ዳንኤል 6 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዳንኤል 6:1-28

ዳንኤል በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ

1ዳርዮስ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ እንዲገዙ አንድ መቶ ሃያ መሳፍንትን መሾም ፈለገ፤ 2በእነዚህም ላይ ሦስት የበላይ አስተዳዳሪዎችን አደረገ፤ ከእነርሱም አንዱ ዳንኤል ነበረ። ንጉሡ ጕዳት እንዳይደርስበት፣ መሳፍንቱ ተጠሪነታቸው ለሦስቱ የበላይ አስተዳዳሪዎች እንዲሆን ተደረገ። 3ከመሳፍንቱና ከበላይ አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ ይልቅ ዳንኤል ልዩ የጥበብ መንፈስ የሞላበት ሆኖ በመገኘቱ፣ ንጉሡ በመላው ግዛቱ ላይ ሊሾመው ዐሰበ። 4በዚህ ምክንያት የበላይ አስተዳዳሪዎቹና መሳፍንቱ ዳንኤል በሚያከናውነው የመንግሥት ሥራ ሊከስሱት ሰበብ ፈለጉ፤ ነገር ግን አላገኙበትም፤ ዳንኤል ታማኝ፣ ጠንቃቃና በሥራው እንከን የሌለበት ስለ ነበር፣ በእርሱ ላይ ስሕተት ሊያገኙ አልቻሉም። 5እነዚህም ሰዎች፣ “ከአምላኩ ሕግ ጋር በተያያዘ ጕዳይ ካልሆነ በቀር፣ ይህን ሰው የምንከስበት ምንም ሰበብ አናገኝበትም” አሉ።

6ከዚያም የበላይ አስተዳዳሪዎቹና መሳፍንቱ በአንድነት ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ! 7ንጉሥ ሆይ፤ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ ሌላ ሰውም ሆነ ወደ ሌላ አምላክ መጸለይ እንደሌለበት ንጉሡ ዐዋጅ እንዲያወጣ፣ ትእዛዙም እንዲፈጸም፣ ይህንም የተላለፈ ወደ አንበሶች ጕድጓድ እንዲጣል፣ የመንግሥት የበላይ አስተዳዳሪዎች፣ መኳንንት፣ መሳፍንት፣ አማካሪዎችና አገረ ገዦች ሁሉ በአንድነት ተስማምተዋል። 8ንጉሥ ሆይ፤ ይህን ዐዋጅ አውጣ፤ እንደማይሻረውና እንደማይለወጠው የሜዶንና የፋርስ ሕግ እንዲሆን ትእዛዙን በጽሑፍ አድርገው።” 9ስለዚህ ንጉሥ ዳርዮስ ዐዋጁ ተጽፎ እንዲወጣ አደረገ።

10ዳንኤልም ዐዋጁ እንደ ወጣ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፤ መስኮቶቹ በኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ባሉበት በሰገነቱ ቀድሞ ያደርግ እንደ ነበረው በቀን ሦስት ጊዜ ተንበርክኮ ጸለየ፤ አምላኩንም አመሰገነ። 11ሰዎቹም በአንድ ላይ ሄደው፣ ዳንኤልን ሲጸልይና አምላኩን ሲማጸን አገኙት። 12ወደ ንጉሡም ሄደው፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በሚቀጥሉት ሠላሳ ቀናት ማንም ሰው ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ወደ ሰውም ሆነ ወደ ማንኛውም አምላክ ቢጸልይ፣ በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ እንደሚጣል ዐዋጅ አውጥተህ አልነበረምን?” ሲሉ እርሱ ስላወጣው ዐዋጅ ጠየቁት።

ንጉሡም፣ “ዐዋጁ እንደማይሻረው እንደ ሜዶንና እንደ ፋርስ ሕግ የጸና ነው” ሲል መለሰ።

13እነርሱም ንጉሡን፣ “ንጉሥ ሆይ፤ ከይሁዳ ምርኮኞች አንዱ የሆነው ዳንኤል፣ አንተንም ሆነ በጽሑፍ ያወጣኸውን ዐዋጅ አያከብርም፤ አሁንም በቀን ሦስት ጊዜ ወደ አምላኩ ይጸልያል” አሉት። 14ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ዐዘነ፤ ዳንኤልን ለማዳን ወሰነ፤ ፀሓይ እስክትጠልቅም ድረስ የተቻለውን ሁሉ አደረገ።

15ከዚያም ሰዎቹ በአንድ ላይ ወደ ንጉሡ ቀርበው፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በሜዶንና በፋርስ ሕግ መሠረት፣ አንድ ንጉሥ ያወጣው ዐዋጅም ሆነ ትእዛዝ ሊለወጥ እንደማይችል ዕወቅ” አሉት። 16ስለዚህ ንጉሡ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም ዳንኤልን አመጡት፤ ወደ አንበሶችም ጕድጓድ ጣሉት። ንጉሡም ዳንኤልን፣ “ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ያድንህ” አለው።

17ድንጋይ አምጥተው በጕድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙበት፤ ንጉሡም፣ በዳንኤል ላይ የተፈጸመው እንዳይለወጥ በራሱ የቀለበት ማኅተምና በመሳፍንቱ ቀለበቶች ዐተመበት። 18ንጉሡም ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ በዚያም ሌሊት ምግብ ሳይበላ፣ የሚያዝናናውም ነገር ሳይቀርብለት ዐደረ፤ እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ።

