ዘፍጥረት 32 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 32:1-32

ያዕቆብ፣ ወንድሙን ዔሳውን ሊገናኝ ተዘጋጀ

1ያዕቆብም ጕዞውን ቀጠለ፤ የእግዚአብሔርም (ኤሎሂም) መላእክት ተገናኙት፤ 2ባያቸውም ጊዜ፣ “ይህ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦታ ስም መሃናይም32፥2 መሃናይም ማለት ሁለት ጐራ ማለት ነው። አለው።

3ያዕቆብም በኤዶም አገር ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤ 4እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፤ “ጌታዬን ዔሳውን እንዲህ ትሉታላችሁ፤ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል በሉት፤ “ከላባ ዘንድ ተቀምጬ እስከ አሁን ድረስ እዚያው ኖርሁ፤ 5ከብቶች፣ አህዮች፣ የበግና የፍየል መንጎች እንደዚሁም የወንድና የሴት አገልጋዮች አሉኝ፤ አሁንም ይህን መልእክት ለጌታዬ መላኬ በጎ ፈቃድህን እንዳገኝ በማሰብ ነው።” ’ ”

6የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ሊቀበልህ በመምጣት ላይ ነው፤ አራት መቶ ሰዎችም አብረውት አሉ” አሉት። 7ያዕቆብም በታላቅ ፍርሀትና ጭንቀት ተውጦ፣ አብረውት የነበሩትን ሰዎች ሁለት ቦታ32፥7 ወይም ጐራ፤ በ10 ላይ ያለውም እንዲሁ፤ ከፈላቸው፤ በጎቹን፣ ፍየሎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን ሁለት ቦታ ከፈላቸው። 8“ዔሳው መጥቶ በአንደኛው ላይ አደጋ ቢጥል፣ ሌላው ክፍል32፥8 ወይም ጐራ ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ አስቦ ነበር።

9ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ፣ የአባቴ የይስሐቅ አምላክ (ኤሎሂም) ሆይ፤ ‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እኔም በጎ ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ 10እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በስተቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሰራዊት ሆኛለሁ። 11ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁና፤ 12ነገር ግን፣ አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።”

13በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው ዐደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለዔሳው እጅ መንሻ እነዚህን መረጠ፦ 14ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣ 15ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፣ አርባ ላሞችና ዐሥር ኮርማዎች፣ ሃያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባት አህዮች። 16እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዷቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎቹንም፣ “እናንተ ቀድማችሁኝ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዷቸው” አላቸው።

17ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ዔሳው አግኝቶህ፣ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ 18‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተ ኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው።”

19እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎችን የሚነዱትን ሌሎቹንም ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “ዔሳውን ስታገኙት ይህንኑ ትነግሩታላችሁ፤ 20በተለይም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለትን አትዘንጉ።” ይህንም ያዘዘው፣ “ዔሳው ከእኔ ጋር ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል” ብሎ ስላሰበ ነበር። 21ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከእርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።

ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር የገጠመው ትግል

22በዚያች ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ፤ ሁለቱን ሚስቶቹን እንዲሁም ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና ዐሥራ አንድ ልጆቹን ይዞ በያቦቅ መልካ ተሻገረ። 23ወንዙን አሻግሮ ከሸኛቸው በኋላ፣ ጓዙን ሁሉ ሰደደ። 24ያዕቆብ ግን ብቻውን እዚያው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስኪነጋ ድረስ ሲታገለው ዐደረ። 25ያም ሰው ያዕቆብን ታግሎ ማሸነፍ እንዳቃተው በተረዳ ጊዜ፣ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ በግብግቡም የያዕቆብ ጭን ከመጋጠሚያው ላይ ተናጋ። 26በዚያን ጊዜ ሰውየው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው።

ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው።

27ሰውየውም፣ “ስምህ ማን ነው?” አለው።

እርሱም፣ “ያዕቆብ ነው” አለ።

28ሰውየውም፣ “ከእግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ ከሰዎችም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና ከእንግዲህ ስምህ እስራኤል32፥28 እስራኤል ማለት ከእግዚአብሔር ታገለ ማለት ነው። እንጂ፣ ያዕቆብ አይባልም” አለው።

29ያዕቆብም፣ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው።

ሰውየውም፣ “ስሜን ለማወቅ ለምን ፈለግህ?” አለው፤ በዚያም ስፍራ ባረከው።

30ስለዚህ ያዕቆብ፣ “እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ፊት ለፊት አይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል፣ የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል32፥30 ጵኒኤል ማለት የእግዚአብሔር ፊት ማለት ነው። አለው።

