ዮሐንስ 12 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዮሐንስ 12:1-50

ኢየሱስ በቢታንያ ሽቱ መቀባቱ

12፥1-8 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥6-13ማር 14፥3-9ሉቃ 7፥37-39

1የፋሲካ በዓል ስድስት ቀን ሲቀረው ኢየሱስ፣ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር ወደሚኖርበት፣ ወደ ቢታንያ መጣ። 2በዚያም ለኢየሱስ ሲባል እራት ተዘጋጀ። ማርታ ስታገለግል፣ አልዓዛር ከእርሱ ጋር በማእድ ከተቀመጡት አንዱ ነበር። 3ማርያምም ዋጋው ውድ የሆነ፣ ግማሽ ሊትር12፥3 በግሪኩ ሊትራን ይላል። ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ አምጥታ በኢየሱስ እግር ላይ አፈሰሰች፤ እግሩንም በጠጕሯ አበሰች፤ ቤቱንም የሽቱው መዓዛ ሞላው።

4ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ ኋላ አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ግን በመቃወም እንዲህ አለ፤ 5“ይህ ሽቱ በሦስት መቶ ዲናር ተሸጦ ገንዘቡ ለድኾች ለምን አልተሰጠም?” 6ይህን የተናገረው የገንዘብ ከረጢት ያዥ በመሆኑ፣ ከሚቀመጠው ለራሱ የሚጠቀም ሌባ ስለ ነበር እንጂ ለድኾች ተቈርቍሮ አልነበረም።

7ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “ይህ ሽቱ ለቀብሬ ቀን የታሰበ ስለሆነ እንድታቈየው ተዋት፤ 8ድኾች ምንጊዜም ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።”

9በዚህ ጊዜ ብዙ አይሁድ ኢየሱስ በዚያ መኖሩን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ኢየሱስን ብለው ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። 10ስለዚህ የካህናት አለቆች አልዓዛርን ጭምር ለመግደል ተማከሩ፤ 11ይህም በእርሱ ምክንያት ብዙ አይሁድ ወደ ኢየሱስ እየሄዱ ያምኑበት ስለ ነበር ነው።

ኢየሱስ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ

12፥12-15 ተጓ ምብ – ማቴ 21፥4-9ማር 11፥7-10ሉቃ 19፥35-38

12በማግስቱም ለበዓሉ የመጣው ብዙ ሕዝብ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየመጣ መሆኑን ሰሙ፤ 13የዘንባባም ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤

“ሆሣዕና!”12፥13 በዕብራይስጡ አድን! ማለት ሲሆን፣ የምስጋና ድምፅ ነው።

“በጌታ ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው!”

“የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው!”

14ኢየሱስም የአህያ ውርንጭላ አግኝቶ ተቀመጠበት፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤

15“የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አትፍሪ፤

እነሆ፤ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል

ተቀምጦ ይመጣል።”

16ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሁሉ በመጀመሪያ አላስተዋሉም፤ ስለ እርሱ የተጻፉትንና ለእርሱም የተደረጉትን ልብ ያሉት ኢየሱስ ከከበረ በኋላ ነበር።

17አልዓዛርን ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ባስነሣበት ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መነሣቱን ይመሰክሩ ነበር። 18ብዙ ሰዎችም ይህን ታምራዊ ምልክት ማድረጉን ስለ ሰሙ ሊቀበሉት ወጡ። 19ስለዚህም ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው፣ “እንግዲህ ምን ማድረግ ይቻላል? አያችሁ ዓለሙ ሁሉ ግልብጥ ብሎ ተከትሎታል” ተባባሉ።

ኢየሱስ ስለ ሞቱ አስቀድሞ ተናገረ

20ለአምልኮ ወደ በዓሉ ከወጡት መካከል የግሪክ ሰዎችም ነበሩ። 21እነርሱም በገሊላ ከምትገኘው ከቤተ ሳይዳ ወደ ሆነው ሰው፣ ወደ ፊልጶስ መጥተው፣ “ጌታው፤ እባክህን፣ ኢየሱስን ለማየት እንፈልጋለን” አሉት። 22ፊልጶስም፤ ለእንድርያስ ሊነግረው ሄደ፤ እንድርያስና ፊልጶስም ለኢየሱስ ነገሩት።

23ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የሰው ልጅ የሚከብርበት ሰዓቱ ደርሷል፤ 24እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። 25ሕይወቱን የሚወድድ ያጣታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን የሚጠላ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። 26የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝንም አባቴ ያከብረዋል።

