ዘፍጥረት 9 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 9:1-29

እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር የገባው ኪዳን

1እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤ 2አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በዱር አራዊት፣ በሰማይ አዕዋፍ፣ በደረት በሚሳቡ ተንቀሳቃሽ ፍጡሮችና በባሕር ዓሦች ሁሉ ላይ ይሁን፤ በእጃችሁ ተሰጥተዋል። 3ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፤ ለምለሙን ዕፀዋት እንደ ሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ።

4“ነገር ግን ሕይወቱ፣ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ። 5ሰውን የገደለ ሁሉ ስለ ሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ፣ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ።

6“የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ፣

ደሙ በሰው እጅ ይፈስሳል፤

በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) አምሳል፣

እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰውን ሠርቶታልና።

7እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ፤ ይንሰራፋ።”

8እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅንና አብረውት ያሉትን ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ 9“እነሆ፤ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ 10እንዲሁም ከእናንተ ጋር ከነበሩት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፦ ከወፎች፣ ከቤት እንስሳት፣ ከዱር እንስሳት፣ ከእናንተ ጋር ከመርከቧ ከወጡት በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ኪዳን እገባለሁ። 11ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋር ኪዳን እገባለሁ።”

12እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለ፤ “በእኔና በእናንተ መካከል፣ ከእናንተም ጋር ካሉ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋር፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤ 13ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል። 14ደመናን በምድር ላይ በጋረድሁና ቀስቴም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ፣ 15ከእናንተና ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም። 16ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ፣ በእኔና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጡራን መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን ዐስባለሁ።”

17ስለዚህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅን፣ “ይህ በእኔና በምድር ላይ በሚኖሩ ሕያዋን ሁሉ መካከል የገባሁት ኪዳን ምልክት ነው” አለው።

የኖኅ ልጆች

18ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበሩ፤ ካም የከነዓን አባት ነው። 19ሦስቱ የኖኅ ልጆች እነዚህ ሲሆኑ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚሁ ነው።

20ኖኅ ገበሬ ነበረና ወይን ተከለ፤9፥20 ወይም የመጀመሪያ ነበር 21ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ ዕርቃኑን ተኛ። 22የከነዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። 23ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ።

24ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፣ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ 25እንዲህም አለ፤

“ከነዓን የተረገመ ይሁን፤

ለወንድሞቹም፣ የባሪያ ባሪያ ይሁን።”

26ደግሞም፤

“የሴም አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይባረክ፤

ከነዓንም የሴም9፥26 ወይም የእርሱ ባሪያ ይሁን ባሪያ ይሁን።

27እግዚአብሔር (ኤሎሂም) የያፌትን9፥27 ያፌት የሚለው ቃል መዘርጋት የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው። ግዛት ያስፋ፤

ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤

ከነዓንም የእርሱ9፥27 ወይም የእነርሱ ባሪያ ይሁን” አለ።

28ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ፤ 29ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖሮ ሞተ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 9:1-29

上帝與挪亞立約

1上帝賜福給挪亞和他的兒子們,對他們說:「你們要生養眾多,遍佈地面。 2你們要管理所有地上的走獸、空中的飛鳥、地上的爬蟲和海裡的魚,牠們都必懼怕你們。 3凡是活著的動物都可作你們的食物,就像菜蔬和穀物一樣。 4只是你們不可吃帶血的肉,因為血就是生命。 5凡是殺人害命的,無論人或獸,我必向他們追討血債。凡殺人的,我必追討他的血債。 6凡殺害人的,也必被人殺害,因為人是上帝照著自己的形像造的。 7你們要生養眾多,使地上人口興旺。」

8上帝又對挪亞和他的兒子們說: 9「我要跟你們和你們的後代, 10以及所有和你們在一起、從方舟出來的飛禽走獸和牲畜等各種動物立約。 11我與你們立約,不再叫洪水淹沒一切生靈,也不再讓洪水毀滅大地。」 12上帝說:「我與你們及各種生靈立世代永存的約,我要給這個約一個記號。 13我把彩虹放在雲中,作為我跟大地立約的記號。 14我使雲彩覆蓋大地的時候,會有彩虹在雲中出現。 15這樣我會記得我與你們及一切生靈所立的約,水就不會再氾濫淹滅所有生靈。 16當我看見彩虹在雲中出現的時候,就會記得我與地上一切生靈立的永約。」 17上帝對挪亞說:「彩虹是我與地上一切生靈立約的記號。」

挪亞和他的兒子

18挪亞一起出方舟的有他的兒子雅弗迦南的父親。 19挪亞這三個兒子的後代遍佈天下。

20挪亞做了農夫,他是第一個栽種葡萄園的人。 21一天,他喝葡萄酒喝醉了,赤裸著身體躺在帳篷裡。 22迦南的父親看見他父親赤身露體,便去告訴外面的兩個弟兄。 23於是,雅弗拿了一件衣服搭在肩上,倒退著走進帳篷,把衣服蓋在父親身上,他們背著臉不看父親赤裸的身體。

24挪亞酒醒後,知道了小兒子做的事, 25就說:

迦南該受咒詛,

必做他弟兄的僕人的僕人。」

26又說:

的上帝耶和華當受稱頌!

迦南要做的僕人。

27願上帝擴張雅弗的疆界,

願他住在的帳篷裡,

迦南做他的僕人。」

28洪水以後,挪亞又活了三百五十年。 29挪亞一生共活了九百五十歲。