1 ሳሙኤል 2 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

1 ሳሙኤል 2:1-36

የሐና የምስጋና ጸሎት

1ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤

“ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤

ቀንዴም2፥1 በዚህ ስፍራና በቍጥር 10 ላይ ቀንድ የጥንካሬ ምልክት ነው። በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤

አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤

በማዳንህ ደስ ይለኛልና።

2“እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ2፥2 ወይም አንድ ቅዱስ ማንም የለም፤

ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤

እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም።

3“ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤

እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤

እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፤

ሥራም ሁሉ በእርሱ ይመዘናል።

4“የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፤

ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል።

5ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤

ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤

መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤

ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች።

6እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤

ወደ መቃብር2፥6 ዕብራይስጡ ሲኦል ይላል ያወርዳል፤ ያወጣልም።

7እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤

ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።

8እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤

ምስኪኑንም ከጕድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤

ከመኳንንቱ ጋር ያስቀምጣቸዋል፤

የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል።

“የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፣

ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጓል።

9እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል፤

ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ።

“ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤

10ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ፤

እርሱ ከሰማይ ያንጐደጕድባቸዋል፤

እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል።

“ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤

የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”

11ከዚያ በኋላ ሕልቃና ወደ ቤቱ ወደ ራማ ሄደ፤ ብላቴናው ግን በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።

የዔሊ ልጆች ክፉ ድርጊት

12የዔሊ ልጆች ምናምንቴዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር። 13በዚያን ጊዜ ካህናቱ ከሕዝቡ ጋር ባላቸው ግንኙነት የሚፈጽሙት ወግ ነበር፤ ይኸውም ማንም ሰው መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለውን ሜንጦ ይዞ ይመጣል፤ 14ወደ ድስቱ ወይም ወደ ቶፋው ወይም ወደ አፍላሉ፣ ወይም ወደ ምንቸቱ ይሰደዋል። ከዚያም ካህኑ ሜንጦው ያወጣውን ማናቸውንም ሥጋ ለራሱ ይወስደዋል። ወደ ሴሎ የሚመጡትን እስራኤላውያን ሁሉ የሚያስተናግዱት በዚህ ዐይነት ነበር። 15ነገር ግን ሥቡ ገና ከመቃጠሉ በፊት የካህኑ አገልጋይ መጥቶ መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰው፣ “ካህኑ ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ ስለማይቀበል፣ ለካህኑ የሚጠበስ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።

16ሰውየውም፣ “በመጀመሪያ ሥቡ ይቃጠል፤ ከዚያ በኋላ የምትፈልገውን ትወስዳለህ” ቢለው እንኳ አገልጋዩ፣ “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ ያለዚያ በግድ እወስዳለሁ” ይለው ነበር።

17ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት ይንቁ ስለ ነበር2፥17 ወይም የሚንቁ ሰዎች ስለ ነበሩ፣ ይህ የወጣቶቹ ኀጢአት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበረ።

18ብላቴናው ሳሙኤል ግን ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር። 19እናቱም ከባሏ ጋር ዓመታዊ መሥዋዕት ለማቅረብ በምትሄድበት ጊዜ ሁሉ ትንሽ መደረቢያ እየሠራች ይዛለት ትሄድ ነበር። 20ዔሊም፣ “በጸሎት ባገኘችውና ለእግዚአብሔር በሰጠችው ልጅ ምትክ እግዚአብሔር ከዚህችው ሴት ዘር ይስጥህ” እያለ ሕልቃናንና ሚስቱን ይመርቃቸው ነበር፤ ከዚያ በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር። 21እግዚአብሔርም ሐናን ባረካት፤ ፀነሰችም፤ ሦስት ወንዶች፣ ሁለት ሴቶች ልጆችም ወለደች። ብላቴናውም ሳሙኤል በእግዚአብሔር ፊት አደገ።

22በዚህ ጊዜ ዔሊ እጅግ አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹም በመላው እስራኤል ያደርጉ የነበረውን፣ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋር ዝሙት መፈጸማቸውን ሰማ። 23ስለዚህም እንዲህ አላቸው፤ “ስለምትፈጽሙት ክፉ ድርጊት ከመላው ሕዝብ እሰማለሁ፤ ለምን እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ? 24ልጆቼ ሆይ፤ ትክክል አይደላችሁም፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ተሠራጭቶ የምሰማባችሁ ወሬ ጥሩ አይደለም። 25አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል፣ እግዚአብሔር2፥25 ወይም መሳፍንት ጣልቃ ገብቶ ይፈርዳል፤ ነገር ግን ሰው እግዚአብሔርን ቢበድል፣ ማን ይማልድለታል?” ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ስለ ፈለገ፣ ልጆቹ የአባታቸውን ተግሣጽ አልሰሙም።

