1 ሳሙኤል 31 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

1 ሳሙኤል 31:1-13

የሳኦል መሞት

31፥1-13 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 1፥4-121ዜና 10፥1-12

1በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያን ከፊታቸው ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ተወግተው ወደቁ። 2ፍልስጥኤማውያን ሳኦልንና ልጆቹን አጥብቀው ተከታተሉ፤ የሳኦልንም ልጆች ዮናታንን፣ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሉ። 3ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፤ ቀስተኞችም ደርሰው እጅግ አቈሰሉት።

4ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፣ “እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝ፣ እንዳያዋርዱኝ፣ አንተው ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው።

ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፣ እንቢ አለው። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት። 5ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ባየ ጊዜ፣ እርሱም እንደዚሁ በሰይፉ ላይ ወድቆ አብሮት ሞተ። 6ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ፣ አብረውት የነበሩ ሰዎች ሁሉና ጋሻ ጃግሬው የሞቱት በዚያኑ ቀን ነበር።

7በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን የእስራኤል ሰራዊት መሸሹን፣ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።

8በማግስቱም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ለመግፈፍ ሲመጡ፣ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው። 9ከዚያም የሳኦልን ራስ ቈርጠው፣ የጦር መሣሪያውንም ገፍፈው፣ የምሥራቹን በየቤተ ጣዖቶቻቸውና በሕዝባቸው መካከል እንዲናገሩ ወደ ፍልስጥኤም ምድር ሁሉ መልክተኞች ላኩ። 10የጦር መሣሪያውን በአስታሮት ቤተ ጣዖት ውስጥ አኖሩት፤ ሬሳውን ደግሞ በቤትሳን ግንብ ላይ አንጠለጠሉት።

11የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ፣ 12ጀግኖቻቸው ሁሉ በሌሊት ወደ ቤትሳን ሄዱ። የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከግንቡ ላይ አውርደው ወደ ኢያቢስ አምጥተው አቃጠሉ። 13ከዚያም ዐጥንቶቻቸውን ወስደው በኢያቢስ ባለው የአጣጥ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።

Japanese Contemporary Bible

サムエル記Ⅰ 31:1-13

31

サウルの死

1その間に、ペリシテ人はイスラエル人と戦いを始めました。イスラエル軍はあえなく敗走し、ギルボア山で大多数が戦死しました。 2ペリシテ軍はサウルを追い詰め、息子のヨナタン、アビナダブ、マルキ・シュアを殺しました。

3-4なお、射手たちはサウルをねらい打ちにし、ついに致命傷を負わせました。王は苦しい息の下から、よろい持ちの護衛兵に言いました。「あの、神を知らぬペリシテ人に捕らえられて恥辱を受けるより、いっそ、おまえの剣で殺してくれ。」しかし、よろい持ちが恐れてためらっていると、王は自分の剣を取り、その切っ先の上にうつ伏せに倒れ、壮烈な最期を遂げました。 5王の死を見届けると、よろい持ちも、自ら剣の上にうつ伏せに倒れて殉死しました。 6こうして、同じ日のうちに、王と三人の息子、よろい持ち、それに兵士たちが次々に死んだのです。 7谷の向かい側やヨルダン川の対岸にいたイスラエル人は、味方の兵士たちが逃げ出し、王とその息子たちが死んだことを聞くと、町々を捨てて逃げ去りました。それで、その町々にはペリシテ人が住むようになったのです。

8翌日、ペリシテ人は死者たちの遺品をはぎ取りに来て、サウルと三人の息子の遺体をギルボア山で発見しました。 9彼らは王の首を切り、武具をはぎ取りました。そして、国中の偶像の神殿と国民とに、サウル王を討ち取ったという朗報を伝えました。 10サウル王の武具はアシュタロテの神殿に奉納され、しかばねはベテ・シャンの城壁にさらされました。 11ヤベシュ・ギルアデの住民は、このペリシテ人の仕打ちを聞くと、 12さっそく勇士たちが夜通しベテ・シャン目指して歩いて行って、サウル王とその息子たちの死体を城壁から降ろし、ヤベシュに運んで火葬にしたのです。 13その骨はヤベシュにある柳の木の根もとに葬られ、人々は七日の間断食して、喪に服しました。