ዘፍጥረት 45 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 45:1-28

ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን ገለጠ

1በዚያን ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩ ሰዎች ፊት ስሜቱን ሊገታ ባለመቻሉ፣ “እዚህ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፤ ስለዚህም ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም። 2ዮሴፍም ድምፁን ከፍ አድርጎ በማልቀሱ፣ ግብፃውያን ሰሙት፤ ወሬውም ወደ ፈርዖን ቤተ ሰዎች ደረሰ።

3ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለ ነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም።

4ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በሉ” አላቸው፤ ወደ እርሱም በቀረቡ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ ወንድማችሁ እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ 5አሁንም በመሸጣችሁ አትቈጩ፤ በራሳችሁም አትዘኑ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሕይወት ለማዳን ሲል ከእናንተ አስቀድሞ እኔን ወደዚህ ልኮኛል። 6በምድር ላይ ራብ ከገባ ይኸው ሁለት ዓመት ሆነ፤ ከዚህ በኋላም የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና አሉ። 7ነገር ግን እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሕይወታችሁን በታላቅ ማዳን ለመታደግና45፥7 ወይም በሕይወት እንደ ተረፉ ታላቅ ሰራዊት ለመታደግ ዘራችሁ ከምድር ላይ እንዳይጠፋ በማሰብ ከእናንተ አስቀድሞ ወደዚህ ላከኝ።

8“ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፣ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብፅ ምድር ላይ ገዥ አደረገኝ። 9አሁንም በፍጥነት ወደ አባቴ ተመልሳችሁ እንዲህ በሉት፤ ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር (ኤሎሂም) የመላው ግብፅ ጌታ አድርጎኛል፤ ስለዚህ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና። 10ልጆችህን፣ የልጅ ልጆችህን፣ በጎችህን፣ ፍየሎችህን፣ ከብቶችህንና ያለህን ሁሉ ይዘህ በአቅራቢያዬ በጌሤም ትኖራለህ። 11ገና ወደ ፊት የሚመጣ የአምስት ዓመት ራብ ስላለ፣ በዚያ የሚያስፈልጋችሁን እኔ እሰጣችኋለሁ፤ ያለበለዚያ ግን አንተና ቤተ ሰዎችህ ያንተም የሆነው ሁሉ፣ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።’

12“ፊታችሁ ሆኜ የማናግራችሁ እኔ ዮሴፍ ራሴ መሆኔን እናንተም ሆናችሁ ወንድሜ ብንያም በዐይናችሁ የምታዩት ነው። 13በግብፅ ስላለኝ ክብርና ስላያችሁትም ሁሉ ለአባቴ ንገሩት፤ አባቴንም በፍጥነት ይዛችሁት ኑ።”

14ከዚያም በወንድሙ በብንያም ዐንገት ላይ ተጠምጥሞ አለቀሰ፤ ብንያምም እያለቀሰ ዮሴፍን ዐቀፈው። 15የቀሩትንም ወንድሞቹን አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ። ከዚያም ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መጨዋወት ጀመሩ።

16የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ፣ ፈርዖንና ሹማምቱ ሁሉ ደስ አላቸው። 17ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ለወንድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እንዲህ አድርጉ፤ አህዮቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከነዓን ምድር ተመለሱ። 18ከዚያም አባታችሁንና ቤተ ሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብፅ ምድር እሰጣችኋለሁ፤ በምድሪቱ በረከት ደስ ብሏችሁ ትኖራላችሁ።’

19“ደግሞም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ይህን አድርጉ፤ ከግብፅ ምድር ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጕዙበት ሠረገላዎች ወስዳችሁ፣ አባታችሁን ይዛችሁት ኑ። 20ስለ ንብረታችሁ ምንም አታስቡ፤ ከግብፅ ምድር እጅግ ለም የሆነው የእናንተ ይሆናልና።’ ”