31ጵኒኤልንም32፥31 በዕብራይስጥ ጵኑኤል ማለት ሲሆን፣ የጵኒኤል አማራጭ ትርጕም ነው። እንዳለፈ ፀሓይ ወጣችበት፤ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። 32ከዚህም የተነሣ የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ ሹልዳን ከጭኑ ጋር የሚያገናኘውን ሥጋ አይበሉም፤ ምክንያቱም በጭኑ መጋጠሚያ ላይ ያለው የያዕቆብ ሹልዳ ተነክቶ ነበር።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 32:1-32

ยาโคบเตรียมพบเอซาว

1ส่วนยาโคบก็ออกเดินทางต่อไปตามทางของตนด้วย แล้วเหล่าทูตของพระเจ้าก็มาพบเขา 2เมื่อยาโคบเห็นทูตเหล่านั้นจึงกล่าวว่า “นี่คือค่ายของพระเจ้า!” ดังนั้นเขาจึงเรียกสถานที่นั้นว่ามาหะนาอิม32:2 แปลว่าสองค่าย

3ยาโคบส่งคนกลุ่มหนึ่งล่วงหน้าไปหาเอซาวพี่ชายของเขาที่เสอีร์ในดินแดนเอโดม 4เขากำชับคนเหล่านั้นว่า “พวกท่านจงพูดกับเอซาวนายของข้าพเจ้าว่า ‘ยาโคบผู้รับใช้ของท่านกล่าวดังนี้ ข้าพเจ้าได้ไปหาลาบันและอยู่ที่นั่นจนถึงบัดนี้ 5ข้าพเจ้ามีวัว ลา แกะ แพะ และคนรับใช้ชายหญิง บัดนี้ข้าพเจ้าส่งข่าวมายังนายของข้าพเจ้าเพื่อท่านจะกรุณาข้าพเจ้า’ ”

6เมื่อคนเหล่านั้นกลับมาหายาโคบ พวกเขากล่าวว่า “เราได้ไปหาเอซาวพี่ชายของท่าน บัดนี้เขากำลังมาหาท่านพร้อมกับชายสี่ร้อยคน”

7ยาโคบหวาดวิตกยิ่งนัก เขาจึงแบ่งคนที่อยู่กับเขาออกเป็นสองกลุ่ม32:7 หรือค่ายเช่นเดียวกับข้อ 8 รวมทั้งฝูงแพะแกะ ฝูงวัว และอูฐด้วย 8เขาคิดว่า “ถ้าเอซาวเข้ามาโจมตีกลุ่มหนึ่ง กลุ่มที่เหลือจะได้หนีไป”

9แล้วยาโคบอธิษฐานว่า “ข้าแต่พระเจ้าของอับราฮัมและพระเจ้าของอิสอัคบิดาของข้าพระองค์ ข้าแต่พระยาห์เวห์องค์พระผู้เป็นเจ้าผู้ได้ตรัสกับข้าพระองค์ว่า ‘จงกลับไปยังประเทศของเจ้าและญาติพี่น้องของเจ้า และเราจะทำให้เจ้าเจริญรุ่งเรือง’ 10ข้าพระองค์ไม่คู่ควรเลยกับความกรุณาและความซื่อสัตย์ซึ่งทรงสำแดงแก่ผู้รับใช้ของพระองค์ เมื่อข้าพระองค์ข้ามแม่น้ำจอร์แดนนี้ไป ข้าพระองค์มีเพียงไม้เท้าอันเดียวเท่านั้น แต่เดี๋ยวนี้ข้าพระองค์มั่งคั่งจนแบ่งทรัพย์สินผู้คนได้เป็นสองค่าย 11โปรดช่วยข้าพระองค์ด้วย ข้าพระองค์อธิษฐานขอให้ข้าพระองค์รอดพ้นจากเงื้อมมือของเอซาวพี่ชายของข้าพระองค์ เพราะข้าพระองค์กลัวว่าเขาจะมาโจมตีข้าพระองค์และลูกๆ รวมทั้งบรรดาแม่ของเด็กเหล่านั้น 12แต่พระองค์ได้ตรัสว่า ‘เราจะทำให้เจ้าเจริญรุ่งเรืองอย่างแน่นอน และจะทำให้ลูกหลานของเจ้ามากมายเหมือนเม็ดทรายที่ชายทะเลซึ่งไม่อาจนับได้’ ”

13เขาพักแรมที่นั่นและเลือกของกำนัลให้เอซาวพี่ชายของเขาจากสิ่งที่เขามีอยู่คือ 14แพะตัวเมียสองร้อยตัว แพะตัวผู้ยี่สิบตัว แกะตัวเมียสองร้อยตัว แกะตัวผู้ยี่สิบตัว 15แม่อูฐสามสิบตัวกับลูกของมัน วัวตัวเมียสี่สิบตัว วัวตัวผู้สิบตัว ลาตัวเมียยี่สิบตัว ลาตัวผู้สิบตัว 16เขามอบสัตว์เหล่านี้ให้บรรดาคนรับใช้ดูแลโดยแยกแต่ละฝูงออกจากกัน และกล่าวกับคนรับใช้ว่า “จงล่วงหน้าเราไปและรักษาระยะห่างระหว่างฝูงสัตว์ไว้”