27“አሁንስ ነፍሴ ተጨነቀች፤ ምን ልበል? አባት ሆይ፤ ከዚህች ሰዓት ብታድነኝስ? ይሁን፤ የመጣሁት ለዚህች ሰዓት ነውና። 28አባት ሆይ፤ ስምህን አክብረው።”

ከዚያም፣ “አክብሬዋለሁ፤ ደግሞም አከብረዋለሁ” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። 29በዚያ የነበሩት፣ ድምፁን የሰሙት አያሌ ሰዎች፣ “ነጐድጓድ ነው” አሉ፤ ሌሎች ደግሞ፣ “መልአክ ተናገረው” አሉ።

30ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “ይህ ድምፅ የመጣው ስለ እኔ ሳይሆን ስለ እናንተ ነው፤ 31ይህ ዓለም የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ የዚህም ዓለም ገዥ አሁን ወደ ውጭ ይጣላል። 32እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።” 33ይህን የተናገረው በምን ዐይነት ሞት እንደሚሞት ለማመልከት ነበር።

34ሕዝቡም፣ “እኛስ ክርስቶስ12፥34 ወይም መሲሕ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕግ ሰምተናል፤ ታዲያ፣ ‘የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ ‘የሰው ልጅ’ ማን ነው?” አሉት።

35ኢየሱስም እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤ “ከእንግዲህ ለጥቂት ጊዜ ብርሃን አለላችሁ፤ ጨለማ ሳይመጣባችሁ፣ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም። 36የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በዚህ ብርሃን እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ተናግሮ እንደ ጨረሰ ተለያቸው፤ ተሰወረባቸውም።

አይሁድ ባለማመን መጽናታቸው

37ኢየሱስ እነዚህን ታምራዊ ምልክቶች ሁሉ በፊታቸው ቢያደርግም እንኳ፣ አሁንም አላመኑበትም፤ 38ይኸውም ነቢዩ ኢሳይያስ፣

“ጌታ ሆይ፤ ምስክርነታችንን ማን አመነ?

የጌታ ክንድስ ለማን ተገለጠ?”

ያለው ቃል እንዲፈጸም ነው።

39ስለዚህ ማመን አልቻሉም፤ ይህም ኢሳይያስ በሌላ ቦታ እንዲህ ሲል እንደ ተናገረው ነው፤

40“ዐይናቸውን አሳውሯል፤

ልባቸውንም አደንድኗል፤

ስለዚህ በዐይናቸው አያዩም፤

በልባቸውም አያስተውሉም፤

እንዳልፈውሳቸውም አይመለሱም።”

41ኢሳይያስ ይህን ያለው የኢየሱስን ክብር ስላየ ነው፤ ስለ እርሱም ተናገረ።

42ይህም ቢሆን፣ ከአለቆች መካከል እንኳ ሳይቀር ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ይሁን እንጂ ፈሪሳውያን ከምኵራብ እንዳያስወጧቸው ስለ ፈሩ ማመናቸውን አይገልጡም ነበር። 43ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ከመመስገን ይልቅ በሰው መመስገንን ስለ ወደዱ ነው።

44ከዚያም ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “ማንም በእኔ ቢያምን በእኔ ብቻ ሳይሆን በላከኝም ማመኑ ነው፤ 45እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል። 46በእኔ የሚያምን በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።

47“ቃሌን ሰምቶ በማይፈጽመው ላይ የምፈርደው እኔ አይደለሁም፤ ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ላይ ልፈርድ አልመጣሁምና። 48በማይቀበለኝና ቃሌን በሚያቃልል ላይ የሚፈርድበት አለ፤ የተናገርሁት ቃል ራሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል፤ ምክንያቱም 49እኔ ከራሴ አልተናገርሁም፤ ነገር ግን የላከኝ አብ ምን እንደምናገርና እንዴት እንደምናገር አዘዘኝ። 50የእርሱ ትእዛዝ ወደ ዘላለም ሕይወት እንደሚያደርስ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም የምለው ሁሉ አብ እንድናገረው የነገረኝን ብቻ ነው።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约翰福音 12:1-50

香膏抹脚

1逾越节前六天,耶稣来到伯大尼,就是祂叫拉撒路从死里复活的村子。 2村里有人为耶稣预备了晚饭,拉撒路也与耶稣同席,玛大在旁边伺候。 3玛丽亚拿出一瓶12:3 一瓶”希腊文是“一罗马磅”,约325克。珍贵的纯哪哒香膏来抹耶稣的脚,又用自己的头发去擦,屋里顿时充满了香气。

4有一个门徒,就是将要出卖耶稣的加略犹大说: 5“为什么不把香膏卖三百个银币12:5 三百个银币”相当于当时一个人一年的工钱。去周济穷人呢?” 6他这样说不是因为他真的关心穷人,其实他是个贼,常常借管钱的机会中饱私囊。

