1 ነገሥት 3 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 3:1-28

ሰሎሞን ጥበብን ከእግዚአብሔር መለመኑ

3፥4-15 ተጓ ምብ – 2ዜና 1፥2-13

1ሰሎሞን የግብፅ ንጉሥ የፈርዖን ወዳጅ ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ። እርሱም ቤተ መንግሥቱን፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የኢየሩሳሌምን ዙሪያ ቅጥር ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አስቀመጣት።

2በዚያን ጊዜ ለእግዚአብሔር ስም ገና ቤተ መቅደስ ስላልተሠራ፣ ሕዝቡ አሁንም መሥዋዕት የሚያቀርበው በማምለኪያ ኰረብታ ላይ ነበር። 3ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱ በዳዊት ሥርዐትም ይሄድ ነበር፤ ይሁን እንጂ፣ በኰረብታዎች ላይ መሥዋዕት ይሠዋና ዕጣን ያጥን ነበር።

4ከሁሉ የሚበልጠው የማምለኪያ ኰረብታ ገባዖን ስለ ነበረ፣ ንጉሡ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ። ሰሎሞን በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺሕ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ። 5በገባዖንም እግዚአብሔር ለሰሎሞን ሌሊት በሕልም ተገለጠለት፤ አምላክም፣ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ሁሉ ለምን” አለው።

6ሰሎሞን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አባቴ ዳዊት በእውነት፣ በጽድቅና በቅን ልቦና በፊትህ ስለ ተመላለሰ፣ ለባሪያህ ታላቅ ቸርነትን አሳይተኸዋል፤ ይህ ታላቅ ቸርነት እንዲቀጥል በማድረግ ዛሬም በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ ሰጥተኸዋል።

7እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ባሪያህ በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቼ እንድነግሥ አድርገሃል፤ እኔ ግን ገና ትንሽ ልጅ ስለሆንሁ፣ መውጫና መግቢያዬን አላውቅም። 8ባሪያህ አንተ በመረጥኸው ሕዝብ፣ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ታላቅ ሕዝብ መካከል ይገኛል። 9ስለዚህ መልካሙንና ክፉውን በመለየት ሕዝብህን ማስተዳደር እንዲችል ለባሪያህ አስተዋይ ልብ ስጠው፤ አለዚያማ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊያስተዳድር ይችላል?”

10ሰሎሞን ይህን በመለመኑ ጌታ ደስ አለው፤ 11ስለዚህ እንዲህ አለው፤ “ለራስህ ረዥም ዕድሜ፣ ብልጽግና እንድታገኝ ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ ሳይሆን፣ በትክክል ማስተዳደር እንድትችል ማስተዋልን ስለ ጠየቅህ፣ 12ይህንኑ አደርግልሃለሁ፤ ከአንተ በፊት ማንም ያልነበረውን፣ ከአንተም በኋላ ማንም የማያገኘውን ጥበብና አስተዋይ ልቡና እሰጥሃለሁ፤ 13ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅኸውን ብልጽግናና ክብር እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በሕይወት ዘመንህ የሚተካከልህ ማንም ንጉሥ እንዳይኖር ነው። 14አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድ፣ ሥርዐቴንና ትእዛዜን ብትጠብቅ ዕድሜህን አረዝመዋለሁ።” 15ሰሎሞንም ከእንቅልፉ ነቃ፤ እነሆ ሕልም መሆኑን ተረዳ።

ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ፣ በጌታ ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት3፥15 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል። አቀረበ፤ ለሹማምቱም ሁሉ ግብዣ አደረገ።

ጥበብን የተሞላ ፍትሕ

16በዚህን ጊዜ ሁለት ዝሙት ዐዳሪዎች ወደ ንጉሡ መጥተው ከፊቱ ቆሙ። 17ከእነርሱም አንዲቱ እንዲህ አለች፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት አብረን እንኖራለን፤ አብራኝ እያለችም እኔ ልጅ ወለድሁ፤ 18እኔ ከወለድሁ ከሦስት ቀን በኋላም፣ ይህች ሴት ወለደች፤ የነበርነው እኛ ብቻ ነን፤ ከሁለታችን በቀር በዚያ ቤት ማንም አልነበረም።

19“የዚህች ሴት ሕፃን ልጅ ስለ ተኛችበት ሌሊት ሞተ። 20ስለዚህም በእኩለ ሌሊት ተነሥታ፣ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ ሳለሁ ልጄን ከአጠገቤ ወሰደችው፤ ከዚያም የእኔን ልጅ ራሷ ታቅፋ፣ የሞተ ልጇን አምጥታ በዕቅፌ አደረገችው። 21በማግስቱም ልጄን ላጠባ ስነሣ እነሆ ሞቷል፤ ነገር ግን በማለዳ ብርሃን ትክ ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድሁት ልጅ አለመሆኑን ተገነዘብሁ።”

22ሌላዪቱም ሴት፣ “ነገሩ አንቺ እንደምትዪው አይደለም፤ የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለውም የእኔ ነው” አለች።

የመጀመሪያዋ ሴት ግን አጠንክራ፣ “አይደለም! የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው” አለች፤ በዚህ ሁኔታም በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።

