1 ቆሮንቶስ 6 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

1 ቆሮንቶስ 6:1-20

መካሰስ በክርስቲያኖች መካከል

1ከመካከላችሁ አንድ ሰው ከሌላው ጋር ሙግት ቢኖረው፣ ጕዳዩን በቅዱሳን ፊት በማቅረብ ፈንታ እንዴት ደፍሮ በማያምኑ ሰዎች ፊት ለመፋረድ ያቀርባል? 2ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ እንግዲያው፣ በትንሹ ነገር ላይ ለመፍረድ አትበቁምን? 3በምድራዊ ሕይወት ጕዳይ ቀርቶ፣ በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን? 4እንግዲህ እንዲህ ያለ ጕዳይ ሲያጋጥማችሁ፣ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጅ አድርጋችሁ ሹሟ6፥4 ወይም በቤተ ክርስቲያን የተናቁ ሰዎችን ፈራጅ አድርጋችሁ ትሾማላችሁ?! 5ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ብዬ ነው። ለመሆኑ ከመካከላችሁ ወንድሞችን ለማስታረቅ የሚበቃ አስተዋይ ሰው የለምን? 6ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ለመክሰስ ፍርድ ቤት ይሄዳል፤ ያውም በማያምኑ ሰዎች ፊት!

7እንግዲህ በመካከላችሁ መካሰስ መኖሩ ራሱ ውድቀታችሁን ያሳያል። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? 8እናንተ ግን ራሳችሁ ትበድላላችሁ፤ ታታልላላችሁም፤ ያውም እኮ ወንድሞቻችሁን።

9ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ አመንዝሮች፣ ወንደቃዎች፣ ግብረ ሰዶማውያን፣ 10ወይም ሌቦች፣ ስግብግቦች፣ ሰካራሞች፣ ተሳዳቢዎችና ቀማኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። 11ከእናንተ አንዳንዶቻችሁ እንደዚህ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።

የዝሙት ኀጢአት

12“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር አይጠቅምም፤ “ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ይሁን እንጂ ምንም ነገር በእኔ ላይ አይሠለጥንም። 13ደግሞም፣ “ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው። 14እግዚአብሔር ጌታን ከሙታን እንዳስነሣው፣ እኛንም ደግሞ በኀይሉ ከሙታን ያስነሣናል። 15ሰውነታችሁ የክርስቶስ የአካሉ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? ታዲያ፣ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ ከዝሙት ዐዳሪ ሴት ብልቶች ጋር አንድ ላድርገውን? ከቶ አይገባም! 16ወይስ ከዝሙት ዐዳሪ ጋር የሚተባበር ሰው ከእርሷ ጋር አንድ ሥጋ እንደሚሆን አታውቁምን? “ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ” ተብሏልና። 17ነገር ግን ከጌታ ጋር የሚተባበር ከእርሱ ጋር አንድ መንፈስ ይሆናል።

18ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል። 19ለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ 20በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

New International Reader’s Version

1 Corinthians 6:1-20

Do Not Take Believers to Court

1Suppose one of you wants to bring a charge against another believer. Should you take it to ungodly people to be judged? Why not take it to the Lord’s people? 2Or don’t you know that the Lord’s people will judge the world? Since this is true, aren’t you able to judge small cases? 3Don’t you know that we will judge angels? Then we should be able to judge the things of this life even more! 4So suppose you disagree with one another in matters like this. Who do you ask to decide which of you is right? Do you ask people who live in a way the church disapproves of? Of course not! 5I say this to shame you. Is it possible that no one among you is wise enough to judge matters between believers? 6Instead, one believer goes to court against another. And this happens in front of unbelievers!

7When you take another believer to court, you have lost the battle already. Why not be treated wrongly? Why not be cheated? 8Instead, you yourselves cheat and do wrong. And you do it to your brothers and sisters. 9Don’t you know that people who do wrong will not receive God’s kingdom? Don’t be fooled. Those who commit sexual sins will not receive the kingdom. Neither will those who worship statues of gods or commit adultery. Neither will men who sleep with other men. 10Neither will thieves or those who always want more and more. Neither will those who are often drunk or tell lies or cheat. People who live like that will not receive God’s kingdom. 11Some of you used to do those things. But your sins were washed away. You were made holy. You were made right with God. All of this was done in the name of the Lord Jesus Christ. It was also done by the Spirit of our God.

Sexual Sins

12Some of you say, “I have the right to do anything.” But not everything is helpful. Again some of you say, “I have the right to do anything.” But I will not be controlled by anything. 13Some of you say, “Food is for the stomach, and the stomach is for food. And God will destroy both of them.” But the body is not meant for sexual sins. The body is meant for the Lord. And the Lord is meant for the body. 14By his power God raised the Lord from the dead. He will also raise us up. 15Don’t you know that your bodies belong to the body of Christ? Should I take what belongs to Christ and join it to a prostitute? Never! 16When you join yourself to a prostitute, you become one with her in body. Don’t you know this? Scripture says, “The two will become one.” (Genesis 2:24) 17But whoever is joined to the Lord becomes one with him in spirit.

18Keep far away from sexual sins. All the other sins a person commits are outside the body. But sexual sins are sins against their own body. 19Don’t you know that your bodies are temples of the Holy Spirit? The Spirit is in you, and you have received the Spirit from God. You do not belong to yourselves. 20Christ has paid the price for you. So use your bodies in a way that honors God.