1 ዜና መዋዕል 13 – NASV & OL

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 13:1-14

የታቦቱ መመለስ

13፥1-14 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 6፥1-11

1ዳዊትም ሻለቆችና መቶ አለቆች ከሆኑት የጦር ሹማምቱ ሁሉ ጋር ተማከረ። 2ከዚያም ለመላው የእስራኤል ማኅበር እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁና የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፣ በእስራኤል ግዛት ሁሉ ለሚኖሩ በሩቅም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም በየራሳቸው ከተሞችና መሰማሪያዎች የሚኖሩ ካህናትና ሌዋውያን መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰባሰቡ እንላክባቸው። 3በሳኦል ዘመነ መንግሥት ሳንፈልገው13፥3 ወይም፣ ችላ ብለን የነበረውን የአምላካችንን ታቦት መልሰን ወደ እኛ እናምጣ”። 4ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ መላው ማኅበር ይህንኑ ለማድረግ ተስማማ።

5ስለዚህ ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ከቂርያትይዓሪም ለማምጣት ከግብፅ ወንዝ ከሺሖር ጀምሮ እስከ ለቦ ሐማት13፥5 ወይም፣ ወይም እስከ መተላለፊያው ድረስ የሰፈሩትን እስራኤላውያን ሁሉ ሰበሰበ። 6ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ በኪሩብና በኪሩብ መካከል የተቀመጠውን ስሙም በእርሱ የተጠራውን፣ የእግዚአብሔር አምላክን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓሪም ወደተባለችው ወደ ባኣላ ሄዱ።

7የእግዚአብሔርንም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በአዲስ ሠረገላ ላይ አድርገው አመጡት፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም ዖዛና አሒዮ ነበሩ። 8ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሆነው በቅኔና በበገና፣ በመሰንቆና በከበሮ፣ በጸናጽልና በመለከት በሙሉ ኀይላቸው በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።

9ወደ ኪዶን ዐውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ አደናቅፏቸው ስለ ነበር፣ ዖዛ ታቦቱን ለመደገፍ እጁን ዘረጋ። 10ታቦቱን በእጁ ስለ ነካ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።

11የእግዚአብሔር ቍጣ ዖዛን በድንገት ስለ ቀሠፈው ዳዊት ዐዘነ፤ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ የዖዛ ስብራት13፥11 ወይም፣ ፔሬዝ ዖዛ ተብሎ ይጠራል።

12ዳዊት በዚያን ዕለት እግዚአብሔርን ስለ ፈራ፣ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት ማምጣት እችላለሁ?” አለ። 13ስለዚህ ታቦቱን ወደ ዳዊት ከተማ በመውሰድ ፈንታ የጋት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ወሰደው። 14የእግዚአብሔርም ታቦት በአቢዳራ ቤት ከቤተ ሰቡ ጋር ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም ቤተ ሰቡንና ያለውንም ሁሉ ባረከ።

O Livro

1 Crónicas 13:1-14

A mudança da arca

(2 Sm 6.1-11)

1Depois de ter consultado todos os seus chefes e comandantes militares, 2David dirigiu-se à assembleia de Israel da seguinte maneira: “Visto que vos parece bem que eu seja vosso rei, e visto que temos a aprovação do Senhor, nosso Deus, mandemos uma mensagem aos nossos irmãos em toda a terra de Israel, incluindo os sacerdotes e os levitas, convidando-os a juntar-se a nós. 3Tornemos também a trazer para junto de nós a arca de Deus, porque tem ficado esquecida, desde que Saul se tornou rei.”

4Houve consenso geral e toda a gente esteve de acordo com a iniciativa. 5David convocou todo o povo de Israel, desde Sior, na fronteira do Egito, até à entrada de Hamate, para que estivesse presente quando a arca de Deus fosse trazida de Quiriate-Jearim.

6Então David e todo o Israel foram a Baalá, ou seja Quiriate-Jearim, em Judá, para trazer a arca do Senhor Deus, cujo trono está acima dos querubins. 7Foram-na buscar a casa de Abinadabe, num carro novo. Uzá e Aiô conduziam o carro. 8David e todo o povo dançaram perante Deus, com grande entusiasmo, acompanhados de cânticos, harpas, liras, tamborins, címbalos e cornetas.

9Quando chegaram à eira de Quidom, os bois tropeçaram e Uzá estendeu a mão para segurar a arca. 10A ira do Senhor acendeu-se contra ele e matou-o, por ter tocado na arca. E ficou ali estendido diante de Deus. 11David ficou muito contristado devido àquilo que o Senhor fizera e deu àquele lugar o nome Perez-Uzá (brecha de Uzá). Ainda hoje é assim chamado.

12O rei ficou com medo de Deus e interrogava-se: “Como hei de trazer a arca de Deus para junto de mim?” 13Finalmente, decidiu-se por trazê-la até à casa de Obede-Edom, originário de Gate, em lugar de a levar para a sua própria casa, na Cidade de David. 14A arca permaneceu ali com a família de Obede-Edom durante três meses. E o Senhor abençoou-o, a ele e à sua casa.