ዘፍጥረት 39 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 39:1-23

ዮሴፍና የጲጥፋራ ሚስት

1በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖን ሹማምት አንዱ የሆነውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብፃዊው ጲጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው።

2እግዚአብሔር (ያህዌ) ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ኑሮው ተቃናለት፤ እርሱም በግብፃዊው አሳዳሪው ቤት ኖረ። 3አሳዳሪውም እግዚአብሔር (ያህዌ) ከእርሱ ጋር እንዳለና ሥራውንም ሁሉ እንዳከናወለት ባየ ጊዜ፣ 4ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፤ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፤ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኀላፊነት ሰጠው። 5ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) የግብፃዊውን ቤት ባረከ፤ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ። 6ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፤ የቀረበለትንም ከመመገብ በስተቀር፣ ማናቸውንም ጕዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር።

ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ መልካም ነበር፤ 7እያደርም የጌታው ሚስት ዐይኗን ጣለችበት፤ አፍ አውጥታም፣ “አብረኸኝ ተኛ” አለችው።

8እርሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኀላፊነት ስለ ሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። 9በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኀላፊነት ያለው ማንም የለም፤ እርሱ ያልሰጠኝ ነገር ቢኖር፣ አንቺን ብቻ ነው፤ ያውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ፣ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ እንዴት በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፊት ኀጢአት እሠራለሁ?” 10ምንም እንኳ ዮሴፍን በየቀኑ ብትጐተጕተውም፣ አልሰማትም፤ ከእርሷ ጋር መተኛት ይቅርና አብሯትም መሆን አልፈቀደም።

11አንድ ቀን ዮሴፍ የዕለት ተግባሩን ለማከናወን ወደ ቤት ገባ፤ ከቤቱ አገልጋዮችም አንድም ሰው በቤት ውስጥ አልነበረም። 12እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ።

13እርሷም ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ መውጣቱን ባየች ጊዜ፣ 14የቤት አገልጋዮቿን ጠራች፤ እንዲህም አለቻቸው፤ “አያችሁ፤ ለካስ ይህ ዕብራዊ የመጣው መሣለቂያ ሊያደርገን ኖሯል! እዚህ ድረስ ሰተት ብሎ ገብቶ ካልተኛሁሽ አለኝ፤ እኔም ጩኸቴን ለቀቅሁት፤ 15ለርዳታ መጮኼን ሲሰማም፣ ልብሱን ከአጠገቤ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ።”

16ጌታውም ወደ ቤት እስኪመለስ ድረስ፣ ልብሱን አጠገቧ አቈየችው። 17ታሪኩንም እንዲህ ስትል ነገረችው፤ “አንተ ያመጣኸው ዕብራዊ ባሪያ መሣቂያ ሊያደርገን ወዳለሁበት ሰተት ብሎ ገባ፤ 18ታዲያ እኔ ድረሱልኝ ብዬ ስጮኽ ልብሱን አጠገቤ ጥሎ ሸሽቶ ወጣ።”

19ጌታውም፣ “ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ ተቈጣ። 20ጌታውም ዮሴፍን ወስዶ፣ የንጉሥ እስረኞች ወደ ተጋዙበት እስር ቤት አስገባው።

21ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፤ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው። 22ስለዚህ የወህኒው አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች ሁሉ አለቃ አደረገው፤ በእስር ቤቱ ላለውም ነገር ሁሉ ኀላፊ ሆነ። 23እግዚአብሔር (ያህዌ) ከዮሴፍ ጋር ሆኖ ሥራውን ሁሉ ያሳካለት ስለ ነበር፣ የወህኒ ቤት አዛዡ በዮሴፍ ኀላፊነት ሥር ስላለው ስለ ማንኛውም ጕዳይ ሐሳብ አይገባውም ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 39:1-23

約瑟遭陷害

1約瑟以實瑪利商人帶到埃及,賣給了法老的內臣護衛長波提乏2約瑟住在他的埃及主人家中,耶和華與他同在,使他凡事亨通。 3他主人看出耶和華與他同在,使他凡事亨通, 4就賞識他,讓他服侍自己,派他管理自己家中一切事務。 5自從埃及波提乏約瑟管理自己家中一切事務以後,耶和華因為約瑟的緣故而賜福他主人家,使他主人家裡和田間的一切都蒙福。 6於是,波提乏把一切事都交給約瑟管理,除了自己要吃的食物以外,什麼也不管。

約瑟體格健壯,相貌英俊。 7後來,波提乏的妻子看中了約瑟,向他眉目傳情,要引誘他上床。 8約瑟拒絕了她,說:「我主人信任我,把家裡一切事都交給我管理。 9在這家裡,沒有人比我權力更大了,我主人把一切都交給了我,唯獨你除外,因為你是他的妻子。我怎能做這種醜事得罪上帝呢?」 10但她還是每天勾引約瑟約瑟不從,並儘量避開她。

11一天,約瑟進屋裡辦事,那時屋裡沒有其他人。 12波提乏的妻子抓住約瑟的外衣,硬要與他上床。約瑟丟下外衣擺脫她逃了出去。 13她見約瑟丟下外衣逃了出去, 14就叫來家裡的人,對他們說:「你們看,我丈夫帶回家的這個希伯來人戲弄我們!他進來要與我上床,我就大聲呼喊, 15他聽見我大聲喊叫,就把衣服丟在我這裡,逃了出去。」 16她把約瑟的外衣留在身邊,等她丈夫回來後, 17就對他說:「你帶回來的那個希伯來人進來要戲弄我, 18我大聲喊叫,他就把衣服丟在我這裡,逃了出去。」

19波提乏聽了妻子講述約瑟如何對待她之後,勃然大怒, 20約瑟關進王囚禁犯人的監牢。 21約瑟坐牢的時候,耶和華與他同在,恩待他,使監獄長賞識他。 22監獄長把獄中所有囚犯及一切事務都交給約瑟管理。 23凡交到約瑟手中的事情,監獄長都很放心,因為耶和華與約瑟同在,使他凡事亨通。