የቤተ መቅደሱ መዘምራን
1ዳዊት ከሰራዊቱ አለቆች ጋር ሆኖ በመሰንቆ፣ በበገናና በጸናጽል ድምፅ እየታጀቡ ትንቢት የሚናገሩትን ከአሳፍ፣ ከኤማንና ከኤዶታም ቤተ ሰብ መካከል መርጦ መደበ፤ ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑትም ሰዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፤
2ከአሳፍ ወንዶች ልጆች፤
ዘኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። የአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሡ አመራር ሥር ነበረ።
3ከኤዶታም ወንዶች ልጆች፤
ጎዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ25፥3 አንድ የዕብራይስጥ ቅጅና ጥቂት የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች (እንዲሁም ቍጥር 17 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ስሜኢ የሚለውን አይጨምሩም፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።
4ከኤማን ወንዶች ልጆች፤
ቡቅያ፣ መታንያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ሐናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት። 5እነዚህም ሁሉ የንጉሡ ባለ ራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ሰጡት25፥5 ዕብራይስጡ፤ ቀንዱ ከፍ ከፍ አለ ይላል። እግዚአብሔር ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።
6እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጸናጽል፣ በመሰንቆና በበገና ድምፅ ለሚቀርበው የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሡ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ። 7እነዚህም ከቤተ ዘመዶቻቸው ጋር በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑና የተካኑ ነበሩ፤ ቊጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ። 8የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።
9የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ለዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ25፥9 የሰብዓ ሊቃናት ትርጒም ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ የሚለውን አይጨምርም፤ | |
ቊጥራቸውም | 1225፥9 ድምሩን በተመለከተ ቍጥር 7 ይመ፤ ዕብራይስጡ፣ “12” የሚለውን አይጨምርም |
ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
10ሦስተኛው ለዛኩር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
11አራተኛው ላይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
12አምስተኛው ለነታንያ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
13ስድስተኛው ለቡቅያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
14ሰባተኛው ለይሽርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቁጥራቸውም | 12 |
15ስምንተኛው ለየሻያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቁጥራቸውም | 12 |
16ዘጠነኛው ለመታንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቁጥራቸውም | 12 |
17ዐሥረኛው ለሰሜኢ፣ ወጣ፤ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
18ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
19ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
20ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
21ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
22ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
23ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
24ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
25ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
26ዐሥራ ዘጠነኛው ለመሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘምዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
27ሃያኛው ለኤልያታ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
28ሃያ አንደኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
29ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
30ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት፣ ለወንዶች ልጆቹ ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12 |
31ሃያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ | |
ቊጥራቸውም | 12። |