19በማለዳም ገና ጎሕ ሲቀድ፤ ንጉሡ ተነሥቶ ወደ አንበሶቹ ጕድጓድ እየተጣደፈ ሄደ። 20ወደ ጕድጓዱም ቀርቦ በሐዘን ድምፅ ዳንኤልን፣ “የሕያው አምላክ አገልጋይ ዳንኤል ሆይ፤ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶቹ ሊያድንህ ችሏልን?” ብሎ ተጣራ።

21ዳንኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፤ 22ንጉሥ ሆይ፤ በፊቱ ቅን ሆኜ ስለ ተገኘሁ፣ በአንተም ፊት በደል ስላልተገኘብኝ፣ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጐዱኝም።”

23ንጉሡ እጅግ ተደስቶ፤ ዳንኤልን ከጕድጓዱ እንዲያወጡት አዘዘ። ዳንኤል በአምላኩ ታምኖ ነበርና ከጕድጓድ በወጣ ጊዜ፣ አንዳች ጕዳት አልተገኘበትም።

24በንጉሡ ትእዛዝ፣ ዳንኤልን በሐሰት የከሰሱትን ሰዎች፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር አምጥተው፣ በአንበሶቹ ጕድጓድ ውስጥ ጣሏቸው፤ ገና ወደ ጕድጓዱ መጨረሻ ሳይደርሱም፣ አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።

25ከዚያ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ፣ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝቦች፣ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ሰዎች ሁሉ እንዲህ የሚል መልእክት ጻፈ፤

“ሰላም ይብዛላችሁ!

26“በማንኛውም የመንግሥቴ ግዛት ሰው ሁሉ፣ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር ይህን ዐዋጅ አውጥቻለሁ።

“እርሱ ለዘላለም የሚኖር፣

ሕያው አምላክ ነውና፣

መንግሥቱ አይጠፋም፤

ለግዛቱም መጨረሻ የለውም።

27እርሱ ይታደጋል፤ ያድናልም፤

በሰማይና በምድር፣

ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋል፤

ዳንኤልን፣

ከአንበሶች አፍ አድኖታል።”

28ስለዚህ ዳንኤል በዳርዮስ ዘመነ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ ዘመነ መንግሥት ሁሉ ኑሮው ተሳካለት።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

但以理書 6:1-28

但以理在獅子坑

1大流士決定設立一百二十個總督治理全國。 2總督之上,設三個總長,以維護王的統治,但以理是其中之一。 3因為但以理有非凡的心智,遠超過其他總長和總督,王便考慮讓他治理全國。 4於是,其他總長和總督想在但以理的政務中找把柄控告他,卻找不到任何把柄或過失,因為他誠實可靠,毫無過失。 5最後他們說:「除非我們從但以理上帝的律法下手,否則找不到指控他的把柄。」

6於是,這些總長和總督齊來見王,說:「願大流士王萬歲! 7所有總長、行政官、總督、謀士和省長都認為王應該下一道禁令,三十天內,任何人不得向王以外的神明或人禱告,違者必被扔進獅子坑。 8王啊,求你頒佈、簽署這道禁令,使之不可更改,正如瑪代人和波斯人的律令是不可更改的。」 9於是大流士王簽署了這道禁令。

10但以理知道王簽署禁令後,就回到家裡。他樓上的窗戶朝向耶路撒冷,他像往常一樣每日三次跪下向上帝禱告、感恩。 11那些官員一同來了,發現但以理向他的上帝禱告、祈求, 12便去見王,提及王的禁令,說:「王啊,你不是簽署禁令,三十天內,任何人不得向王以外的神明或人禱告,違者必被扔進獅子坑嗎?」王說:「確有此事,按照瑪代人和波斯人的律,這禁令不可更改。」 13他們對王說:「王啊,被擄來的猶大但以理不理會你和你的禁令,仍一日三次向他的上帝祈禱。」 14王聽了這些話,十分愁煩,一心想救但以理,直到日落都在籌畫解救之道。 15那些人齊來見王,說:「王啊,按照瑪代人和波斯人的律,王頒佈的禁令和律例是不可更改的。」

16王便下令把但以理帶來扔進獅子坑。他對但以理說:「願你忠心事奉的上帝拯救你!」 17坑口用大石封住,並加上王和大臣的封印,使懲辦但以理的事不可更改。 18王回宮後,整夜禁食,拒絕娛樂,無法入睡。

19次日黎明,王起來匆忙趕往獅子坑, 20到了坑邊,淒聲呼喊但以理:「永活上帝的僕人但以理啊,你忠心事奉的上帝有沒有救你脫離獅子的口?」 21但以理對王說:「願王萬歲! 22我的上帝差遣天使封住了獅子的口,不讓牠們傷害我,因為我在上帝面前是清白的。王啊,我在你面前也沒有過錯。」 23王非常高興,便命人把但以理從坑中拉上來。於是,但以理從坑中被拉了上來,他因為信靠他的上帝,身上毫無損傷。 24王下令把那些惡意控告但以理的人及其兒女妻子都帶來,扔進獅子坑。他們還沒到坑底,獅子便撲上去,咬碎了他們的骨頭。

25後來,大流士王傳諭境內的各族、各邦、各語種的人,說:「願你們大享平安! 26我下令,我統治的國民都要敬畏但以理的上帝,

「因為祂是永活長存的上帝,

祂的國度永不滅亡,

祂的統治直到永遠。

27祂庇護、拯救,

在天上地下行神蹟奇事,

但以理脫離獅子的口。」

28因此,在大流士波斯塞魯士執政期間,但以理凡事亨通。