ዘፍጥረት 10 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 10:1-32

የኖኅ ልጆች ትውልድ

1የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።

የያፌት ዝርያዎች

10፥2-5 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥5-7

2የያፌት ልጆች፦10፥2 ልጆች ማለት ዘርዐ ትውልዶች ወይም ወራሾች ወይም ሕዝቦች ማለት ሊሆን ይችላል፤ በ3፡4፡6፡7፡20-23፡29 እና 31 እንዲሁ፤

ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ ናቸው።

3የጋሜር ልጆች፦

አስከናዝ፣ ራፋት፣ ቴርጋማ ናቸው።

4የያዋን ልጆች፦

ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዲኢ10፥4 ጥቂት የማሶሬቲክ የጥንት ጽሑፎች፣ ከኦሪተ ሳምራውያን፣ ሰብዓ ሊቃናትና አብዛኞቹ የማሶሬቲክ የጥናት ጽሑፎች የሚሉት ዶዳኒም ነው። ናቸው። 5ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።

የካም ዝርያዎች

10፥6-20 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥8-16

6የካም ልጆች፦

ኵሽ፣ ምጽራይም፣10፥6 13ትንም ጨምሮ ግብፅን ያመለክታል። ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።

7የኵሽ ልጆች፦

ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰበቅታ ናቸው።

የራዕማ ልጆች፦

ሳባ፣ ድዳን ናቸው።

8ኵሽ የናምሩድ አባት10፥8 13፡15፡24 እና 26ትን ጨምሮ አባት ማለት ቅድመ አያት ወይም ተተኪ ወይም መሥራች ማለት ሊሆን ይችላል። ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ። 9በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ብርቱ ዐዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ ዐዳኝ” ይባል ነበር። 10የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በ10፥10 ወይም ኦሬክና አርካድ፣ ሁሉም ሰናዖር10፥10 ባቢሎን ነው ምድር ነበሩ። 11ከዚያም ምድር ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን፣ ረሆቦትን፣10፥11 ወይም ነነዌ ከነከተማዋ አደባባዮች ካለህን 12እንዲሁም በነነዌና በካለህ መካከል ሬስን ቈረቈረ፤ ታላቁንም ከተማ መሠረተ።

13ምጽራይም፦

የሉዳማውያን፣ የዕሚማውያን፣ ላህቢያውያን፣ የነፍታሌማውያን፣ 14የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የኮስሉሂማውያን፣ የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።

15ከነዓንም፦

የበኵር ልጁ10፥15 ወይም ከሲዶናውያን የመጀመሪያው የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣ 16የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርሳውያን አባት ነበረ፤ 17እንዲሁም የኤዊያውያን፣ የዑር ኬዋናውያን፣ የሲኒያውያን፣ 18የአራዴዎናውያን፣ የሰማሪናውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነበረ።

ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ 19የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።

20እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።

የሴም ዝርያዎች

10፥21-31 ተጓ ምብ – ዘፍ 11፥10-271ዜና 1፥17-27

21ለያፌት ታላቅ ወንድም10፥21 ወይም ሴም፣ የ…ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።

22የሴም ልጆች፦

ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።

23የአራም ልጆች፦

ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ10፥23 ሰብዓ ሊቃናትንና 1ዜና 1፥17 ይመ፤ በዕብራይስጡ ማሽ ይለዋል። ናቸው።

24አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤10፥24 ከዕብራይስጡ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ሰብዓ ሊቃናት ግን የቃይናን አባት፣ ቃይናንም የ…አባት ነበረ ይላል።

ሳላም ዔቦርን ወለደ።

25ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤

አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፍሌቅ10፥25 ፍሌቅ ማለት ክፍፍል ማለት ነው። ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

26ዮቅጣንም፦

የኤልሞሳድ፣ የሣሌፍ፣ የሐስረሞት፣ የያራሕ፣ 27የሀደራም፣ የአውዛል፣ የደቅላ አባት ነበረ፤ 28እንዲሁም የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣ 29የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባል አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።

30መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል።

31እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው።

32የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 10:1-32

挪亞三個兒子的後代

1洪水以後,挪亞的兒子雅弗都生養了兒女,以下是他們的後代。

2雅弗的兒子是歌篾瑪各瑪代雅完土巴米設提拉3歌篾的兒子是亞實基拿利法陀迦瑪4雅完的兒子是以利沙他施基提多單5雅弗的這些後裔按宗族、語言和民族分散在各海島。

6的兒子是古實麥西10·6 麥西」希伯來文是Mizraim,就是「埃及」,13節亦同。迦南7古實的兒子是西巴哈腓拉撒弗他拉瑪撒弗提迦拉瑪的兒子是示巴底但

8古實也是寧錄之父,寧錄是世上第一位勇士, 9在耶和華眼中是個孔武有力的獵人,因此有俗話說:「要像寧錄那樣在耶和華眼中是個孔武有力的獵人。」 10他首先在示拿地區的巴別以力亞甲甲尼各地建國, 11後來擴展到亞述,在那裡建立了尼尼微利河伯迦拉各城, 12又在尼尼微迦拉之間建立了利鮮大城。

13麥西的後代有路低人、亞拿米人、利哈比人、拿弗土希人、 14帕斯魯細人、迦斯路希人和迦斐托人。非利士人是迦斐托人的後代。

15迦南生長子西頓和次子16他的後代還有耶布斯人、亞摩利人、革迦撒人、 17希未人、亞基人、西尼人、 18亞瓦底人、洗瑪利人和哈馬人。後來迦南各宗族散居在各地。 19迦南的疆域從西頓基拉耳延伸,遠至迦薩,再向所多瑪蛾摩拉押瑪洗扁延伸,遠至拉沙20以上記載的都是的子孫,他們根據自己的宗族、語言、地域和民族散居各處。

21雅弗的哥哥希伯子孫的祖先。 22的兒子是以攔亞述亞法撒路德亞蘭23亞蘭的兒子是烏斯戶勒基帖瑪施24亞法撒沙拉沙拉希伯25希伯有兩個兒子,一個名叫法勒,意思是分開,因為那時人們分地而居。法勒的兄弟叫約坍26約坍亞摩答沙列哈薩瑪非耶拉27哈多蘭烏薩德拉28俄巴路亞比瑪利示巴29阿斐哈腓拉約巴。這些都是約坍的兒子。 30他們居住的地方,從米沙直到東邊的西發山區。 31以上記載的都是的子孫,他們按著自己的宗族、語言、地域和民族散居各處。

32這些人都是洪水以後挪亞三個兒子所生的子孫,他們按著自己的族系散居在各地,後來成為地上不同的民族。