17เขาสั่งคนที่นำฝูงสัตว์ไปเป็นกลุ่มแรกสุดว่า “เมื่อเอซาวพี่ชายของเรามาพบเจ้าและถามว่า ‘พวกเจ้าเป็นคนของใคร กำลังจะไปที่ไหน และใครเป็นเจ้าของสัตว์ทั้งหมดที่อยู่ข้างหน้าเจ้า?’ 18ก็ให้เจ้าตอบว่า ‘สัตว์เหล่านี้เป็นของยาโคบผู้รับใช้ของท่าน ส่งมาเป็นของกำนัลแก่เอซาวนายของข้าพเจ้า และยาโคบกำลังตามมาข้างหลัง’ ”

19ยาโคบสั่งคนต้อนฝูงสัตว์คนที่สอง ที่สาม และคนอื่นๆ ทุกกลุ่มว่า “พวกเจ้าต้องพูดอย่างเดียวกันนี้กับเอซาวเมื่อพบเขา 20และพวกเจ้าอย่าลืมพูดว่า ‘ยาโคบผู้รับใช้ของท่านกำลังตามมาข้างหลังเรา’ ” เพราะยาโคบคิดว่า “เราจะทำให้เขาหายโกรธด้วยของกำนัลเหล่านี้ที่ส่งไปล่วงหน้า ภายหลังเมื่อเราพบหน้าเขา บางทีเขาอาจจะยอมรับเรา” 21ดังนั้นยาโคบจึงส่งของกำนัลไปล่วงหน้า ส่วนตัวเขาเองค้างแรมอยู่ในค่าย

ยาโคบปล้ำสู้กับพระเจ้า

22คืนนั้นยาโคบลุกขึ้นพาภรรยาทั้งสอง เมียทาสทั้งสอง และลูกชายสิบเอ็ดคน ข้ามลำน้ำยับบอกตรงบริเวณสันดอน 23หลังจากส่งพวกเขาข้ามลำน้ำไปแล้ว ก็ส่งทรัพย์สมบัติทั้งหมดข้ามตามไป 24ดังนั้นจึงเหลือยาโคบอยู่แต่ลำพัง และมีบุรุษผู้หนึ่งมาปล้ำสู้กับเขาจนรุ่งสาง 25เมื่อบุรุษนั้นเห็นว่าไม่สามารถเอาชนะเขาได้ จึงแตะ32:25 หรือทุบที่เบ้าข้อต่อสะโพกของยาโคบขณะที่ปล้ำสู้กัน ทำให้สะโพกเคล็ด 26แล้วบุรุษนั้นก็พูดว่า “ปล่อยเราไปเถิด ฟ้าสางแล้ว”

แต่ยาโคบตอบว่า “ข้าพเจ้าจะไม่ปล่อยจนกว่าท่านจะอวยพรข้าพเจ้า”

27บุรุษนั้นถามเขาว่า “เจ้าชื่ออะไร?”

เขาตอบว่า “ยาโคบ”

28แล้วบุรุษนั้นจึงกล่าวว่า “เจ้าจะไม่ชื่อว่ายาโคบอีก แต่จะชื่อว่าอิสราเอล32:28 แปลว่าเขาปล้ำสู้กับพระเจ้า เพราะเจ้าสู้กับพระเจ้าและสู้กับมนุษย์แล้วเจ้าก็ชนะ”

29ยาโคบพูดว่า “โปรดบอกชื่อของท่านให้ข้าพเจ้าทราบ”

แต่บุรุษนั้นตอบว่า “เจ้าถามชื่อเราทำไม? เจ้าไม่รู้หรือว่าเราคือใคร?” แล้วอวยพรเขาที่นั่น

30ดังนั้นยาโคบจึงเรียกที่แห่งนั้นว่าเปนีเอล32:30 แปลว่าพระพักตร์พระเจ้า โดยกล่าวว่า “เราได้เห็นพระเจ้าต่อหน้าต่อตา กระนั้นพระองค์ยังทรงไว้ชีวิตเรา”

31ขณะที่ยาโคบเดินทางผ่านเปนีเอล32:31 ภาษาฮีบรูว่าเปนูเอลเป็นอีกรูปหนึ่งของเปนีเอล ดวงอาทิตย์ขึ้นแล้ว เขาเดินโขยกเขยกเพราะยังเจ็บสะโพกอยู่ 32ฉะนั้นชาวอิสราเอลจึงไม่กินเอ็นที่ติดกับเบ้าข้อต่อสะโพกจนกระทั่งทุกวันนี้ เพราะพระเจ้าได้ทรงแตะต้องเบ้าข้อต่อสะโพกบริเวณใกล้เส้นเอ็นของยาโคบ