1 ነገሥት 7 – NASV & NSP

New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 7:1-51

ሰሎሞን ቤተ መንግሥቱን ሠራ

1ሰሎሞን የራሱን ቤተ መንግሥት ሠርቶ ለመጨረስ ዐሥራ ሦስት ዓመት ፈጀበት። 2የሊባኖስ ዱር የተባለ ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ይህም ርዝመቱ7፥2 ርዝመቱ 46 ሜትር፣ ወርዱ 23 ሜትር እንዲሁም ቁመቱ 13.5 ሜትር ያህል ነው። መቶ ክንድ፣ ወርዱ አምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ ሲሆን፣ በአራት ረድፍ የቆሙ የዝግባ ምሰሶዎች ደግፈው የያዟቸው አግዳሚ የዝግባ ተሸካሚዎች ነበሩት። 3ቤቱ ከምሰሶዎቹ ላይ ያረፉ አግዳሚ ተሸካሚዎች አሉት፤ በእያንዳንዱ ዐምድ ላይ ዐሥራ አምስት፣ በድምሩ አርባ አምስት ተሸጋጋሪዎች ሲኖሩ፣ ከእነዚህም ተሸጋጋሪዎች በላይ ከዝግባ የተሠራ የጣሪያ ክዳን ነበር። 4መስኮቶቹም ከፍ ብለው የተሠሩ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ ነበሩ። 5በሮቹ በሙሉ ባለ አራት ማእዘን መቃኖች ያሏቸው፣ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ7፥5 በዕብራይስጥ የክፍሉ መልእክት በትክክል አይታወቅም። ነበሩ።

6ሰሎሞን፣ “ባለ ብዙ ምሰሶ አዳራሽ” የተባለ ቤት ሠራ፤ የዚህም ርዝመቱ አምሳ ክንድ፣ ወርዱ ሠላሳ ክንድ፣7፥6 ርዝመቱ 23 ሜትር፣ ወርዱ 13.5 ሜትር ያህል ነው። ነበር፤ በስተ ፊት በኩልም ጣራ ያለውና በአዕማድ የተደገፈ መመላለሻ ነበረው።

7ዳኝነት የሚያይበትንም የዙፋን ችሎት አዳራሽ ሠራ፤ ይኸውም የፍትሕ አዳራሽ የተባለው ነው፤ ይህንም ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው7፥7 ቩልጌትና የሱርስቱ ትርጕም ከዚህ ጋር ሲስማሙ ዕብራይስጡ ግን፣ ወለል ይላል። ድረስ በዝግባ ሳንቃ ሸፈነው። 8ከአዳራሹ በስተ ጀርባ ባለው አደባባይ መኖሪያው እንዲሆን የተሠራው ቤተ መንግሥትም የዚሁ ተመሳሳይ ነበር። ሰሎሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ይህንኑ ቤተ መንግሥት የመሰለ አዳራሽ ሠራ።

9ከውጭ አንሥቶ እስከ ትልቁ አደባባይ፣ ከመሠረቱ አንሥቶ እስከ ድምድማቱ ያለው የሕንጻ ሥራ በሙሉ፣ በውስጥም በውጭም በልክ በልኩ በተቈረጠና አምሮ በተስተካከለ ምርጥ ድንጋይ የተሠራ ነበር። 10መሠረቱም ዐሥርና7፥10 4.5 ሜትር ያህል ነው። ስምንት ክንድ7፥10 3.6 ሜትር ያህል ነው። ርዝመት ባላቸውና ምርጥ በሆኑ ታላላቅ ድንጋዮች የተሠራ ነበር። 11በላዩም ላይ ምርጥ የሆኑ፣ በልክ በልኩ የተቈረጡ ድንጋዮችና የዝግባ ሳንቃዎች ነበሩ። 12የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጠኛ አደባባይ ከመመላለሻ በረንዳው ጭምር እንደ ትልቁ አደባባይ አምሮ በተጠረበ ሦስት ረድፍ ድንጋይና ተስተካክሎ በተከረከመ በአንድ ረድፍ የዝግባ ሳንቃ የታጠረ ነበር።

የቤተ መቅደሱ ዕቃዎች

7፥23-26 ተጓ ምብ – 2ዜና 4፥2-5

7፥3840-51 ተጓ ምብ – 2ዜና 4፥6፡10–5፥1

13ንጉሥ ሰሎሞንም መልእክተኛ ልኮ ኪራም7፥13 በዚህ ስፍራ እንዲሁም በ40 እና 45 ላይ ኪራም የሚለው ዕብራይስጡ ሂራም ይለዋል። የተባለውን ሰው ከጢሮስ አስመጣ፤ 14የኪራም እናት ከንፍታሌም ነገድ ስትሆን፣ እርሷም መበለት ነበረች፤ አባቱ የጢሮስ ሰው ሲሆን፣ የናስ ሥራ ባለሙያ ነበር። ኪራም በማናቸውም የናስ ሥራ ጥበብን፣ ማስተዋልንና ዕውቀትን የተሞላ ሰው ነበር፤ እርሱም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን መጥቶ የተመደበለትን ሥራ ሁሉ አከናወነ።