26ብላቴናውም ሳሙኤል በአካልና በሞገስ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት እያደገ ሄደ።

በዔሊ ቤተ ሰብ ላይ የተነገረ ትንቢት

27በዚህ ጊዜ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአባትህ ቤት በግብፅ ምድር በፈርዖን እጅ በነበረ ጊዜ ራሴን ገለጥሁለት? 28የእኔ ካህን እንዲሆን፣ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፣ ዕጣን እንዲያጥን፣ በፊቴም ኤፉድ እንዲለብስ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ አባትህን መረጥሁት። ደግሞም እስራኤላውያን በእሳት የሚያቀርቡትን ቍርባን ሁሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ። 29ታዲያ በማደሪያዬ እንዲቀርብ ያዘዝሁትን መሥዋዕትና ቍርባን የናቃችሁ ለምንድን ነው? አንተና ልጆችህ ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቍርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር ከእኔ ይልቅ ልጆችህን የምታከብራቸው ስለ ምንድን ነው?’

30“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ቤትህና የአባትህ ቤት በፊቴ ለዘላለም ያገለግሉኝ ዘንድ ተስፋ ሰጥቼ ነበር፤’ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ከእንግዲህ አላደርገውም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ፤ የሚንቁኝም ፈጽሞ ይናቃሉ። 31እነሆ፤ በዘርህ ሽማግሌ እንዳይገኝ ያንተን ኀይልና የአባትህን ቤተ ሰብ ኀይል የምሰብርበት ጊዜ ይመጣል፤ 32በማደሪያዬም መከራ ታያለህ፤ ምንም እንኳ ለእስራኤል በጎ ነገር ቢደረግም፣ በቤተ ሰብህ ውስጥ ሽማግሌ ፈጽሞ አይገኝም። 33ከመሠዊያዬ የማላስወግዳቸው ዘሮችህ በሕይወት የሚተርፉትም ዐይኖችህን በእንባ ለማፍዘዝ፣ ልብህን በሐዘን ለማደንዘዝ ብቻ ነው፣ ሌሎቹ ዘሮችህ ግን በሙሉ በለጋነታቸው በዐጭር ይቀጫሉ።

34“ ‘በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚደርሰው ላንተ ምልክት ይሆንሃል፣ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ። 35እንደ ልቤና እንደ አሳቤ የሚያገለግል የታመነ ካህን ለራሴ አስነሣለሁ፤ ቤቱን አጽንቼ አቆማለሁ፣ እርሱም በቀባሁት ፊት ለዘላለም ያገለግላል። 36ከዘሮችህም መካከል የተረፈው ማንኛውም ሰው፣ ለአንዲት ጥሬ ብርና ለቍራሽ እንጀራ ሲል በፊቱ ወድቆ ይሰግዳል፤ “የዕለት ጕርሴን እንዳገኝ እባክህ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ” በማለት ይለምናል።’ ”

