ዘፍጥረት 15 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 15:1-21

እግዚአብሔር ለአብራም የገባው ኪዳን

1ከዚህም በኋላ፣ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቃል እንዲህ ሲል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤

“አብራም ሆይ፤ አትፍራ፤

እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤15፥1 ወይም ገዥ

ታላቅ ዋጋህም15፥1 ወይም ዋጋህም እጅግ ታላቅ ይሆናል እኔው ነኝ።”

2አብራምም፣ “እግዚአብሔር (አዶናይ ያህዌ) አምላክ ሆይ፤ ያለ ልጅ የቀረሁ ስለሆንሁ፣ የቤቴ ወራሽ15፥2 በዕብራይስጡ የዚህ ሐረግ ትርጕም አይታወቅም። የደማስቆ ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ ምን ትሰጠኛለህ?” አለው። 3“አንተ ልጆች ስላልሰጠኸኝ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም።”

4በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚከፈል ልጅ ወራሽህ ይሆናል።” 5ወደ ውጭም አውጥቶ፣ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስቲ መቍጠር ከቻልህ፣ ከዋክብቱን ቍጠራቸው፤ ዘርህም እንዲሁ ይበዛል” አለው።

6አብራም እግዚአብሔርን (ያህዌ) አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቈጠረለት።

7ደግሞም እግዚአብሔር፣ “ይህችን ምድር ላወርስህ፣ ከከለዳውያን ምድር፣ ከዑር ያወጣሁህ እግዚአብሔር (ያህዌ) እኔ ነኝ” አለው።

8አብራምም፣ “እግዚአብሔር (አዶናይ ያህዌ) አምላክ ሆይ፤ ይህችን ምድር እንደምወርሳት በምን ዐውቃለሁ?” አለ።

9እግዚአብሔርም (ያህዌ) “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንድ ፍየልና አንድ በግ፣ በተጨማሪም አንድ ዋኖስና አንድ ርግብ አብረህ አቅርብልኝ” አለው።

10አብራምም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቈርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ፣ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጠ፤ ዋኖሷንና ርግቧን ግን ለሁለት አልከፈላቸውም። 11አሞሮችም ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራም ግን አባረራቸው።

12ፀሓይ ልትገባ ስትል አብራም እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማ መጣበት። 13እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ “ዘርህ በባዕድ አገር ስደተኛ እንደሚሆን በርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመትም በባርነት ተረግጦ ይገዛል። 14ነገር ግን በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እፈርድበታለሁ፤ ከዚያም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ። 15አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ወደ መቃብር ትወርዳለህ፤ 16በአራተኛውም ትውልድ ዘርህ ወደዚህ ምድር ይመለሳል፤ የአሞራውያን ኀጢአት ገና ጽዋው አልሞላምና።”

17ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና ታየ፤ በተከፈለውም ሥጋ መካከል ዐለፈ። 18በዚያ ዕለት እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብፅ ወንዝ15፥18 ወይም ደረቅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤ 19የምሰጣቸውም የቄናውያንን፣ የቄኔዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣ 20የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣ 21የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያንን፣ የጌርጌሳውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር ነው።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

创世记 15:1-21

上帝与亚伯兰立约

1这些事以后,耶和华在异象中对亚伯兰说:“亚伯兰,你不用害怕,我是你的盾牌,我要大大赏赐你。” 2亚伯兰说:“主耶和华啊,你要赐我什么呢?我没有儿子,继承我家业的人是大马士革以利以谢。” 3亚伯兰又说:“你没有赐我儿子,我家中的仆人将继承我的产业。” 4耶和华又对他说:“这人不会成为你的继承人,你亲生的儿子才是你的继承人。” 5耶和华把亚伯兰带到外面,对他说:“你抬头看看天空,数数繁星,你能数得尽吗?你的后裔必这么多。” 6亚伯兰信耶和华,耶和华便算他为义人。

7耶和华又对他说:“我是耶和华,我带你离开了迦勒底吾珥,为要把这片土地赐给你。” 8亚伯兰说:“主耶和华啊,我怎么知道我会得到这片土地呢?” 9耶和华说:“你要给我预备三岁的母牛、母山羊和公绵羊各一头,斑鸠和雏鸽各一只。” 10亚伯兰一一照办,把牲畜都劈成两半,一半对着一半地摆列,但没有劈开雀鸟。 11有鸷鸟飞到那些尸体上,亚伯兰赶走了它们。

12太阳下山的时候,亚伯兰睡得很沉,忽然有可怕的黑暗笼罩着他。 13耶和华对他说:“你要清楚知道,你的后裔必流落异乡,被奴役、虐待四百年。 14但我必惩罚奴役他们的国家,之后他们必带着大量的财物离开那里。 15而你必享长寿,安然离世。 16到了第四代15:16 ”希伯来文可能指人一生的年日。,你的子孙必重回此地,因为亚摩利人现在还没有恶贯满盈。”

17太阳下山后,大地黑暗,突然有冒烟的火炉和点着的火炬在肉块中经过。 18就在那天,耶和华跟亚伯兰立约,说:“我必将这片土地赐给你的后代,使他们得到从埃及河到幼发拉底河一带的土地, 19就是基尼人、基尼洗人、甲摩尼人、 20人、比利洗人、利乏音人、 21亚摩利人、迦南人、革迦撒人和耶布斯人的土地。”