ዮሐንስ 16 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዮሐንስ 16:1-33

1“ይህን ሁሉ የነገርኋችሁ እንዳትሰናከሉ ነው። 2ከምኵራብ ያስወጧችኋል፤ እንዲያውም የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንዳገለገለ የሚቈጥርበት ጊዜ ይመጣል። 3ይህን ሁሉ የሚያደርጉባችሁ፣ አብን ወይም እኔን ስላላወቁ ነው። 4አስቀድሜ ይህን የነገርኋችሁ ጊዜው ሲደርስ እንድታስታውሱ ነው፤ ከእናንተ ጋር ስለ ነበርሁ፣ ይህን ከመጀመሪያው አልነገርኋችሁም።

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ

5“እንግዲህ ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ይሁን እንጂ ከእናንተ፣ ‘የምትሄደው የት ነው?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም። 6ይህን በመናገሬም ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል፤ 7ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መሄዴ ይበጃችኋል። እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ ከሄድሁ ግን እርሱን ወደ እናንተ እልካለሁ፤ 8በሚመጣበትም ጊዜ ዓለምን ስለ ኀጢአት16፥8 ወይም የዓለምን ኀጢአት ይገልጣል፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ይወቅሣል። 9ስለ ኀጢአት ሲባል፣ ሰዎች በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ 10ስለ ጽድቅ፣ ወደ አብ ስለምሄድና ከእንግዲህ ስለማታዩኝ ነው፤ 11ስለ ፍርድም፣ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።

12“ብዙ የምነግራችሁ ነበረኝ፤ አሁን ግን ልትሸከሙት አትችሉም። 13የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ ከራሱ አይናገርም፤ የሚሰማውን ብቻ ይናገራል፤ እንዲሁም ወደ ፊት ስለሚሆነው ይነግራችኋል፤ 14የእኔ ከሆነው ወስዶ እንድታውቁ በማድረግ ያከብረኛል። 15የአብ የሆነው ሁሉ የእኔ ነው፤ እንግዲህ፣ ‘የእኔ ከሆነው ወስዶ እንድታውቁ ያደርጋል’ ያልኋችሁ ለዚሁ ነው።

16“ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ይሁን እንጂ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ።”

የደቀ መዛሙርት ሐዘን ወደ ደስታ መለወጥ

17ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ፣ “ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ይሁን እንጂ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ እንዲሁም፣ ‘ወደ አብ ስለምሄድ’ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ተባባሉ፤ 18“ ‘ጥቂት ጊዜ’ ማለቱስ ምን ይሆን? የሚለውም ነገር አልገባንም” እያሉ ይጠያየቁ ነበር።

19ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ፈለጉ ባወቀ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ፣ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ይሁን እንጂ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ ስላልኋችሁ፣ ምን ማለቴ እንደ ሆነ እርስ በርሳችሁ ትጠያየቃላችሁ? 20እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝናላችሁም፤ ዓለም ግን ሐሤት ያደርጋል፤ ይሁን እንጂ ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል። 21ሴት ቀኗ ደርሶ ስትወልድ ትጨነቃለች፤ ከተገላገለች በኋላ ግን፣ ሰው ወደ ዓለም ስለ መጣ ጭንቋን ትረሳለች፤ 22ለእናንተም እንደዚሁ አሁን የሐዘን ጊዜ ነው፤ ሆኖም እንደ ገና ስለማያችሁ ደስ ይላችኋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። 23በዚያ ቀን ከእኔ ምንም አትለምኑም፤ እውነት እላችኋለሁ፤ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። 24እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ለምኑ ትቀበላላችሁ፤ ደስታችሁም ሙሉ ይሆናል።

25“እስከ አሁን የነገርኋችሁ በምሳሌ ቢሆንም እንኳ፣ ከእንግዲህ ግን ስለ አብ በምሳሌ ሳይሆን በግልጽ የምናገርበት ጊዜ ይመጣል። 26በዚያ ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ ይህም በእናንተ ፈንታ አብን እለምናለሁ ማለቴ አይደለም፤ 27ስለ ወደዳችሁኝና ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ ራሱ ይወድዳችኋል። 28ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ አሁን ግን ዓለምን ትቼ ወደ አብ እሄዳለሁ።”

29ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አሉ፤ “አሁንም እኮ ያለ ምሳሌ በግልጽ እየተናገርህ ነው። 30አሁን ሁሉን ነገር እንደምታውቅና ማንም ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ ተረድተናል፤ ይህም ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እንድናምን አድርጎናል።”

31ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንስ አመናችሁ ማለት ነው?16፥31 ወይም በስተ መጨረሻው አመናችሁ! 32እነሆ፤ ሁላችሁም በየፊናችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ጊዜ አሁን ነው። እኔንም ብቻዬን ትተዉኛላችሁ፤ ይሁን እንጂ አባቴ ከእኔ ጋር ስለሆነ ብቻዬን አይደለሁም።

33“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

約翰福音 16:1-33

聖靈的工作

1「我把這些事告訴你們,以免你們失去信心。 2人們將把你們趕出會堂;時候將到,殺害你們的人還以為是在事奉上帝。 3他們這樣做,是因為他們根本不認識父,也不認識我。 4我把這些事提前告訴你們,是要叫你們到時候可以想起我曾跟你們講過這些事。我以前沒有告訴你們,那是因為我還跟你們在一起。

5「現在我要去差我來的父那裡,你們沒有人問我去哪裡。 6因為我把這些事告訴了你們,你們心裡充滿了憂愁。 7然而,我把實情告訴你們,我去對你們是有益的,因為如果我不去,護慰者就不會來,我去了就會派祂到你們這裡來。 8祂來了,就要在罪、義、審判方面責備世人。 9在罪方面責備他們,是因為他們不信我; 10在義方面責備他們,是因為我要去父那裡,你們再也看不到我了; 11在審判方面責備他們,是因為這世界的王受了審判。

12「我還有許多事情要告訴你們,可是你們現在不能明白。 13等到真理之靈來了,祂會引導你們,讓你們明白一切的真理。祂不憑自己說話,而是把祂所聽見的和有關將來的事告訴你們。 14祂也要把從我那裡領受的指示你們,使我得榮耀。 15因為父的一切都是我的,所以我才說祂要把從我那裡領受的指示你們。

轉憂為喜

16「不久,你們就見不到我了,再過不久,你們還會看見我。」

17幾個門徒彼此議論說:「祂說,『不久,你們就見不到我了,再過不久,你們還會看見我』,祂又說,『因為我要去父那裡』,這到底是什麼意思呢? 18祂說『不久』是什麼意思呢?我們真不明白!」

19耶穌知道他們想問祂,就說:「你們在議論我剛才說的話是什麼意思嗎? 20我實實在在地告訴你們,你們將痛哭、哀號,世人卻要歡喜;你們將憂愁,然而你們的憂愁將變為喜樂。 21婦人分娩時都會痛苦不已,但孩子生下來後,她就會因為這世界添了一個新生命而充滿歡樂,忘掉了生產的痛苦。 22同樣,現在你們有憂愁,但到我再見你們的時候,你們的心必歡喜,而且這份喜樂是誰也奪不去的。

23「到那一天,你們就什麼也不用問我了。我實實在在地告訴你們,你們奉我的名無論向父求什麼,祂都會賜給你們。 24你們從來沒有奉我的名求過什麼,你們現在求,就必得到,好使你們的喜樂滿溢。

勝過世界

25「我一直用比喻跟你們講這些事,不久,我就不再用比喻了,而是清楚地把父的事告訴你們。 26到那天,你們將要奉我的名祈求,我不是說我要為你們向父祈求。 27父愛你們,因為你們一直愛我,並且相信我來自上帝。 28我從父那裡來到這個世界,現在我要離開這個世界回到父那裡。」

29門徒說:「如今你直截了當地告訴我們,不再用比喻了。 30現在我們知道你無所不知,無需人向你發問,因此我們相信你來自上帝。」

31耶穌說:「你們現在相信嗎? 32看啊!時候快到了,現在就是,你們將要分散,各自回家,只留下我一人。不過,我並非一人,因為父與我在一起。 33我把這些事告訴你們,是要叫你們在我裡面有平安。你們在世上會有苦難,但你們要放心,我已經勝過這個世界。」