15ኪራም የእያንዳንዱ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ ዙሪያው ዐሥራ ሁለት ክንድ7፥15 ቁመቱ 8.1 ሜትር፣ ዙሪያው 5.4 ሜትር ያህል ነው። የሆነ፣ ሁለት የናስ ምሰሶዎች ሠራ። 16እንዲሁም በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ የሚሆኑ፣ ሁለት ጕልላት ከቀለጠ ናስ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ7፥16 በዚህና በ23 ላይ 2.3 ሜትር ያህል ነው። ነበር። 17በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ ላሉት ጕልላቶችም ጌጥ እንዲሆኑ፣ ለእያንዳንዳቸው ሰባት የመረብ ሰንሰለት አበጀ፤ 18ደግሞም በምሰሶዎቹ ላይ ያሉትን ጕልላቶች ለማስጌጥ የእያንዳንዱን መረብ ዙሪያ የሚከብቡ ሮማኖች በሁለት ረድፍ7፥18 ሁለት የዕብራይስጥ ቅጆችና የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋር ሲስማሙ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ በሁለት ረድፍ አዕማዶች ሥራ ይላሉ። ሠራ፤ ለሁለቱም ጕልላቶች7፥18 ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆችና የሱርስቱ ትርጕም ከዚህ ጋር ሲስማሙ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ሮማኖች ይላሉ። ያደረገው ተመሳሳይ ነበር። 19በመመላለሻው ምሰሶዎች ዐናት ላይ ያሉት ጕልላቶች ቁመታቸው አራት ክንድ7፥19 በዚህና በ38 ላይ 1.8 ሜትር ይላል። ሲሆን፣ የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበራቸው። 20በሁለቱም የምሰሶ ጕልላቶችና ከመርበቡ ቀጥሎ ባለው የክብ ቅርጽ ላይ ዙሪያውን በሙሉ ሁለት መቶ ሮማኖች በተርታ ነበሩ። 21ምሰሶዎቹንም በቤተ መቅደሱ መመላለሻ ላይ አቆመ፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ምሰሶ ያኪን፣7፥21 ምናልባት አነጸ ማለት ሊሆን ይችላል። በስተ ሰሜን በኩል ያለውንም ቦዔዝ7፥21 ምናልባት በእርሱ ዘንድ ጥንካሬ አለ ማለት ሊሆን ይችላል ብሎ ጠራው። 22ዐናቱ ላይ ያሉት ጕልላቶች የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበራቸው። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ሁኔታ ተፈጸመ።

23ቅርጹ ክብ፣ ስፋቱ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፣7፥23 4.5 ሜትር ያህል ነው። ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ ክብ ገንዳ ከቀለጠ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ7፥23 13.5 ሜትር ያህል ነው። ሆነ። 24ከከንፈሩም ዝቅ ብሎ፣ በእያንዳንዱ ክንድ ላይ እንደ ቅል ያሉ ዐሥር ቅርጾች ዙሪያውን በሁለት ረድፍ ከብበውታል፤ እነዚህም ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ተሠርተው ነበር።

25ገንዳውም፣ ሦስቱ ፊታቸውን ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ባዞሩ የዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስሎች ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ገንዳው በላያቸው ሆኖ የሁሉም የኋላ አካል በመካከል ላይ የገጠመ ነበር። 26የገንዳው ውፍረት አንድ ጋት7፥26 8 ሴንቲ ሜትር ያህል ነው። ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ እንደ አበባ ቅርጽ ሆኖ፣ የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም አርባ ሁለት ሺሕ ሊትር7፥26 44 ኪሎ ሊትር ያህል ነው። የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ይህን ዐረፍተ ነገር አይጨምርም። ያህል ውሃ የሚይዝ ነበር።

