1 ቆሮንቶስ 4 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

1 ቆሮንቶስ 4:1-21

የክርስቶስ ሐዋርያት

1እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለ ዐደራዎች ሊቈጥረን ይገባል። 2ባለ ዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው። 3በእናንተም ሆነ በሰዎች የፍርድ ሸንጎ ቢፈረድብኝ እኔ በበኩሌ ግድ የለኝም፤ እኔ እንኳ በራሴ ላይ አልፈርድም። 4ኅሊናዬ ንጹሕ ነው፤ ይህ ግን ጥፋት አልባ መሆኔን አያረጋግጥም፤ በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ነው። 5ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።

6እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ለእናንተ ጥቅም ብዬ በዚህ ጕዳይ እኔን ራሴንና አጵሎስን ምሳሌ አድርጌ አቅርቤላችኋለሁ፤ ይህንም ያደረግሁት፣ “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ከእኛ እንድትማሩ ነው። ስለዚህ አንዱን ሰው ከሌላው አብልጣችሁ አትመኩበት። 7ለመሆኑ፣ አንተን ከሌላው እንድትበልጥ ያደረገህ ማን ነው? ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ? ከተቀበልህ ታዲያ፣ እንዳልተቀበልህ ለምን ትመካለህ?

8አሁንስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል! ሀብታምም ሆናችኋል! ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል! በርግጥ ብትነግሡማ እኛም ከእናንተ ጋር በነገሥን ነበር፤ 9ምክንያቱም እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን፣ ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሰው ሁሉ መጨረሻ ያሰለፈን ይመስለኛል፤ ለዓለም ሁሉ፣ ለመላእክትም ለሰዎችም ትርኢት ሆነናል። 10እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን። 11እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንደበደባለን፤ ያለ መጠለያ እንንከራተታለን፤ 12በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲረግሙን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤ 13ስማችንን ሲያጠፉ መልካም እንመልሳለን፤ እስከ አሁንም ድረስ የዓለም ጕድፍ፣ የምድር ጥራጊ ሆነናል።

14ይህን የምጽፍላችሁ እንደ ተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ብዬ አይደለም። 15ምንም እንኳ በዐሥር ሺሕ የሚቈጠሩ ሞግዚቶች በክርስቶስ ቢኖሯችሁም፣ ብዙ አባቶች ግን የሏችሁም፤ በወንጌል አማካይነት በክርስቶስ ኢየሱስ ወልጄአችኋለሁና። 16ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ። 17እንግዲህ በጌታ የተወደደውንና የታመነውን ልጄን ጢሞቴዎስን የላክሁላችሁ በዚህ ምክንያት ነው፤ እርሱም በየስፍራው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከማስተምረው ትምህርት ጋር የሚስማማውን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን የሕይወት አካሄዴን ያሳስባችኋል።

18ከእናንተ አንዳንዶቹ ወደ እናንተ የማልመጣ መስሏቸው ታብየዋል፤ 19ይሁን እንጂ የጌታ ፈቃድ ቢሆን ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ ከዚያም እነዚህ ትዕቢተኞች የሚናገሩትን ብቻ ሳይሆን፣ ምን ኀይል እንዳላቸውም ማየት እሻለሁ። 20ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት የወሬ ጕዳይ ሳይሆን የኀይል ጕዳይ ነው። 21ለመሆኑ የምትፈልጉት የቱን ነው? በትር ይዤ ልምጣ ወይስ በፍቅርና በገርነት መንፈስ?

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

哥林多前书 4:1-21

基督的使徒

1因此,人应该把我们当作是基督的仆人,是上帝奥秘之事的管家。 2对管家的要求是忠心。 3我对你们或别人给我的评价毫不介意,我也不评价我自己。 4就算我今日问心无愧,也不能自以为义,因为评价我的是主。 5所以,时候未到,不可妄下断语。到主耶稣再来的时候,祂会揭开暗中的隐情,使人心里的动机显露。到时候上帝会给各人应得的称赞。

6弟兄姊妹,为了你们的益处,我以亚波罗和自己作例子,好让你们效法我们不越过圣经的准则,免得有人自高自大、厚此薄彼。 7谁使你与众不同呢?你有哪一样不是领受的呢?既然一切都是领受的,你为什么还自夸,好像不是领受的? 8你们已经饱足了,富有了,不需要我们,自己已经做王了。我倒希望你们真的能做王,好让我们也和你们一同做王。 9我想,上帝把我们使徒排在队伍的末尾,好像被判了死罪的囚犯,让我们成了一台戏,给全宇宙看,就是给世人和天使观看。

10我们为了基督的缘故被人看为愚昧,你们在基督里倒成了聪明人;我们软弱,你们倒强壮;你们受人尊敬,我们倒被人藐视。 11我们至今还是又饥又渴,衣不蔽体,遭受毒打,居无定所, 12还要亲手劳作。我们被人咒骂,就为对方祝福;受人迫害,就逆来顺受; 13被人毁谤,就好言相劝。人们至今仍将我们看作世上的废物,万物中的渣滓。

14我之所以写这些事,并非是叫你们羞愧,而是像劝诫我亲爱的儿女一样劝诫你们。 15虽然有千万老师将基督的事教导你们,但父亲并不多,因为我借着福音在基督耶稣里成为你们的父亲。 16所以,我劝你们效法我。 17正因如此,我派了提摩太去你们那里。他在主里忠心耿耿,是我所爱的孩子。他会提醒你们我在基督里如何行事为人,在各地、各教会如何教导人。

18你们当中有些人以为我不会再去你们那里,就傲慢自大起来。 19但主若许可,我会很快去你们那里。那时我要看看这些骄傲的人究竟是只会空谈,还是真有上帝的权能。 20因为上帝的国不在于空谈,而在于权能。 21到底你们要什么呢?要我带着刑杖去呢?还是要我带着温柔慈爱的心去呢?