Japanese Contemporary Bible

サムエル記Ⅰ 2:1-36

2

ハンナの祈り

1ハンナは祈りました。

「ああ、うれしゅうございます、主よ。

こんなにも祝福していただいて。

私は敵にはっきり答えることができます。

主が悩みを取り去ってくださいましたから。

私は喜びでいっぱいです。

2主のように聖なるお方はありません。

あなたのほかに神はないのです。

私たちの神のような大岩はありません。

3思い上がりも、尊大さも許されません。

主は何もかもご存じで、

すべての行為をおさばきになるのです。

4力を誇った者が弱くなり、

弱かった者が今や強くなっています。

5満ち足りていた者が今は飢え、

飢えていた者が満ち足りています。

不妊の女が今は七人の子持ちとなり、

多産の女がもう子を産めません。

6主は殺し、

主はいのちをお与えになります。

7主は、ある人々を貧しくし、

また、ある人々を裕福になさいます。

主はある者を倒し、

また、ある者を立ち上がらせてくださいます。

8主は、貧しい者をちりの中から、灰の山から引き上げ、

高貴な者のように取り扱い、

栄光の座につかせてくださいます。

この世はすべて主のものですから。

主はこの世界をふさわしくされました。

9主は信仰者を守られます。

しかし、悪者は暗闇に葬り去られます。

だれも自力でははい上がれません。

10主は手向かう者を打ちのめし、

天から彼らに雷鳴をとどろかせます。

主は地を隅々までさばき、

ご自分が選んだ王に特別な力を授け、

主に油注がれた者に大きな栄誉をお与えになるのです。」

11そののちエルカナとハンナは、サムエルを残してラマに帰りました。幼いサムエルは、祭司エリのもとで主に仕える者となりました。

エリの息子たち

12ところでエリの息子たちは、主をないがしろにする、不道徳でよこしまな者たちでした。 13-14いけにえをささげている人がいると、しもべを送り、いけにえの動物の肉が煮えている大なべの中に、そのしもべが三つ又の肉刺しを突き刺して、これらはみなエリの息子のものだと宣告しました。彼らは、いけにえをささげて礼拝するためにシロにやって来るすべてのイスラエル人に対して、このように行っていました。 15時には、祭壇で脂肪を焼く儀式が行われないうちから、しもべをやって、生の肉をよこせと言うことさえありました。焼き肉にして食べるためでした。

16いけにえをささげている人が、「いくらでもお取りになってけっこうです。しかし、まず〔律法のとおりに〕脂肪をすっかり焼いてしまわなければなりません」と答えると、使いの者はこう言うのです。「いや、たった今ほしいのだ。つべこべ言うなら、力ずくでももらうぞ。」

17こんなふうに、彼らは主の前に非常に大きな罪を犯しました。主へのささげ物を侮るようなことをしたからです。

18サムエルはまだ子どもでしたが、一人前の祭司のように、小さな亜麻布の儀式服を着て、主に仕えていました。 19毎年、母親が小さな上着をこしらえ、夫とともに、いけにえをささげに来る時に持って来てくれていたのです。 20エルカナとハンナが家路につく前に、エリは二人を祝福し、主にささげた子の代わりに、もっと子どもが授かるよう主に願い求めてくれました。 21それで主はハンナに、三人の息子と二人の娘を授けました。一方、少年サムエルは、主のもとで成長していきました。

22エリはすでに高齢に達していましたが、身辺の出来事についてはよくわきまえていました。例えば、息子たちが幕屋(聖所)の入口で仕えている女たちを誘惑したことも、ちゃんと知っていました。

23-25エリは息子たちを呼びつけて注意しました。「私は民から、おまえたちのおぞましい悪行についてさんざん聞かされた。よくも民を罪に惑わすようなことをしてくれたものだ。少しの罪でもきびしい罰が下るのに、主に対するおまえたちの罪には、どれほど重い罰が下るか知れたものではない。」

しかし、息子たちは耳を貸そうともしませんでした。というのは、主がすでに、この二人のいのちを絶とうとしていたからです。

26一方、少年サムエルはすくすく育ち、人からも神からも愛されました。

エリへの預言

27ある日、一人の預言者が来て、エリに主のことばを伝えました。「イスラエルの民がエジプトで奴隷だった時、わたしははっきり力を示したではないか。 28そして、なみいる同胞の中からあなたの先祖レビを選んで、祭司としたのではなかったか。その務めは、わたしの祭壇でいけにえをささげ、香をたき、祭司の服を着て仕えることだった。わたしは、あなたがた祭司にも、いけにえのささげ物を分け与えたではないか。 29それなのに、どうしてささげ物を一人占めしようとするのか。わたしよりも息子のほうが大事なのか。よくも親子して最上のささげ物によって肥え太ったものだ。

30それゆえ、イスラエルの神であるわたしは、こう宣言する。レビ族の一門であるあなたの家系が常に祭司となると約束したのは確かだが、今や、それがいつまでも続くと考えたら、大きな間違いである。わたしは、わたしを重んじる者を重んじる。わたしを侮る者は、わたしも軽んじる。 31あなたの家系は断絶する。これ以上、祭司を務めるには及ばない。家族全員、長寿を全うせずに死ぬのだ。よわいを重ねる者は一人もいない。 32あなたがたは、わたしが民に与える繁栄をうらやむだろう。あなたの一族は苦難と窮乏に陥る。だれ一人、長生きできない。 33かろうじて生き残った者も、悲嘆にくれて日を過ごす。子どもたちは、剣によって殺される。 34わたしのことばに偽りがないことを見せよう。二人の息子ホフニとピネハスは、同じ日に死ぬことになる。

35代わりに、わたしは一人の忠実な祭司を起こす。彼はわたしに仕え、わたしが告げるとおり正しく行うだろう。その子孫を末代まで祝福し、その一族を王の前に永遠の祭司とする。 36だから、あなたの子孫はみな、彼に頭を下げ、金と食物を乞うようになる。彼らはこう言ってすがるだろう。『どうか、祭司のどんな仕事でもさせてください。何とか食べていきたいのです』と。」