1 ቆሮንቶስ 11 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

1 ቆሮንቶስ 11:1-34

1እኔ የክርስቶስን ምሳሌ እንደምከተል እናንተም የእኔን ተከተሉ።

ሥርዐት ያለው አምልኮ

2በሁሉም ነገር ስለምታስቡልኝና ከእኔ የተቀበላችሁትን ትምህርት11፥2 ወይም ወግ አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።

3ነገር ግን ይህን እንድታውቁ እወድዳለሁ፤ የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ ነው፤ የሴትም ራስ ወንድ ነው፤ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር ነው። 4ራሱን ተከናንቦ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ማንኛውም ወንድ የእርሱን ራስ ያዋርዳል፤ 5ራሷን ሳትሸፍን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ማንኛዋም ሴት የእርሷን ራስ ታዋርዳለች፤ ጠጕሯን እንደ ተላጨች ይቈጠራልና። 6ሴት ራሷን የማትሸፍን ከሆነ፣ ጠጕሯን ትቈረጥ፤ ጠጕሯን መቈረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር መስሎ ከታያት ግን ራሷን ትሸፈን።

7ወንድ ራሱን መከናነብ የለበትም፤11፥4-7 ወይም የራሱን ጠጕር አስረዝሞ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ማንኛውም ወንድ ራሱ የሆነውን ያዋርዳል፤ 5 ራሷን ሳትከናነብ የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ማንኛዋም ሴት ራሷ የሆነውን ታዋርዳለች፤ እንዲህ ያለችው ሴት ጠጕራቸውን ከተላጩ ሴቶች አንዷን ትመስላለችና። ሴት ራሷን የማትከናነብ ከሆነ፣ ጠጕሯን ታሳጥር፤ ጠጕሯን መቈረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ስለሆነ ግን እንደ ገና ታሳድገው። 7 ወንድ ጠጕሩን ማስረዘም የለበትም፤ ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ነውና፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት፤ 8ምክንያቱም ሴት ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘም። 9ደግሞም ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም። 10በዚህ ምክንያት፣ በመላእክትም ምክንያት፣ ሴት በሥልጣን ሥር መሆኗን የሚያሳይ ምልክት በራሷ ላይ ታድርግ።

11በጌታ ዘንድ ግን ሴት ያለ ወንድ፣ ወንድም ያለ ሴት አይሆንም። 12ሴት ከወንድ እንደ ተገኘች ሁሉ፣ ወንድም ከሴት ይወለዳልና፤ ነገር ግን የሁሉም መገኛ እግዚአብሔር ነው።

13እስቲ እናንተ ፍረዱ፤ ሴት ራሷን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ይገባታልን? 14ወንድ ጠጕሩን ቢያስረዝም ነውር እንደሚሆንበት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? 15ሴት ግን ጠጕሯን ብታስረዝም ክብሯ አይደለምን? ረዥም ጠጕር የተሰጣት መጐናጸፊያ እንዲሆናት ነውና። 16እንግዲህ ማንም በዚህ ጕዳይ ላይ መከራከር ቢፈልግ፣ እኛም ሆንን የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ የተለየ ልማድ የለንም።

የጌታ እራት

11፥23-25 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥26-28ማር 14፥22-24ሉቃ 22፥17-20

17ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚጐዳ እንጂ ለሚጠቅም ስላልሆነ፣ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ እያመሰገንኋችሁ አይደለም። 18ከሁሉ አስቀድሞ በቤተ ክርስቲያን በምትሰበሰቡበት ጊዜ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ ሰምቻለሁ፤ ይህም ሊሆን እንደሚችል በከፊል አምናለሁ። 19ከእናንተ መካከል እውነተኞቹ ተለይተው ይታወቁ ዘንድ፣ ይህ መለያየት በመካከላችሁ መኖሩ የግድ ነው። 20በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምትበሉት የጌታን እራት አይደለም፤ 21በምትበሉበት ጊዜ አንዱ ሌላውን ሳይጠብቅ ምግቡን ይበላልና፤ አንዱ እየተራበ ሌላው ይሰክራል። 22ለመሆኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን በመናቅ፣ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? እንግዲህ ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? ፈጽሞ አላመሰግናችሁም።

23እኔ ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ ዐልፎ በተሰጠባት ሌሊት እንጀራን አንሥቶ 24ከባረከ በኋላ ቈርሶ፣ “ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ለመታሰቢያዬም አድርጉት” አለ። 25እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ፣ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ ስለዚህ ከጽዋው በምትጠጡበት ጊዜ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ። 26ይህን እንጀራ በምትበሉበት ጊዜ፣ ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።

