1 ሳሙኤል 3 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

1 ሳሙኤል 3:1-21

እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው

1ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር።

2ዐይኖቹ ከመድከማቸው የተነሣ ማየት የተሳነው ዔሊ አንድ ሌሊት በስፍራው ተኝቶ ነበር። 3ሳሙኤልም ደግሞ የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ3፥3 የማደሪያው ድንኳን ነው። ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ የእግዚአብሔር መብራትም ገና አልጠፋም ነበር። 4እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ጠራው።

ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” አለ፤ 5ወደ ዔሊም ሮጦ በመሄድ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው።

ዔሊ ግን፣ “እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው፤ እርሱም ሄዶ ተኛ።

6ደግሞም እግዚአብሔር፣ “ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው።

ሳሙኤልም ተነሣና ወደ ዔሊ ሄዶ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው።

ዔሊም መልሶ፣ “ልጄ ሆይ፤ እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው።

7በዚያም ጊዜ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ገና አላወቀም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር።

8እግዚአብሔር ሳሙኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው፤ አሁንም ሳሙኤል ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው።

ዔሊ በዚህ ጊዜ ብላቴናውን ይጠራ የነበረው እግዚአብሔር መሆኑን ተረዳ። 9በዚያ ጊዜ ዔሊ ሳሙኤልን፣ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ስለዚህም ሳሙኤል ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።

10እግዚአብሔርም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ቀደም ሲል እንዳደረገው ሁሉ “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው።

ሳሙኤልም፣ “ባሪያህ ይሰማልና ተናገር” አለ።

11እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፤ የሰሚውን ሁሉ ጆሮ ጭው የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ። 12በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተ ሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ። 13ዔሊ በሚያውቀው ኀጢአት ምክንያት በቤተ ሰቡ ላይ ለዘላለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር፤ ልጆቹ አስጸያፊ ነገር አድርገዋል3፥13 የማሶሬቱ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ነገር ግን ጥንታዊው የዕብራይስጡ ጸሐፍት ትውፊት እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናት፣ ልጆቹ እግዚአብሔርን ተዳፍረዋል ይላል።፤ እርሱ ግን አልከለከላቸውም። 14ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቍርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።”

15ሳሙኤል እስኪነጋ ድረስ ተኛ፤ ከዚያም ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ ራእዩንም ለዔሊ መንገር ፈራ፤ 16ዔሊ ግን ሳሙኤልን፣ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው።

ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” ሲል መለሰ።

17ዔሊም፣ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ ለከፋም ይዳርግህ” አለው። 18ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፣ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ” አለ።

19ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ፣ ከሚናገረው ቃል አንዳች በምድር አይወድቅም ነበር። 20ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል በርግጥ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን ዐወቁ። 21እግዚአብሔር በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ በዚያም በቃሉ አማካይነት ራሱን ለሳሙኤል ገለጠ።

New International Version – UK

1 Samuel 3:1-21

The Lord calls Samuel

1The boy Samuel ministered before the Lord under Eli. In those days the word of the Lord was rare; there were not many visions.

2One night Eli, whose eyes were becoming so weak that he could barely see, was lying down in his usual place. 3The lamp of God had not yet gone out, and Samuel was lying down in the house of the Lord, where the ark of God was. 4Then the Lord called Samuel.

Samuel answered, ‘Here I am.’ 5And he ran to Eli and said, ‘Here I am; you called me.’

But Eli said, ‘I did not call; go back and lie down.’ So he went and lay down.

6Again the Lord called, ‘Samuel!’ And Samuel got up and went to Eli and said, ‘Here I am; you called me.’

‘My son,’ Eli said, ‘I did not call; go back and lie down.’

7Now Samuel did not yet know the Lord: the word of the Lord had not yet been revealed to him.

8A third time the Lord called, ‘Samuel!’ And Samuel got up and went to Eli and said, ‘Here I am; you called me.’

Then Eli realised that the Lord was calling the boy. 9So Eli told Samuel, ‘Go and lie down, and if he calls you, say, “Speak, Lord, for your servant is listening.” ’ So Samuel went and lay down in his place.

10The Lord came and stood there, calling as at the other times, ‘Samuel! Samuel!’

Then Samuel said, ‘Speak, for your servant is listening.’

11And the Lord said to Samuel: ‘See, I am about to do something in Israel that will make the ears of everyone who hears about it tingle. 12At that time I will carry out against Eli everything I spoke against his family – from beginning to end. 13For I told him that I would judge his family for ever because of the sin he knew about; his sons uttered blasphemies against God,3:13 An ancient Hebrew scribal tradition (see also Septuagint); Masoretic Text sons made themselves contemptible and he failed to restrain them. 14Therefore I swore to the house of Eli, “The guilt of Eli’s house will never be atoned for by sacrifice or offering.” ’

15Samuel lay down until morning and then opened the doors of the house of the Lord. He was afraid to tell Eli the vision, 16but Eli called him and said, ‘Samuel, my son.’

Samuel answered, ‘Here I am.’

17‘What was it he said to you?’ Eli asked. ‘Do not hide it from me. May God deal with you, be it ever so severely, if you hide from me anything he told you.’ 18So Samuel told him everything, hiding nothing from him. Then Eli said, ‘He is the Lord; let him do what is good in his eyes.’

19The Lord was with Samuel as he grew up, and he let none of Samuel’s words fall to the ground. 20And all Israel from Dan to Beersheba recognised that Samuel was attested as a prophet of the Lord. 21The Lord continued to appear at Shiloh, and there he revealed himself to Samuel through his word.