ዘፍጥረት 18 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 18:1-33

ሦስቱ እንግዶች

1ቀትር ላይ አብርሃም በመምሬ ትልልቅ ዛፎች አቅራቢያ በምትገኘው ድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገለጠለት፤ 2ቀና ብሎም ሲመለከት፣ ሦስት ሰዎች ቆመው አየ፤ ወዲያውም ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ፣ ፈጥኖ ወደ ሰዎቹ ሄደ፤ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ።

3አብርሃምም እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ፤18፥3 ወይም ጌታ ሆይ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ ባሪያህን ዐልፈህ አትሂድ፤ 4ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ እዚህም ከዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። 5ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ ከመጣችሁ፣ እህል ቀምሳችሁ ትበረቱ ዘንድ ምግብ ላቅርብላችሁና ጕዟችሁን ትቀጥላላችሁ።”

እነርሱም፣ “መልካም፤ እንዳልኸው አድርግ” አሉት።

6አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወዳለችበት ወደ ድንኳኑ ገብቶ፣ “ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ18፥6 22 ሊትር ገደማ ይሆናል። ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ” አላት።

7ከዚያም ወደ መንጋው በጥድፊያ ሄዶ፣ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ገር የሆነ ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም ጥጃውን ዐርዶ አዘጋጀው። 8አብርሃምም እርጎ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀረበላቸው፤ ሲበሉም ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።

9እነርሱም አብርሃምን፣ “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” ብለው ጠየቁት።

እርሱም፣ “ድንኳን ውስጥ ናት” አላቸው።

10እግዚአብሔርም (ያህዌ)18፥10 ዕብራይስጡ ከዚያም እርሱ ይለዋል። “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ በርግጥ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።

ሣራም በዚህ ጊዜ ከበስተ ጀርባው ካለው ከድንኳኑ ደጃፍ ሆና ትሰማ ነበር። 11በዚያን ጊዜ አብርሃምና ሣራ አርጅተው፣ ዕድሜያቸው ገፍቶ ነበር፤ ሣራም ልጅ የመውለጃዋ ዕድሜ ዐልፎ ነበር። 12ሣራ በልቧ፣ “ካረጀሁና ጌታዬም18፥12 ወይም ባሌ ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛል?” ብላ ሣቀች።

13እግዚአብሔርም (ያህዌ) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሣራ፣ ‘ካረጀሁ በኋላ ልጅ እንዴት አድርጌ እወልዳለሁ’ ስትል ለምን ሣቀች? 14ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት በተባለው ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሣራም ልጅ ይኖራታል።”

15ሣራ ስለ ፈራች፣ “ኧረ አልሣቅሁም” ብላ ዋሸች።

እርሱ ግን፣ “ሣቅሽ እንጂ” አላት።

አብርሃም ስለ ሰዶም ማለደ

16ሰዎቹም ለመሄድ ሲነሡ፣ ቍልቍል ወደ ሰዶም ተመለከቱ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሯቸው ወጣ። 17እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “እኔ የማደርገውን ነገር ከአብርሃም እሰውራለሁን? 18አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ። 19ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቦቹን እንዲያዝዝ መርጬዋለሁ፤ ይኸውም እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሁሉ እንዲፈጸም ነው።”

20ደግሞም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ጩኸት እጅግ በዝቷል፤ ኀጢአታቸውም እጅግ ከፍቷል፤ 21አድራጎታቸው እኔ ዘንድ እንደ ደረሰው ጩኸት መሆኑን ለማየት ወደዚያው እወርዳለሁ፤ እንደዚያ ካልሆነም ዐውቃለሁ።”

22ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ቆመ ነበር።18፥22 ከማሶሬቲኩ ጽሑፍ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን የጥንት ዕብራውያን የጻፉት ትውፊት ግን እግዚአብሔር ግን በአብርሃም ፊት እንደ ቆመ ነበር ይላል። 23አብርሃምም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር አብረህ ታጠፋለህን? 24አምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ቢገኙ፣ በውኑ ነዋሪዎቹን ሁሉ ታጠፋለህን? በውስጧ ለሚገኙ አምሳ ጻድቃን ስትል ከተማዪቱን አትምርምን?18፥24 ወይም ይቅርታ ማድረግ ሊሆን ይችላል፤ ይህም በ26 ላይ ያለውንም ጨምሮ ነው። 25እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ18፥25 ወይም ገዥ በቅን አይፈርድምን?”

26እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “በሰዶም ከተማ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ለእነርሱ ስል አገሪቱን በሞላ እምራለሁ” አለ።

27ደግሞም አብርሃም እንዲህ አለ፤ “እኔ ከንቱ፣ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታ (አዶናይ) ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤ 28ለመሆኑ ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ በአምስቱ ሰዎች ምክንያት መላ ከተማዋን ታጠፋለህን?”

እርሱም፣ “አርባ አምስት ጻድቃን ባገኝ አላጠፋትም” አለ።

29አብርሃምም እንደ ገና፣ “ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?” አለ። እርሱም፣ “ለአርባው ስል እምራታለሁ” አለ።

30ደግሞም አብርሃም፣ “ጌታዬ (አዶናይ) አይቈጣ፤ እባክህ ልናገር፤ ሠላሳ ጻድቃን ብቻ ቢገኙስ?”