7耶稣说:“由她吧!她这是为我安葬作预备。 8因为你们身边总会有穷人,可是你们身边不会总有我。”

9有许多犹太人知道耶稣在那里,就来看祂,不单是为了看耶稣,也想看看从死里复活的拉撒路10于是,祭司长计划连拉撒路也杀掉, 11因为有许多犹太人因为拉撒路的缘故离开他们,去信了耶稣。

光荣进圣城

12第二天,很多上来过节的人听见耶稣快到耶路撒冷了, 13就拿着棕树枝出去迎接祂,并且高声欢呼:

“和散那12:13 和散那”原意是“拯救我们”,此处有“赞美”的意思。

奉主名来的以色列王当受称颂!”

14那时,耶稣找到一头驴驹,就骑上它,正如圣经记载:

15锡安的居民啊,不要害怕!

你的君王骑着驴驹来了。”

16起初门徒不明白这些事,后来耶稣得了荣耀,他们才想起圣经上这些有关耶稣的记载果然在祂身上应验了。 17那些亲眼看见耶稣叫拉撒路复活、走出坟墓的人不断传扬这件事。 18许多听过耶稣行这神迹的人都去迎接祂。 19法利赛人彼此议论说:“我们真是枉费心思!你看,整个世界都跟着祂跑了。”

耶稣预言自己的死

20有几个希腊人也上耶路撒冷过节。 21他们找到了加利利伯赛大腓力,请求说:“先生,我们想见见耶稣。” 22腓力把这件事告诉安得烈,二人去转告耶稣。

23耶稣说:“人子得荣耀的时候到了。 24我实实在在地告诉你们,一粒麦子如果不落在地里死了,仍是一粒,如果死了,就会结出许多麦粒来。 25爱惜自己生命的,必会失掉生命;憎恶自己今世生命的,才能保住生命,直到永生。 26谁要事奉我,就要跟从我。我在哪里,事奉我的人也要在哪里。我父必尊重事奉我的人。

27“我现在心里忧伤,说什么才好呢?求父救我离开这个时刻吗?然而,我原是为这个时刻来的。 28父啊!愿你使自己的名得荣耀!”

当时天上有声音说:“我已使自己的名得了荣耀,并且还要得荣耀。”

29站在那里的人群中有人听见就说:“打雷了!”也有人说:“是天使在跟祂说话。”

30耶稣说:“这声音不是为我发出的,是为你们发出的。 31现在是这世界受审判的时候,世界的王12:31 世界的王”指“魔鬼,又名撒旦”,参见路加福音10:18歌罗西书2:15约翰一书3:8要被赶出去了。 32至于我,当我从地上被举起来时,必吸引万人归向我。” 33耶稣这句话指的是祂会怎样死。

34众人问:“我们从律法书上知道,基督是永远长存的,你怎么说‘人子要被举起来’呢?这人子是谁呢?”

35耶稣对他们说:“光在你们中间照耀的时候不多了,你们要趁着有光的时候走路,免得黑暗来临后,走在黑暗里的人不知道要往哪里去。 36所以你们当趁着有光的时候信从光,好成为光明的儿女。”

耶稣说完后,便离开他们,隐藏起来。

犹太人不信祂

37耶稣虽然在他们面前行了许多神迹,他们还是不信祂。 38这是要应验以赛亚先知的话:

“主啊,谁相信我们所传的呢?主的能力12:38 主的能力”希腊文是“主的臂膀”,参见以赛亚书53:1向谁显现呢?”

39接着,以赛亚又说出他们不能信的缘故:

40“主使他们眼瞎、心硬,

免得他们眼睛看见,

心里明白,回心转意,

就得到我的医治。”

41以赛亚看见了祂的荣耀,所以才这样说。 42虽然这样,仍有很多犹太的官员信了耶稣,只是在法利赛人面前不敢公开承认,因为害怕会被赶出会堂。 43因为他们爱从世人而来的荣耀,胜过爱从上帝而来的荣耀。

耶稣的道要审判人

44耶稣高声说:“信我的,其实不只是信我,而是信差我来的那位。 45人看见了我,就是看见了差我来的那位。 46我来是要作世界的光,好叫信我的人脱离黑暗。 47听了我的话却不遵守的人,我不审判他,因为我来不是要审判世人,而是要拯救世人。 48弃绝我、不接受我话的人将受到审判,我讲过的道在末日要审判他, 49因为我不是凭自己讲的,我说什么、讲什么都是差我来的父吩咐的。 50我知道祂的命令能带来永生。所以祂怎么告诉我,我就怎么说。”