ዘፍጥረት 28 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 28:1-22

1ይስሐቅ ያዕቆብን አስጠርቶ ከመረቀው28፥1 ወይም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ፣ እንዲህ ሲል አዘዘው፤

“ምንም ቢሆን ከነዓናዊት ሴት አታግባ። 2አሁኑኑ ተነሥተህ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ወደሚኖረው፣ ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጎትህ ከላባ ሴቶች ልጆች መካከል አንዲቷን አግባ። 3ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ28፥3 በዕብራይስጥ ኤልሻዳይ ማለት ነው። ይባርክህ፤ ብዙ ሕዝብ እስክትሆን ድረስ ልጆች አፍራ፤ ዘርህን ያብዛው። 4እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ለአብርሃም ሰጥቶ የነበረውን አንተም በስደት የምትኖርበትን ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ያወርስህ ዘንድ፣ ለአብርሃም የሰጠውን በረከት ለአንተና ለዘርህ ይስጥ።” 5ይስሐቅም ያዕቆብን በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ወደሚኖረው፣ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ወደ ሆነው ወደ ሶርያዊው የባቱኤል ልጅ ወደ ላባ ላከው።

6ዔሳው፣ ይስሐቅ ያዕቆብን መርቆ ሚስት እንዲያገባ ወደ ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ እንደ ላከውና በባረከውም ጊዜ “ከነዓናዊት ሴት አታግባ” ብሎ ትእዛዝ እንደ ሰጠው ሰማ። 7ያዕቆብ የአባት የእናቱን ፈቃድ ለመፈጸም፣ ወደ መስጴጦምያ መሄዱንም ተረዳ። 8በዚህም የከነዓናውያን ሴቶች በአባቱ በይስሐቅ ዘንድ የቱን ያህል የተጠሉ መሆናቸውን ተገነዘበ፤ 9ስለዚህም ወደ እስማኤል ሄደ፣ የአብርሃም ልጅ እስማኤል የወለዳትን፣ የነባዮትን እኅት ማዕሌትን በሚስቶቹ ላይ ተጨማሪ አድርጎ አገባ።

ያዕቆብ በቤቴል ያየው ሕልም

10ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሥቶ ወደ ካራን ሄደ። 11ወደ አንድ ስፍራ እንደ ደረሰም ፀሓይዋ ጠልቃ ስለ ነበር፣ ዐዳሩን በዚያ አደረገ፤ በአቅራቢያው ከነበሩትም ድንጋዮች አንዱን ተንተርሶ ተኛ። 12በሕልሙም፣ ጫፉ ሰማይ የሚደርስ መሰላል በምድር ላይ ቆሞ፣ በላዩም የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ አየ። 13እግዚአብሔርም (ያህዌ) ከጫፉ ላይ28፥13 ወይም በዚህ በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ (ኤሎሂም)፣ የይስሐቅ አምላክ (ኤሎሂም) እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ። 14ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ። 15እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።”

16ያዕቆብም ከእንቅልፉ ሲነቃ፣ “በእውነት እግዚአብሔር (ያህዌ) በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር” አለ። 17እርሱም በፍርሀት፣ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህስ ሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ቤት መሆን አለበት፤ የሰማይ ደጅ ነው” አለ።

18ያዕቆብም በማግስቱም ማልዶ ተነሣ፣ ተንተርሶት ያደረውን ድንጋይ አንሥቶ እንደ ሐውልት አቆመው፤ በዐናቱም ላይ የወይራ ዘይት አፈሰሰበት። 19ያንን ቦታ ቤቴል28፥19 ቤቴል ማለት የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው። ብሎ ሰየመው፤ ቀደም ሲል ግን የከተማዪቱ ስም ሎዛ ነበር።

20ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከእኔ ጋር ቢሆን በምሄድበትም መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላው ምግብ፣ የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ 21ወደ አባቴ ቤትም በደኅና ቢመልሰኝ፣ እግዚአብሔር አምላኬ (ያህዌ ኤሎሂም) ይሆናል፤ 22ይህ ሐውልት አድርጌ ያቆምሁት ድንጋይ፣ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሀብት ሁሉ፣ ከዐሥር እጅ አንዱን ለአንተ እሰጣለሁ።”

New International Reader’s Version

Genesis 28:1-22

1So Isaac called for Jacob and blessed him. Then he commanded him, “Don’t get married to a Canaanite woman. 2Go at once to Paddan Aram. Go to the house of your mother’s father Bethuel. Find a wife for yourself there. Take her from among the daughters of your mother’s brother Laban. 3May the Mighty God bless you. May he give you children. May he make your family larger until you become a community of nations. 4May he give you and your children after you the blessing he gave to Abraham. Then you can take over the land where you now live as an outsider. It’s the land God gave to Abraham.” 5Isaac sent Jacob on his way. Jacob went to Paddan Aram. He went to Laban, the son of Bethuel the Aramean. Laban was Rebekah’s brother. And Rebekah was the mother of Jacob and Esau.

6Esau found out that Isaac had blessed Jacob and had sent him to Paddan Aram. Isaac wanted him to get a wife from there. Esau heard that when Isaac blessed Jacob, he commanded him, “Don’t get married to a woman from Canaan.” 7Esau also learned that Jacob had obeyed his father and mother and had gone to Paddan Aram. 8Then Esau realized how much his father Isaac disliked Canaanite women. 9So he went to Ishmael and married Mahalath. She was the sister of Nebaioth and the daughter of Abraham’s son Ishmael. Esau added her to the wives he already had.

Jacob Has a Dream at Bethel

10Jacob left Beersheba and started out for Harran. 11He reached a certain place and stopped for the night. The sun had already set. He took one of the stones there and placed it under his head. Then he lay down to sleep. 12In a dream he saw a stairway standing on the earth. Its top reached to heaven. The angels of God were going up and coming down on it. 13The Lord stood beside the stairway. He said, “I am the Lord. I am the God of your grandfather Abraham and the God of Isaac. I will give you and your children after you the land you are lying on. 14They will be like the dust of the earth that can’t be counted. They will spread out to the west and to the east. They will spread out to the north and to the south. All nations on earth will be blessed because of you and your children after you. 15I am with you. I will watch over you everywhere you go. And I will bring you back to this land. I will not leave you until I have done what I have promised you.”

16Jacob woke up from his sleep. Then he thought, “The Lord is surely in this place. And I didn’t even know it.” 17Jacob was afraid. He said, “How holy this place is! This must be the house of God. This is the gate of heaven.”

18Early the next morning Jacob took the stone he had placed under his head. He set it up as a sacred stone. And he poured olive oil on top of it. 19He named that place Bethel. But the city used to be called Luz.

20Then Jacob made a promise. He said, “May God be with me. May he watch over me on this journey I’m taking. May he give me food to eat and clothes to wear. 21May he do as he has promised so that I can return safely to my father’s home. Then you, Lord, will be my God. 22This stone I’ve set up as a sacred stone will be God’s house. And I’ll give you a tenth of everything you give me.”