23ንጉሡም፣ “ይህችኛዪቱ፣ ‘የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው፣ የአንቺ የሞተው ነው’ ትላለች፤ ያችኛዪቱ ደግሞ፣ ‘አይደለም የአንቺ ልጅ ሞቷል፣ በሕይወት ያለው የእኔ ነው’ ትላለች” አለ።

24ከዚያም ንጉሡ፣ “እንግዲያውስ ሰይፍ አምጡልኝ” አለ፤ ለንጉሡም ሰይፍ አመጡለት። 25በዚህ ጊዜ ንጉሡ፣ “በሉ በሕይወት ያለውን ልጅ ከሁለት ክፈሉና ለአንዷ ግማሹን፣ ለሌላዪቱም ግማሹን ስጡ” ብሎ አዘዘ።

26በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ እጅግ ስለ ራራች ንጉሡን፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለእርሷ ስጣት፤ አትግደለው” አለች።

ሌላዪቱ ግን፣ “ለእኔም ሆነ ለአንቺ አይሰጥም፤ ሁለት ላይ ይከፈል!” አለች።

27ከዚህ በኋላ ንጉሡ፣ “በሉ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለመጀመሪያዪቱ ሴት ስጧት፤ አትግደሉት፤ እናቱ እርሷ ናት” አለ።

28እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ የሰጠውን ፍርድ ሲሰሙ ፈሩት፤ ፍትሕ ለመስጠት የአምላክን ጥበብ የታደለ መሆኑን አይተዋልና።

Thai New Contemporary Bible

1พงศ์กษัตริย์ 3:1-28

โซโลมอนทูลขอสติปัญญา

(2พศด.1:2-13)

1โซโลมอนทรงเจริญพระราชไมตรีกับฟาโรห์กษัตริย์แห่งอียิปต์และอภิเษกกับพระธิดาองค์หนึ่งของฟาโรห์ พระองค์ทรงพาพระนางมาประทับในเมืองดาวิดจนกระทั่งการก่อสร้างพระราชวัง พระวิหารขององค์พระผู้เป็นเจ้า และกำแพงรอบกรุงเยรูซาเล็มเสร็จเรียบร้อย 2แต่ว่าประชาชนยังคงถวายเครื่องบูชาที่สถานบูชาบนที่สูงทั้งหลายเพราะพระวิหารเพื่อพระนามพระยาห์เวห์ยังไม่ได้สร้างขึ้น 3โซโลมอนทรงรักองค์พระผู้เป็นเจ้า และปฏิบัติตามกฎเกณฑ์ของดาวิดราชบิดา เว้นแต่ยังทรงถวายเครื่องบูชาและเผาเครื่องหอมที่สถานบูชาบนที่สูงทั้งหลาย

4พระองค์เสด็จไปยังกิเบโอนเพื่อถวายเครื่องบูชา เพราะที่นั่นเป็นสถานบูชาบนที่สูงที่สำคัญที่สุด ทรงถวายสัตว์หนึ่งพันตัวเป็นเครื่องเผาบูชาบนแท่นนั้น 5องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงปรากฏแก่โซโลมอนที่กิเบโอนในความฝันยามค่ำคืน พระเจ้าตรัสว่า “จงขอสิ่งที่เจ้าต้องการเถิด แล้วเราจะให้เจ้า”

6โซโลมอนกราบทูลว่า “พระองค์ได้ทรงสำแดงพระกรุณาอย่างยิ่งต่อผู้รับใช้ของพระองค์คือดาวิดเสด็จพ่อของข้าพระองค์ เนื่องจากเสด็จพ่อทรงซื่อสัตย์ต่อพระองค์ มีใจชอบธรรมและซื่อตรง และพระองค์ยังคงสำแดงพระกรุณาเดียวกันนี้ต่อเสด็จพ่อสืบมาจนถึงวันนี้ โดยให้บุตรคนหนึ่งครองราชบัลลังก์

7“ข้าแต่พระยาห์เวห์พระเจ้าของข้าพระองค์ บัดนี้ทรงโปรดให้ผู้รับใช้ของพระองค์ได้เป็นกษัตริย์สืบต่อจากเสด็จพ่อดาวิด แต่ข้าพระองค์ยังเป็นเพียงเด็กเล็กๆ คนหนึ่ง ไม่รู้วิธีปฏิบัติภาระหน้าที่ 8ผู้รับใช้ของพระองค์อยู่ท่ามกลางประชากรที่ทรงเลือกสรร ซึ่งเป็นชนชาติที่ยิ่งใหญ่และมากมายเหลือคณานับ 9ฉะนั้นขอทรงโปรดให้ผู้รับใช้ของพระองค์มีความคิดฉลาดหลักแหลม เพื่อจะปกครองประชากรของพระองค์ และรู้จักแยกแยะผิดชอบชั่วดี เพราะใครเล่าจะสามารถปกครองชนชาติที่ยิ่งใหญ่ของพระองค์นี้ได้?”

10องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงพอพระทัยที่โซโลมอนทูลขอเช่นนี้ 11ดังนั้นพระเจ้าจึงตรัสกับโซโลมอนว่า “เนื่องจากเจ้าขออย่างนี้ ไม่ได้ขอชีวิตยืนยาว หรือทรัพย์สมบัติสำหรับตัวเอง หรือชีวิตศัตรูของเจ้า แต่ขอให้มีความฉลาดหลักแหลมเพื่อผดุงความยุติธรรม 12เราจะให้ตามที่เจ้าขอ เราจะให้เจ้ามีสติปัญญาและความฉลาดหลัดแหลมอย่างที่ไม่เคยมี และจะไม่มีใครเสมอเหมือนเจ้า 13ยิ่งกว่านั้นเราจะให้สิ่งที่เจ้าไม่ได้ขออีกด้วย คือทรัพย์สมบัติและเกียรติ เพื่อที่จะไม่มีกษัตริย์องค์ใดเสมอเหมือนตลอดชีวิตของเจ้า 14และหากเจ้าดำเนินในทางของเรา ปฏิบัติตามคำสั่งและกฎเกณฑ์ของเราเหมือนดาวิดบิดาของเจ้า เราจะให้เจ้ามีชีวิตยืนยาว” 15แล้วโซโลมอนก็ตื่นบรรทมและตระหนักว่าได้ทรงฝันไป

พระองค์เสด็จกลับมายังกรุงเยรูซาเล็ม ทรงยืนอยู่หน้าหีบพันธสัญญาของพระเจ้า ถวายเครื่องเผาบูชาและเครื่องสันติบูชา จากนั้นทรงจัดงานเลี้ยงให้ข้าราชสำนักทั้งปวง

การตัดสินคดีอย่างมีปัญญา

16มีหญิงโสเภณีสองคนมาเข้าเฝ้ากษัตริย์โซโลมอน 17คนหนึ่งทูลว่า “ข้าแต่กษัตริย์ หม่อมฉันกับหญิงคนนี้อาศัยอยู่ในบ้านเดียวกัน นางอยู่ด้วยเมื่อหม่อมฉันคลอดลูก 18พอลูกอายุได้สามวัน ผู้หญิงคนนี้ก็คลอดลูกด้วยเช่นกัน มีเพียงเราสองคนอยู่ในบ้าน ไม่มีคนอื่น

19“ลูกชายของหญิงคนนี้ตายไปตอนกลางคืนเพราะถูกนางนอนทับ 20แล้วนางตื่นขึ้นมากลางดึก ขณะที่หม่อมฉันหลับอยู่ นางเอาลูกชายของหม่อมฉันออกไปจากข้างตัว ไปนอนแนบอก และเอาลูกของนางที่ตายแล้วมาไว้แนบอกของหม่อมฉัน 21เช้าวันรุ่งขึ้นหม่อมฉันตื่นขึ้นจะให้นมลูก ก็พบว่าลูกตายแล้ว พอสว่างหม่อมฉันเพ่งดู จึงเห็นว่าไม่ใช่ลูกของหม่อมฉัน”

22หญิงอีกคนพูดขึ้นว่า “นั่นแหละเป็นลูกของเธอ ส่วนเด็กที่ยังมีชีวิตอยู่เป็นลูกของฉัน”

แต่หญิงคนแรกยืนยันว่า “ไม่ใช่ ลูกที่ตายแล้วเป็นของเธอ ลูกที่ยังมีชีวิตอยู่เป็นของฉัน” แล้วทั้งสองคนก็เถียงกันต่อหน้ากษัตริย์

23กษัตริย์ตรัสว่า “คนนี้ก็ว่า ‘ลูกฉันยังอยู่ ลูกเธอตายแล้ว’ คนนั้นก็ว่า ‘ไม่ใช่ ลูกเธอตายแล้ว ลูกฉันสิยังอยู่’ ”

24แล้วกษัตริย์ตรัสว่า “เอาดาบมาให้เราสักเล่มสิ” ก็มีผู้นำดาบมาถวาย 25กษัตริย์ตรัสสั่งว่า “จงฟันเด็กคนที่ยังมีชีวิตอยู่ออกเป็นสองท่อน แบ่งให้ผู้หญิงสองคนนี้คนละท่อน”

26หญิงที่เป็นแม่ของเด็กนั้นจริงๆ สงสารลูกจับใจ จึงทูลกษัตริย์ว่า “อย่าเลยพระองค์เจ้าข้า ยกลูกให้นางไปเถิด อย่าฆ่าลูกเลย!”

แต่อีกคนพูดว่า “ฟันเป็นสองท่อนเลย จะได้ไม่ต้องเป็นของเธอหรือของฉัน!”

27กษัตริย์จึงตรัสว่า “อย่าฆ่าเด็กนั้นเลย จงมอบเขาให้กับหญิงคนที่ต้องการให้เด็กมีชีวิตอยู่ เพราะเธอนั่นแหละเป็นแม่”

28เมื่อชนชาติอิสราเอลทั้งปวงได้รู้ถึงคำตัดสินของกษัตริย์ ก็ยำเกรงพระองค์ เพราะเห็นว่าทรงมีสติปัญญาจากพระเจ้าเพื่อผดุงความยุติธรรม