ዘፍጥረት 6 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 6:1-22

የጥፋት ውሃ

1ሰዎች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። 2የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወንዶች ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ውብ ሆነው አዩአቸው፤ ከመካከላቸውም የመረጧቸውን አገቡ። 3እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “ሰው ሟች6፥3 ወይም በስባሽ ስለሆነ መንፈሴ እያዘነ6፥3 ወይም መንፈሴ አይኖርም ከእርሱ ጋር ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜው 120 ዓመት ይሆናል” አለ።

4የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ተገናኝተው ልጆች በወለዱ ጊዜም ሆነ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንቱ ዘመን በጀግንነታቸው ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ ናቸው።

5እግዚአብሔር (ያህዌ) አምላክ የሰው ዐመፅ በምድር ላይ የበዛና የልቡም ሐሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ። 6እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ ልቡም እጅግ ዐዘነ። 7ስለዚህም እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ “የፈጠርሁትን የሰው ዘር ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን እስከ ሰማይ ወፎች አጠፋለሁ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ። 8ኖኅ ግን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘንድ ሞገስን አገኘ።

9የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ አካሄዱንም ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር አደረገ።

10ኖኅም ሴም፣ ካምና ያፌት የሚባሉ ሦስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።

11ምድር በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች፤ በዐመፅም ተሞላች። 12እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ምድር ምን ያህል በክፉ ሥራ እንደ ረከሰች አየ። እነሆ፤ ሰው ሁሉ አካሄዱን አበላሽቶ ነበርና 13ስለዚህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅን እንዲህ አለው፦ “ሰውን ሁሉ ላጠፋ ነው፤ ምድር በሰው ዐመፅ ስለ ተሞላች በርግጥ ሰውንም ምድርንም አጠፋለሁ። 14አንተ ግን በጎፈር6፥14 በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም። ዕንጨት መርከብ ሥራ፤ ለመርከቧም ክፍሎች አብጅላት፤ ውስጧንና ውጭዋን በቅጥራን ለብጠው። 15እንዲህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ 140 ሜትር፣ ወርዷ 23 ሜትር፣ ከፍታዋ 13.5 ሜትር ይሁን። 16ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤6፥16 ወይም ለብርሃን መግቢያ አድርገህ ሥራ ከጐኗ በር አውጣላት፤ ባለ ሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት። 17እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸውን ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ለማጥፋት እነሆ፤ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል። 18ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እመሠርታለሁ። አንተና ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ። 19ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲቈዩ ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ተባዕትና እንስት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ። 20ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ። 21ለአንተና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ አከማች።”

22ኖኅም ሁሉን እግዚአብሔር (ኤሎሂም) እንዳዘዘው አደረገ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

创世记 6:1-22

人类的邪恶

1人类在地上逐渐增多,生了女儿。 2上帝的儿子们6:2 上帝的儿子”可能指塞特的后代,天使或有权势的人。看见人的女儿漂亮,就随意选来做妻子。 3耶和华说:“人既然是血肉之躯,我的灵不会永远住在人的里面,然而人还可以活一百二十年。” 4从那时起,地上出现了一些巨人,他们是上古有名的勇士,是上帝的儿子和人的女儿所生的后代。

5耶和华看见人罪恶深重,心中终日思想恶事, 6就后悔在地上造了人,心里伤痛, 7说:“我要把所造的人从地上除掉,连同一切飞禽走兽和爬虫都除掉,我后悔造了他们。” 8只有挪亚在耶和华面前蒙恩。

上帝命挪亚造方舟

9以下是有关挪亚的记载。

挪亚是个义人,在当时的世代是个纯全无过的人,他与上帝同行。 10挪亚生了三个儿子:雅弗

11当时的世界在上帝眼中非常败坏,充满了暴行。 12上帝看见世界败坏了,因为世人行为败坏。 13祂对挪亚说:“世人恶贯满盈,他们的结局到了。我要把他们跟大地一起毁灭。 14你要为自己用歌斐木建造一艘方舟,里面要有舱房,内外都要涂上柏油。 15你建造的方舟要长一百三十三米,宽二十二米,高十三米。 16舟顶要有五十厘米高的透光口,门开在方舟的侧面,整艘方舟要分为上、中、下三层。 17看啊,我要使洪水在地上泛滥,毁灭天下。地上一切有气息的生灵都要灭亡。 18但我要跟你立约,你与妻子、儿子和儿媳都可以进方舟。 19每种动物你要带两只进方舟,雌雄各一只,好保存它们的生命。 20各种飞禽走兽和爬虫要按种类每样一对到你那里,好保住生命。 21你要为自己和这些动物预备各种食物,贮存起来。”

22挪亚就照着上帝的吩咐把事情都办好了。