ዘፍጥረት 17 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 17:1-27

የግዝረት ኪዳን

1አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ17፥1 ሁሉን የሚገዛ ማለት ነው። ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤ 2በእኔና በአንተ መካከል የተመሠረተውን ኪዳን አጸናለሁ፤ ዘርህንም እጅግ አበዛለሁ።”

3አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለው፤ 4“እነሆ፤ የምገባልህ ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ። 5ከእንግዲህ ወዲያ ስምህ አብራም17፥5 አብራም ማለት የከበረ አባት ማለት ነው። መባሉ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁና። 6ዘርህን እጅግ አበዛለሁ፤ ብዙ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ። 7በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ (ኤሎሂም) እሆናለሁ። 8ይህችን አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ አምላካቸውም (ኤሎሂም) እሆናለሁ።”

9ከዚያም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “በአንተም በኩል፣ አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን ትጠብቃላችሁ። 10አንተና ከአንተም በኋላ የሚመጣው ዘርህ የምትጠብቁት ኪዳን ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። 11ስለዚህ ሁላችሁም ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ኪዳን ምልክት ይሆናል። 12የሚመጣውም ትውልድ ሁሉ፣ ማንኛውም ወንድ ልጅ፣ ስምንት ቀን ሲሞላው ይገረዝ፤ እንደዚሁም በቤትህ የተወለደውና ከውጭ በገንዘብ የተገዛ ባዕድ ሁሉ ይገረዝ። 13በቤትህ የተወለደም ሆነ በገንዘብህ የተገዛ ሁሉ መገረዝ አለበት፤ በሥጋችሁ የሚፈጸመው ይህ ኪዳኔ የዘላለም ኪዳን ይሆናል። 14የሥጋ ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን በማፍረሱ ከወገኖቹ ይወገድ።”

15እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሦራን ከእንግዲህ ሦራ ብለህ አትጠራትም፤ ስሟ ከዛሬ ጀምሮ ሣራ ይሁን። 16እኔ እባርካታለሁ ከእርሷም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ የብዙም ሕዝቦች እናት ትሆን ዘንድ እባርካታለሁ፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ከእርሷ ይወጣሉ።”

17አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ። 18አብርሃም እግዚአብሔርን (ኤሎሂም)፣ “እስማኤልን ብቻ ባርከህ ባኖርህልኝ” አለው።

19እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለ፤ “ይሁን እሺ፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ17፥19 ይስሐቅ ማለት ይሥቃል ማለት ነው። ብለህ ትጠራዋለህ፤ እኔም ከእርሱ በኋላ ለዘሩ ሁሉ የሚሆን የዘላለም ኪዳን ከእርሱ ጋር እገባለሁ። 20ስለ እስማኤልም ቢሆን ልመናህን ሰምቼሃለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ የዐሥራ ሁለት አለቆች አባት ይሆናል፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ። 21ኪዳኔን ግን የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ልጅ፣ ከይስሐቅ ጋር አደርጋለሁ።” 22እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ላይ ወጣ።

23በዚያችም ዕለት አብርሃም እግዚአብሔር (ያህዌ) ባዘዘው መሠረት ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትንና ከውጭ በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች በሙሉ ገረዛቸው። 24አብርሃም ሲገረዝ ዕድሜው 99 ዓመት ነበር። 25ልጁም እስማኤል ሲገረዝ 13 ዓመቱ ነበር። 26አብርሃምና ልጁ እስማኤል፣ ሁለቱም በዚያኑ ቀን ተገረዙ። 27በአብርሃም ቤት ያሉ ወንዶች ሁሉ፣ በቤቱ የተወለዱትም ሆኑ ከውጭ በገንዘብ የተገዙ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 17:1-27

上帝再次與亞伯蘭立約

1亞伯蘭九十九歲那年,耶和華向他顯現說:「我是全能的上帝。你要遵行我的旨意,做純全無過的人。 2我要與你立約,我要使你子孫極其興旺。」 3亞伯蘭就俯伏在地,上帝又對他說: 4「我要與你立約,你必成為許多民族的始祖。 5以後你的名字不再叫亞伯蘭,要改為亞伯拉罕17·5 亞伯拉罕」意思是「萬族之父」。,因為我要立你為萬族之父。 6我要使你的子孫極其興旺,許多民族和君王必從你而出。 7我要和你並你的子子孫孫立永恆的約,我要做你和你子孫的上帝。 8我要把你現在寄居的整個迦南賜給你和你的後裔永遠作產業,我也必做他們的上帝。」

9上帝又對亞伯拉罕說:「你和你的子孫世世代代都要遵守我的約。 10你們所有的男子都要受割禮,這是我與你和你的子孫所立的約,你們要遵守。 11你們都要割包皮,作為我與你們立約的記號。 12你們世世代代的男子在出生後的第八日都要接受割禮。在你家裡出生的和用錢從外族人那裡買來的奴僕也要受割禮。 13不論是在你家裡生的,還是你用錢買來的男子,都要接受割禮,這樣你們的肉體上就有我永恆之約的記號。 14任何沒有接受割禮的男子,要將他從民中剷除,因為他違背了我的約。」

15上帝對亞伯拉罕說:「你的妻子以後不要叫撒萊,她的名字要叫撒拉16我必賜福給她,讓她為你生一個兒子。她必成為萬族的母親,萬民的君王必從她而出。」 17亞伯拉罕就俯伏在地,笑了起來,心想:「我一百歲了,還能有孩子嗎?撒拉已經九十歲了,還能生養嗎?」 18亞伯拉罕對上帝說:「願以實瑪利蒙你賜福。」 19上帝說:「不,你妻子撒拉必為你生一個兒子,你要給他取名叫以撒,我必向他和他的後代堅守我的約,直到永遠。 20至於以實瑪利,我已聽見你的祈求,我必賜福給他,使他的後代極其興旺昌盛。他必做十二個族長的父親,我必使他成為大國。 21撒拉必在明年這時候給你生以撒,我必向他堅守我的約。」 22上帝說完以後,便離開亞伯拉罕上升而去。

23亞伯拉罕就在那天照著上帝的吩咐,為兒子以實瑪利和家中所有的男子,不論是在家中出生的,還是買回來的,都行了割禮。 24亞伯拉罕接受割禮的時候九十九歲。 25他的兒子以實瑪利接受割禮的時候十三歲。 26他們父子二人就在那天接受了割禮。 27亞伯拉罕家裡所有的男子,包括家中出生的和買回來的,都一起接受了割禮。