27እንዲሁም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ዐሥር ባለ መንኰራኵር የዕቃ ማስቀመጫዎች ከመዳብ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ርዝመት አራት ክንድ፣ ወርድ አራት ክንድ፣ ቁመትም ሦስት ክንድ7፥27 ርዝመቱና ወርዱ 1.8 ሜትር ያህል ሲሆን ቁመቱ 1.3 ሜትር ያህል ነው። ነበር። 28የዕቃ ማስቀመጫዎቹ የተሠሩት እንደዚህ ነው፤ እነዚህም ቀጥ ብለው ከቆሙ ደጋፊዎች ጋር የተያያዙ ባለ አራት ማእዘን ጠፍጣፋ ናሶች ነበሯቸው። 29ዳርና ዳር ባሉት ድጋፎች መካከል በሚገኙት ጠፍጣፋ ናሶች ላይ የአንበሶችን፣ የኮርማዎችንና የኪሩቤልን ምስል አደረገ፤ በድጋፎቹም ላይ እንደዚሁ አደረገ። ከአንበሶቹና ከኮርማዎቹ በላይና በታች በኩል ደግሞ የአበባ ጕንጕን የሚመስሉ ተቀጥቅጠው የተሠሩ ቅርጾች ነበሩ። 30እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት የናስ መንኰራኵርና መንኰራኵሮቹ የሚሽከረከሩባቸው የናስ ወስከምቶች እንዲሁም እያንዳንዳቸው በአራቱም ማእዘን ገጽ ላይ የአበባ ጕንጕን ቀልጦ የተሠራባቸው የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበረው። 31በዕቃ ማስቀመጫዎቹም ውስጥ ጥልቀቱ አንድ ክንድ7፥31 0.5 ሜትር ያህል ነው። የሆነ ባለ ክብ ክፍተት ነበር፤ ይህም ክፍተት ድቡልቡል ሆኖ ከታች ከመቆሚያው በኩል ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል7፥31 በዚህና በ32 ላይ 0.7 ሜትር ያህል ነው። ወርድ ሲኖረው፣ በክፍተቱም ዙሪያ ቅርጾች ነበሩ፤ ክፈፎቹ ግን ባለ አራት ማእዘን እንጂ ክብ አልነበሩም። 32አራቱ መንኰራኵሮች በዕቃ ማስቀመጫው ጠፍጣፋ ናስ ሥር ሲሆኑ፣ የመንኰራኵሮቹ ወስከምቶች ደግሞ ከዕቃ ማስቀመጫዎቹ ጋር የተያያዙ ነበሩ፤ የእያንዳንዱም መንኰራኵር ስፋት አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 33መንኰራኵሮቹ የሠረገላ መንኰራኵር መሰል ሲሆኑ፣ ወስከምቶቹ የመንኰራኵሮቹ ክፈፎችና ዐቃፊዎቻቸው እንዲሁም ወስከምቶቹ የሚገቡባቸው ቧምቧዎች በሙሉ ከቀለጠ ብረት የተሠሩ ነበሩ።

34እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ወጣ ያለ እጀታ ነበረው። 35በዕቃ ማስቀመጫው ጫፍ ላይ ግማሽ ክንድ7፥35 0.2 ሜትር ያህል ነው። የሆነ ዙሪያ ክብ ነበረበት፤ ድጋፎቹና ጠፍጣፋ ናሶቹ ከዕቃ ማስቀመጫው ዐናት ጋር የተያያዙ ነበሩ። 36እርሱም በድጋፎቹና በጠፍጣፋ ናሶቹ ላይ ባለው ቦታ ሁሉ፣ ዙሪያውን የአበባ ጕንጕን እያደረገ ኪሩቤልን፣ አንበሶችንና የዘንባባ ዛፎችን ቀረጸ። 37ዐሥሩም የዕቃ ተሸካሚዎች የተሠሩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ሁሉም ከአንድ ቅርጽ ቀልጠው የወጡ ስለሆነ፣ በመጠንና በቅርጽ ፍጹም ተመሳሳይ ነበሩ።

38ከዚያም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ የሚሆን፣ እያንዳንዱ ስምንት መቶ ሰማንያ ሊትር የሚይዝ ዐሥር የናስ መታጠቢያ ገንዳ ሠራ፤ ስፋቱም አራት ክንድ ነበር። 39ከዕቃ ማስቀመጫዎቹም አምስቱን ከመቅደሱ በስተ ደቡብ፣ አምስቱን በስተ ሰሜን በኩል አኖረ፤ ገንዳውንም ከቤተ መቅደሱ በደቡብ ምሥራቅ ጫፍ ላይ በስተ ደቡብ አኖረው። 40እንዲሁም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችንና ድስቶችን ሠራ።

ኪራምም በዚህ ሁኔታ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ እንደሚከተለው ፈጸመ፤

41ሁለቱን ምሰሶዎች፣

በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ በክብ ቅርጽ የተሠሩ ሁለት ጕልላቶችን፤

በምሰሶዎቹ ላይ ያሉትን በክብ ቅርጽ የተሠሩትን ሁለት ጕልላት ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤

42በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ ያሉትንና ክብ ቅርጽ የያዙትን፣ በሁለት ረድፍ የተቀረጹትን መረቦች፣ የሚያስጌጡትን አራት መቶ ሮማኖች፤

43ዐሥሩን የዕቃ ማስቀመጫዎች፣ ከዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎቻቸው ጋር፤

44ገንዳውንና በሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች፤

45ድስቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን።

ኪራም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለና ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር። 46ንጉሡም እነዚህን በማቅለጥ በሸክላ ቅርጽ ውስጥ ፈስሰው እንዲወጡ ያደረገው በሱኮትና በጻርታን መካከል ባለው በዮርዳኖስ ሸለቆ ነበር። 47ሰሎሞን ከብዛታቸው የተነሣ እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች እንዲመዘኑ አላደረገም፣ ስለዚህም የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበረ አልታወቀም።

48እንዲሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት እንዲውሉ ከዚህ የሚከተሉትን ዕቃዎች ሁሉ ሠራ፤

የወርቅ መሠዊያን፣

ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥበትን የወርቅ ጠረጴዛ፤

49በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በቀኝ፣ አምስቱ በግራ የሚቀመጡ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞችን፣ ከወርቅ የተሠሩ አበቦችን፣ የመብራት ቀንዲሎችንና መቈስቈሻዎችን፤

50የንጹሕ ወርቅ ሳሕኖችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችንና ጭልፋዎችን፣

የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።

51ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር የለየውን ብሩንና ወርቁን እንዲሁም ዕቃውን አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አኖረ።

New Serbian Translation

1. Књига о царевима 7:1-51

Соломонов двор и остале зграде

1Соломон је зидао себи двор тринаест година и довршио га. 2Сазидао је и дом у Ливанској шуми, стотину лаката дуг, педесет лаката широк и тридесет лаката7,2 Око 50 m дуг и широк и око 15 m висок. висок, на четири кедрова стуба, с кедровим гредама изнад стубова. 3Дом је био покривен кедровим дрветом преко греда, које су биле на четрдесет пет стубова, по петнаест у сваком реду. 4Било је три реда прозора, један наспрам другог у три реда. 5Сва врата и прагови су били на четири угла, с прозорима који су стајали један наспрам другог у три реда.

6Начинио је и трем од стубова, педесет лаката дуг и тридесет лаката7,6 Око 25 m дуг и 15 m широк. широк. Трем је био с предње стране а испред њега су били стубови с надстрешницом.

7Затим је начинио престони трем, то јест, судски трем где је делио правду; био је обложен кедровином од пода до крова. 8У његовој кући где је пребивао, био је други трем иза оног трема. Он је направио дом као тај трем за фараонову ћерку којом се оженио.

9Све ово је било од скупоценог камена, тесаног на меру и сеченог тестером, и изнутра и споља, од пода до крова, и споља до великог дворишта. 10Темељ је био од великог и скупоценог камења, величине од осам и десет лаката7,10 Око 4 m и 5 m.. 11Одозго је било скупоцено камење тесано по мери, и кедрове даске. 12Велики трем је имао унаоколо три реда тесаног камења и један ред кедрових балвана, као унутрашње двориште Дома Господњег и храмски трем.

Опрема Дома

13Цар Соломон је послао поруку Хираму из Тира и позвао га. 14Он је био син једне удовице из Нефталимовог племена, коме је отац био из Тира. Он је био уметник бронзарски. Хирам је био веома вешт и уман, па је свашта умео да направи од бронзе. Он је дошао к цару Соломону и урадио му сав посао.

15Салио је два стуба од бронзе; један стуб је био осамнаест лаката висок, а дванаест лаката7,15 Око 9 m у висину и 6 m у обиму. му је био обим унаоколо. Други стуб је био једнак првом. 16Затим је начинио два оглавља саливена од бронзе да се ставе одозго на стубове. Једно оглавље је било високо пет лаката, а друго оглавље је такође било високо пет лаката7,16 Око 2,5 m.. 17На оглављима, која су била на врху стубова, начинио је преплетене плетенице и врпце у облику ланаца; седам на једном оглављу и седам на другом оглављу. 18На та два оглавља је направио и два реда нарова око једне плетенице да покривају оглавље на врху стубова; исто је направио и на другом оглављу. 19На та два оглавља на врху стубова у трему, били су направљени љиљани од четири лакта7,19 Око 2 m.. 20На оглављима оба стуба, изнад и испод плетеница, било је две стотине нарова у два реда свуда око оба оглавља.