27እንግዲህ ማንም ሳይገባው፣ ይህን እንጀራ ቢበላ ወይም የጌታን ጽዋ ቢጠጣ፣ የጌታ ሥጋና ደም ባለ ዕዳ ይሆናል። 28ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ከመብላቱና ከዚህ ጽዋ ከመጠጣቱ በፊት፣ ራሱን ይመርምር፤ 29ምክንያቱም ማንም የጌታን ሥጋ ሳይገባው11፥29 ሳይለይ ወይም ሳይገነዘብ ማለት ነው። ቢበላና ቢጠጣ ፍርድ የሚያመጣበትን ይበላል፤ ይጠጣልም። 30ከእናንተ መካከል ብዙዎች የደከሙትና የታመሙት፣ አንዳንዶችም ያንቀላፉት በዚህ ምክንያት ነው። 31ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብን ነበር። 32ነገር ግን ጌታ በሚፈርድብን ጊዜ እንገሠጻለን፤ ይኸውም ከዓለም ጋር አብረን እንዳንኰነን ነው።

33ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፤ ለመብላት በምትሰበሰቡበት ጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ። 34በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለፍርድ እንዳይሆንባችሁ፣ ማንም የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ።

ስለ ቀረው ነገር ደግሞ በምመጣበት ጊዜ እደነግጋለሁ።

King James Version

1 Corinthians 11:1-34

1Be ye followers of me, even as I also am of Christ.

2Now I praise you, brethren, that ye remember me in all things, and keep the ordinances, as I delivered them to you. 3But I would have you know, that the head of every man is Christ; and the head of the woman is the man; and the head of Christ is God. 4Every man praying or prophesying, having his head covered, dishonoureth his head. 5But every woman that prayeth or prophesieth with her head uncovered dishonoureth her head: for that is even all one as if she were shaven. 6For if the woman be not covered, let her also be shorn: but if it be a shame for a woman to be shorn or shaven, let her be covered. 7For a man indeed ought not to cover his head, forasmuch as he is the image and glory of God: but the woman is the glory of the man. 8For the man is not of the woman; but the woman of the man. 9Neither was the man created for the woman; but the woman for the man. 10For this cause ought the woman to have power on her head because of the angels. 11Nevertheless neither is the man without the woman, neither the woman without the man, in the Lord. 12For as the woman is of the man, even so is the man also by the woman; but all things of God. 13Judge in yourselves: is it comely that a woman pray unto God uncovered? 14Doth not even nature itself teach you, that, if a man have long hair, it is a shame unto him? 15But if a woman have long hair, it is a glory to her: for her hair is given her for a covering. 16But if any man seem to be contentious, we have no such custom, neither the churches of God.

17Now in this that I declare unto you I praise you not, that ye come together not for the better, but for the worse. 18For first of all, when ye come together in the church, I hear that there be divisions among you; and I partly believe it. 19For there must be also heresies among you, that they which are approved may be made manifest among you. 20When ye come together therefore into one place, this is not to eat the Lord’s supper. 21For in eating every one taketh before other his own supper: and one is hungry, and another is drunken. 22What? have ye not houses to eat and to drink in? or despise ye the church of God, and shame them that have not? What shall I say to you? shall I praise you in this? I praise you not. 23For I have received of the Lord that which also I delivered unto you, That the Lord Jesus the same night in which he was betrayed took bread: 24And when he had given thanks, he brake it, and said, Take, eat: this is my body, which is broken for you: this do in remembrance of me. 25After the same manner also he took the cup, when he had supped, saying, This cup is the new testament in my blood: this do ye, as oft as ye drink it, in remembrance of me. 26For as often as ye eat this bread, and drink this cup, ye do shew the Lord’s death till he come. 27Wherefore whosoever shall eat this bread, and drink this cup of the Lord, unworthily, shall be guilty of the body and blood of the Lord. 28But let a man examine himself, and so let him eat of that bread, and drink of that cup. 29For he that eateth and drinketh unworthily, eateth and drinketh damnation to himself, not discerning the Lord’s body. 30For this cause many are weak and sickly among you, and many sleep. 31For if we would judge ourselves, we should not be judged. 32But when we are judged, we are chastened of the Lord, that we should not be condemned with the world. 33Wherefore, my brethren, when ye come together to eat, tarry one for another. 34And if any man hunger, let him eat at home; that ye come not together unto condemnation. And the rest will I set in order when I come.