21የእስራኤልም ልጆች ይህንኑ አደረጉ። ዮሴፍም ፈርዖን ባዘዘው መሠረት ሠረገላዎች አቀረበላቸው፤ የመንገድም ስንቅ አስያዛቸው። 22ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን ሦስት መቶ ጥሬ ብርና አምስት የክት ልብስ ሰጠው። 23ለአባቱም በግብፅ ምድር ከሚገኘው የተመረጠ ነገር በዐሥር አህዮች፣ እንደዚሁም ለመንገዱ ስንቅ የሚሆነው እህል፣ ዳቦና ሌላ ምግብ በዐሥር እንስት አህዮች አስጭኖ ሰደደለት። 24ከዚህ በኋላ ወንድሞቹን አሰናበታቸው፤ ከእርሱም ሲሰናበቱ፣ “መንገድ ላይ እንዳትጣሉ!” አላቸው።

25እነርሱም ከግብፅ ወጥተው በከነዓን ምድር ወደሚኖረው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ መጡ። 26አባታቸውንም፣ “እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብፅ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኗል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብም በድንጋጤ ክው አለ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም። 27ነገር ግን ዮሴፍ የነገራቸውን ሁሉ ሲያጫውቱትና እርሱንም ወደ ግብፅ ለማጓጓዝ ዮሴፍ የላከለትን ሠረገላዎች ሲያይ የአባታቸው የያዕቆብ መንፈስ ታደሰ። 28ከዚያም እስራኤል፤ “ልጄ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ ከመሞቴ በፊት ሄጄ ልየው” አለ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 45:1-28

約瑟與弟兄相認

1約瑟再也控制不住自己,於是令所有的隨從都出去。這樣,約瑟跟弟兄們相認時,沒有外人在場。 2約瑟放聲大哭,埃及人聽見了他的哭聲,法老家也聽到了這個消息。 3約瑟對他的弟兄們說:「我是約瑟!我的父親還健在嗎?」他的弟兄們嚇得一句話也說不出來。

4約瑟叫他們走近一點,等他們靠近了,便說:「我是你們賣到埃及的弟弟約瑟5現在,你們不要因為把我賣到這裡而自怨自責。上帝差我先來這裡,是為了保住大家的性命。 6地上的饑荒已經兩年了,我們還有五年不能種、不能收。 7上帝差我先來,是要為你們保留後代,又要大施拯救,保住你們的性命。 8這樣看來,不是你們,是上帝把我送到這裡的。祂使我成為法老的宰相,管理他的家和整個埃及9你們快回去告訴父親,他兒子約瑟說,『上帝已經使我管理整個埃及,請他立刻來這裡。 10他可以帶著他的子孫、牛羊及一切所有住在歌珊。那裡離我很近, 11我可以奉養他,以免他和全家老少及僕婢牲畜都陷入絕境,因為還有五年的饑荒。』 12你們和我弟弟便雅憫都看見了,這是我親口對你們說的。 13你們要把我在埃及享有的尊榮和你們見到的一切都告訴父親,儘快把他接來。」 14約瑟和弟弟便雅憫抱頭痛哭, 15然後又親吻其他弟兄,抱著他們痛哭,弟兄們跟他交談起來。

16約瑟弟兄們到來的消息傳到法老的王宮,法老和他的臣僕都為約瑟感到高興。 17法老對約瑟說:「你去吩咐你的弟兄備好驢回迦南18把你們的父親和家眷都接到我這裡。我要把埃及最好的土地賜給他們,讓他們享受這裡肥美的物產。 19吩咐你的弟兄從埃及帶著車去把他們的妻子、兒女和你們的父親接來。 20不要擔心你們在迦南的產業,因為埃及全國的美物都是你們的。」

21以色列的兒子們答應了。約瑟遵照法老的吩咐,為他的弟兄們預備好車輛和路上需用的糧食, 22又給他們每人一套新衣服,但給了便雅憫五套新衣服和三百塊銀子。 23約瑟送給父親十頭公驢,馱著埃及的美物,還送了十頭母驢,馱著糧食、餅和其他食物,讓父親路上用。 24約瑟送弟兄們回去,囑咐他們路上不要爭吵。

25於是,他們離開埃及回到在迦南的父親雅各那裡, 26對父親說:「約瑟還活著,並且做了埃及的宰相。」雅各驚呆了,不敢相信他們的話。 27雅各聽了他們轉述約瑟的話,又看見約瑟派來接他的車,才回過神來。 28以色列說:「我信了!我兒約瑟還活著,我要在死之前去見他。」