እርሱም፣ “ሠላሳ ባገኝ አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።

31አብርሃምም፣ “ከጌታ (አዶናይ) ጋር እናገር ዘንድ መቼም አንዴ ደፍሬአለሁና ምናልባት ሃያ ብቻ ቢገኙስ?” አለ።

እርሱም፣ “ሃያ ቢገኙ፣ ለእነርሱ ስል እምራታለሁ” አለ።

32አብርሃምም፣ “ጌታዬ (አዶናይ) አይቈጣ፤ አንድ ጊዜ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት ዐሥር ብቻ ቢገኙስ?” አለ።

እርሱም “ስለ ዐሥሩ ስል አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።

33እግዚአብሔር (ያህዌ) ከአብርሃም ጋር ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

New International Version – UK

Genesis 18:1-33

The three visitors

1The Lord appeared to Abraham near the great trees of Mamre while he was sitting at the entrance to his tent in the heat of the day. 2Abraham looked up and saw three men standing nearby. When he saw them, he hurried from the entrance of his tent to meet them and bowed low to the ground.

3He said, ‘If I have found favour in your eyes, my lord,18:3 Or eyes, Lord do not pass your servant by. 4Let a little water be brought, and then you may all wash your feet and rest under this tree. 5Let me get you something to eat, so you can be refreshed and then go on your way – now that you have come to your servant.’

‘Very well,’ they answered, ‘do as you say.’

6So Abraham hurried into the tent to Sarah. ‘Quick,’ he said, ‘get three seahs18:6 That is, probably about 16 kilograms of the finest flour and knead it and bake some bread.’

7Then he ran to the herd and selected a choice, tender calf and gave it to a servant, who hurried to prepare it. 8He then brought some curds and milk and the calf that had been prepared, and set these before them. While they ate, he stood near them under a tree.

9‘Where is your wife Sarah?’ they asked him.

‘There, in the tent,’ he said.

10Then one of them said, ‘I will surely return to you about this time next year, and Sarah your wife will have a son.’

Now Sarah was listening at the entrance to the tent, which was behind him. 11Abraham and Sarah were already very old, and Sarah was past the age of childbearing. 12So Sarah laughed to herself as she thought, ‘After I am worn out and my lord is old, will I now have this pleasure?’

13Then the Lord said to Abraham, ‘Why did Sarah laugh and say, “Will I really have a child, now that I am old?” 14Is anything too hard for the Lord? I will return to you at the appointed time next year, and Sarah will have a son.’

15Sarah was afraid, so she lied and said, ‘I did not laugh.’

But he said, ‘Yes, you did laugh.’

Abraham pleads for Sodom

16When the men got up to leave, they looked down towards Sodom, and Abraham walked along with them to see them on their way. 17Then the Lord said, ‘Shall I hide from Abraham what I am about to do? 18Abraham will surely become a great and powerful nation, and all nations on earth will be blessed through him.18:18 Or will use his name in blessings (see 48:20) 19For I have chosen him, so that he will direct his children and his household after him to keep the way of the Lord by doing what is right and just, so that the Lord will bring about for Abraham what he has promised him.’

20Then the Lord said, ‘The outcry against Sodom and Gomorrah is so great and their sin so grievous 21that I will go down and see if what they have done is as bad as the outcry that has reached me. If not, I will know.’

22The men turned away and went towards Sodom, but Abraham remained standing before the Lord.18:22 Masoretic Text; an ancient Hebrew scribal tradition but the Lord remained standing before Abraham 23Then Abraham approached him and said: ‘Will you sweep away the righteous with the wicked? 24What if there are fifty righteous people in the city? Will you really sweep it away and not spare18:24 Or forgive; also in verse 26 the place for the sake of the fifty righteous people in it? 25Far be it from you to do such a thing – to kill the righteous with the wicked, treating the righteous and the wicked alike. Far be it from you! Will not the Judge of all the earth do right?’

26The Lord said, ‘If I find fifty righteous people in the city of Sodom, I will spare the whole place for their sake.’

27Then Abraham spoke up again: ‘Now that I have been so bold as to speak to the Lord, though I am nothing but dust and ashes, 28what if the number of the righteous is five less than fifty? Will you destroy the whole city for lack of five people?’

‘If I find forty-five there,’ he said, ‘I will not destroy it.’

29Once again he spoke to him, ‘What if only forty are found there?’

He said, ‘For the sake of forty, I will not do it.’

30Then he said, ‘May the Lord not be angry, but let me speak. What if only thirty can be found there?’

He answered, ‘I will not do it if I find thirty there.’

31Abraham said, ‘Now that I have been so bold as to speak to the Lord, what if only twenty can be found there?’

He said, ‘For the sake of twenty, I will not destroy it.’

32Then he said, ‘May the Lord not be angry, but let me speak just once more. What if only ten can be found there?’

He answered, ‘For the sake of ten, I will not destroy it.’

33When the Lord had finished speaking with Abraham, he left, and Abraham returned home.