21Такве стубове је поставио на трему Дома; десни стуб је назвао Јакин, а леви стуб је назвао Воаз. 22На врху стубова били су вешто израђени љиљани. Тако је рад на стубовима био завршен.

23Затим је израдио море од искованог метала. Било је сасвим округло и имало је десет лаката од једног краја до другог; било је пет лаката високо, а у обиму је било тридесет лаката7,23 Око 5 m од једног до другог краја, око 2,5 m у висину а у обиму око 15 m., мерено ужетом. 24Испод руба су му били украси у облику цветних латица свуда око њега, по десет на сваки лакат, којима је било опточено море унаоколо; два је реда латица било саливено с њим.

25Море је стајало на дванаест волова; три су гледала на север, три су гледала на запад, три су гледала на југ, а три су гледала на исток. Море је стајало на њима одозго, а њихова задња страна је била унутра. 26Дебљина му је била један педаљ7,26 Око 23 cm., а руб му је био као руб чаше, као цвет љиљана, и примало је две хиљаде вата7,26 Око 40.000 l..

27Затим је начинио десет подножја од бронзе; свако подножје је било по четири лакта у дужину, четири лакта у ширину, и три лакта7,27 Око 2 m у дужину и ширину и око 1,5 m у висину. у висину. 28А подножја су била овако направљена: оквири су били причвршћени између углова. 29На оквирима мећу угловима били су лавови, волови и херувими, а одозго на угловима су били стубићи. Испод и изнад лавова и волова био је искован венац. 30Испод сваког подножја била су по четири бронзана точка с бронзаним осовинама, а на четири угла били су држачи. Држачи под сваком умиваоницом били су сливени са сваким венцем. 31Отвор унутар подножја, био је један педаљ7,31 Око 23 cm.. Отвор је био округао, а са својим постољем био је педаљ и по7,31 Око 34,5 cm.. На отвору су били урезани украси; али оплате нису биле округле, него четвртасте.

32Четири точка су била испод оплата, а осовине точкова су биле причвршћене на постоље. Висина сваког точка била је лакат и по7,32 Омо 75 cm.. 33Точкови су били направљени као точкови за кола; њихове осовине, главњаче, наплаци и паоци, све је било ливено. 34Била су четири држача на четири угла; држачи су били спојени с постољем. 35На врху постоља био је округли ремен пола лакта7,35 Око 25 cm. висине. Држачи и оплате су били причвршћени за врх постоља. 36На његовим угловима и оплатама изрезао је херувиме, лавове и палме, где год је било места, и венце свуда унаоколо. 37На тај је начин начинио десет подножја; сви су били једнако саливени, једнаке мере и облика.

38Начинио је и десет умиваоница од бронзе, које су захватале по четрдесет вата7,38 Између 1.000–1.600 l, зависно од начина рачунања древних мера.; свака умиваоница је имала обим од четири лакта7,38 Око 2 m., и свака је умиваоница захватала по четрдесет вата. По једна умиваоница је стајала на сваком од десет подножја. 39Наместио је пет подножја на десној страни Дома, и пет на левој страни Дома. Море је поставио на десну страну, према југоистоку.

40Хирам је направио и лонце, лопатице и котлиће. Тако је Хирам довршио сав посао који је радио на Дому Господњем за цара Соломона:

41Два стуба и два округла оглавља на врху два стуба, и две плетенице да покривају та два оглавља на врху два стуба;

42четири стотине нарова на две плетенице; два реда нарова на свакој плетеници, да покривају два округла оглавља на врху стубова;

43десет подножја и десет умиваоница на њима;

44једно море и дванаест волова испод мора;

45лонце, лопатице и котлиће. Сви судови које је Хирам направио цару Соломону за Дом Господњи, били су од углачане бронзе.

46Цар их је лио у глиненим калупима, у долини Јордана, између Сокота и Сартана. 47Соломон није мерио све судове, јер их је било много; није се тражио извештај о тежини бронзе.

48Соломон је направио и све остало посуђе које је било у Дому Господњем:

златни жртвеник,

златни сто на коме је био принесени хлеб,

49свећњаке од чистог злата, пет с десне стране и пет с леве стране испред Светиње над светињама;

латице, светиљке и машице од злата;

50чаше, усекаче и котлиће; кадионице и тепсије од чистог злата;

златне преворнице за врата унутрашњег Дома – за Светињу над светињама и за врата велике дворане.

51Тако је био довршен сав посао који је цар Соломон урадио за Дом Господњи. Затим је унео у ризницу Дома Господњег ствари које је његов отац Давид посветио: сребро, злато, и посуђе.