicles 16:1-43

1So they brought the ark of God, and set it in the midst of the tent that David had pitched for it: and they offered burnt sacrifices and peace offerings before God. 2And when David had made an end of offering the burnt offerings and the peace offerings, he blessed the people in the name of the LORD. 3And he dealt to every one of Israel, both man and woman, to every one a loaf of bread, and a good piece of flesh, and a flagon of wine.

4¶ And he appointed certain of the Levites to minister before the ark of the LORD, and to record, and to thank and praise the LORD God of Israel: 5Asaph the chief, and next to him Zechariah, Jeiel, and Shemiramoth, and Jehiel, and Mattithiah, and Eliab, and Benaiah, and Obed-edom: and Jeiel with psalteries and with harps; but Asaph made a sound with cymbals;16.5 with psalteries…: Heb. with instruments of psalteries and harps 6Benaiah also and Jahaziel the priests with trumpets continually before the ark of the covenant of God.

7¶ Then on that day David delivered first this psalm to thank the LORD into the hand of Asaph and his brethren. 8Give thanks unto the LORD, call upon his name, make known his deeds among the people. 9Sing unto him, sing psalms unto him, talk ye of all his wondrous works. 10Glory ye in his holy name: let the heart of them rejoice that seek the LORD. 11Seek the LORD and his strength, seek his face continually. 12Remember his marvellous works that he hath done, his wonders, and the judgments of his mouth; 13O ye seed of Israel his servant, ye children of Jacob, his chosen ones. 14He is the LORD our God; his judgments are in all the earth. 15Be ye mindful always of his covenant; the word which he commanded to a thousand generations; 16Even of the covenant which he made with Abraham, and of his oath unto Isaac; 17And hath confirmed the same to Jacob for a law, and to Israel for an everlasting covenant, 18Saying, Unto thee will I give the land of Canaan, the lot of your inheritance;16.18 the lot: Heb. the cord 19When ye were but few, even a few, and strangers in it.16.19 few, even: Heb. men of number, etc 20And when they went from nation to nation, and from one kingdom to another people; 21He suffered no man to do them wrong: yea, he reproved kings for their sakes, 22Saying, Touch not mine anointed, and do my prophets no harm. 23Sing unto the LORD, all the earth; shew forth from day to day his salvation. 24Declare his glory among the heathen; his marvellous works among all nations. 25For great is the LORD, and greatly to be praised: he also is to be feared above all gods. 26For all the gods of the people are idols: but the LORD made the heavens. 27Glory and honour are in his presence; strength and gladness are in his place. 28Give unto the LORD, ye kindreds of the people, give unto the LORD glory and strength. 29Give unto the LORD the glory due unto his name: bring an offering, and come before him: worship the LORD in the beauty of holiness. 30Fear before him, all the earth: the world also shall be stable, that it be not moved. 31Let the heavens be glad, and let the earth rejoice: and let men say among the nations, The LORD reigneth. 32Let the sea roar, and the fulness thereof: let the fields rejoice, and all that is therein. 33Then shall the trees of the wood sing out at the presence of the LORD, because he cometh to judge the earth. 34O give thanks unto the LORD; for he is good; for his mercy endureth for ever. 35And say ye, Save us, O God of our salvation, and gather us together, and deliver us from the heathen, that we may give thanks to thy holy name, and glory in thy praise. 36Blessed be the LORD God of Israel for ever and ever. And all the people said, Amen, and praised the LORD.

37¶ So he left there before the ark of the covenant of the LORD Asaph and his brethren, to minister before the ark continually, as every day’s work required: 38And Obed-edom with their brethren, threescore and eight; Obed-edom also the son of Jeduthun and Hosah to be porters: 39And Zadok the priest, and his brethren the priests, before the tabernacle of the LORD in the high place that was at Gibeon, 40To offer burnt offerings unto the LORD upon the altar of the burnt offering continually morning and evening, and to do according to all that is written in the law of the LORD, which he commanded Israel;16.40 morning…: Heb. in the morning, and in the evening 41And with them Heman and Jeduthun, and the rest that were chosen, who were expressed by name, to give thanks to the LORD, because his mercy endureth for ever; 42And with them Heman and Jeduthun with trumpets and cymbals for those that should make a sound, and with musical instruments of God. And the sons of Jeduthun were porters.16.42 porters: Heb. for the gate 43And all the people departed every man to his house: and David returned to bless his house.