ዘፍጥረት 11 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 11:1-32

የባቤል ግንብ

1በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር። 2ሰዎቹም ምሥራቁን11፥2 ወይም ከምሥራቅ፣ በምሥራቅ ይዘው ሲጓዙ፣ በሰናዖር11፥2 ባቢሎንን ያመላክታል። አንድ ሜዳ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ።

3እነርሱም እርስ በርሳቸው፣ “ኑ፤ ጡብ እንሥራ፤ እስኪበቃውም በእሳት እንተኵሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ፣ ለማያያዣም ቅጥራን ተጠቀሙ። 4ከዚያም “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆንና በምድር ላይ እንዳንበተን፣ ኑ፤ ከተማ፣ ሰማይ የሚደርስ ግንብም ለራሳችን እንሥራ” አሉ።

5እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን ሰዎቹ ይሠሩ የነበሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። 6እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “እንዲህ እንደ አንድ ሕዝብ አንድ ቋንቋ በመናገር ይህን ማድረግ ከጀመሩ፣ ከእንግዲህ ያቀዱትን ሁሉ ማከናወን አያዳግታቸውም። 7ኑ እንውረድ፤ እርስ በርሳቸውም እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።”

8ስለዚህ እግዚአብሔር (ያህዌ) በምድር ሁሉ ላይ በታተናቸው፤ ከተማዋንም መሥራት አቆሙ። 9እግዚአብሔር (ያህዌ) በዚያ የመላውን ዓለም ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዪቱ ስም ባቤል11፥9 ባቢሎንን ያመላክታል። ባቤል የሚለው ቃል ድንግርታ የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር አንድ ዐይነት ድምፅ አለው። ተባለ። ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰዎቹን በምድር ሁሉ በተናቸው።

ከሴም እስከ አብራም

11፥10-27 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥21-321ዜና 1፥17-27

10የሴም ትውልድ ይህ ነው፦

ሁለት ዓመት ከጥፋት ውሃ በኋላ ሴም በ100 ዓመቱ አርፋክስድን ወለደ። 11ሴም፣ አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

12አርፋክስድ በ35 ዓመቱ ሳላን ወለደ፤ 13ሳላን ከወለደ በኋላ አርፋክስድ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶችን ወለደ።11፥12-13 ከዕብራይስጡ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣ ሰብዓ ሊቃናት ግን (በተጨማሪ ሉቃ 3፥35-36 እና የዘፍ 10፥24 ማብ ይመ) እንዲሁ ይሉታል፤ 12 በ35 ዓመት ቃይናንን ወለደ፤ 13 ቃይናንን ከወለደ በኋላ፣ አርፋክስድ 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ ቃይናንም 130 ዓመት ከኖረ በኋላ ሳላን ወለደ፤ ሳላንን ከወለደ በኋላ፣ ቃይናን 330 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ ይላል።

14ሳላ በ30 ዓመቱ ዔቦርን ወለደ፤ 15ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

16ዔቦር በ34 ዓመቱ ፋሌቅን ወለደ፤ 17ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

18ፋሌቅ በ30 ዓመቱ ራግውን ወለደ፤ 19ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

20ራግው በ32 ዓመቱ ሴሮሕን ወለደ፤ 21ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

22ሴሮሕ በ30 ዓመቱ ናኮርን ወለደ፤ 23ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

24ናኮር በ29 ዓመቱ ታራን ወለደ፤ 25ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር 119 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

26ታራ 70 ዓመት ከሆነው በኋላ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።

27የታራ ትውልድ ይህ ነው፦

ታራ፣ አብራምን ናኮርንና ሐራንን ወለደ፤

ሐራንም ሎጥን ወለደ። 28ሐራን፣ አባቱ ታራ ገና በሕይወት እንዳለ በከለዳውያን ምድር በምትገኘው በተወለደባት ከተማ በዑር ሞተ። 29አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ፤ የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካም የሐራን ልጅ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነበረ። 30ሦራ መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።

31ታራ ልጁን አብራምን፣ ሐራን የወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን እንዲሁም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ከዑር አብረው ወጡ፤ ነገር ግን ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ።

32ታራ 205 ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 11:1-32

巴別塔

1那時,天下人都用同一種語言,講同一種話。 2人們向東遷移時,在示拿地區找到一處平原,定居下來。 3他們彼此商量說:「來呀,我們燒些磚吧。」他們用磚作石塊,用柏油作水泥來造塔, 4說:「來吧,讓我們造一座城和一座高聳入雲的塔,這樣我們可以揚名天下,不致分散在地上。」 5耶和華從天上下來,要察看人建造的城和塔。 6耶和華說:「看啊,他們同屬一個民族,都用同一種語言,現在就做這樣的事,如果繼續下去,他們會為所欲為。 7讓我們下去變亂他們的語言,使他們彼此言語不通。」 8於是,耶和華把他們從那裡分散到世界各地,他們便不再建造那城了。 9因此,人稱那城為巴別,因為耶和華在那裡變亂了人類的語言,把他們分散到世界各地。

閃的後代

10以下是的後代。

洪水過後兩年,一百歲生亞法撒11之後又活了五百年,生兒育女。

12亞法撒三十五歲生沙拉13之後又活了四百零三年,生兒育女。

14沙拉三十歲生希伯15之後又活了四百零三年,生兒育女。

16希伯三十四歲生法勒17之後又活了四百三十年,生兒育女。

18法勒三十歲生拉吳19之後又活了二百零九年,生兒育女。

20拉吳三十二歲生西鹿21之後又活了二百零七年,生兒育女。

22西鹿三十歲生拿鶴23之後又活了二百年,生兒育女。

24拿鶴二十九歲生他拉25之後又活了一百一十九年,生兒育女。

26他拉七十歲後,生了亞伯蘭拿鶴哈蘭

他拉的後代

27以下是他拉的後代。

他拉亞伯蘭拿鶴哈蘭哈蘭羅得28哈蘭比他父親他拉先去世,他死在自己的家鄉——迦勒底吾珥29亞伯蘭拿鶴都娶了妻子,亞伯蘭的妻子名叫撒萊拿鶴的妻子名叫密迦,是哈蘭的女兒。哈蘭密迦亦迦的父親。 30撒萊不能生育,沒有孩子。

31他拉帶著兒子亞伯蘭、孫子——哈蘭的兒子羅得、兒媳婦——亞伯蘭的妻子撒萊,離開迦勒底吾珥前往迦南,他們來到哈蘭定居下來。 32他拉在那裡去世,享年二百零五歲11·32 二百零五歲」有古卷作「一百四十五歲」。