ዘፀአት 26 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 26:1-37

የማደሪያው ድንኳን

26፥1-37 ተጓ ምብ – ዘፀ 36፥8-38

1“በቀጭኑ ከተፈተለ የበፍታ ድርና በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ፤ እጀ ብልኅ ሠራተኛም ኪሩቤልን ይጥለፍባቸው። 2መጋረጃዎች ሁሉ እኵል ይሁኑ፤ የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ ወርዱም አራት ክንድ26፥2 ርዝመቱ 12.5 ሜትር ወርዱ 1.8 ሜትር ያህል ነው። ይሁን። 3አምስቱን መጋረጃዎች አገጣጥመህ ስፋ፤ የቀሩትንም አምስት መጋረጃዎች እንደዚሁ አገጣጥመህ ስፋቸው። 4ከዳር በኩል ባለው መጋረጃ ጠርዝ ላይ፣ ከሰማያዊ ጨርቅ የተሠሩ ቀለበቶች አድርግ፤ በሌላውም የመጋረጃ ጠርዝ ላይ እንዲሁ አድርግ። 5ቀለበቶችን ትይዩ በማድረግ አምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው ጠርዝ መጋረጃ፣ አምሳ ቀለበቶችንም በሌላው ጠርዝ መጋረጃ አድርግ። 6ከዚያም የመገናኛው ድንኳን አንድ ወጥ ይሆን ዘንድ መጋረጃዎቹን በአንድ ላይ ለማያያዝ አምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሥራ።

7“ማደሪያ ድንኳኑን ከላይ ሆነው የሚሸፍኑ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎች ሥራ። 8ዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች እኩል ይሁኑ፤ የእያንዳንዱ ርዝመት ሠላሳ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ26፥8 ርዝመቱ 13.5 ሜትር ወርዱ 1.8 ሜትር ያህል ነው። ይሁን። 9አምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ፣ እንደዚሁም ስድስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርገህ ስፋቸው፤ ከማደሪያው ድንኳን ፊት ለፊት ስድስተኛውን መጋረጃ ዕጠፍና በላዩ ላይ ደርበው። 10በአንድ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለበቶችን፣ እንዲሁም በሌላ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለበቶችን አድርግ። 11ከዚያም አምሳ የናስ ማያያዣዎችን ሥራ፤ ድንኳኑን አንድ ወጥ አድርጎ ለማያያዝ በቀለበቶቹ ውስጥ ጨምራቸው። 12ስለ ድንኳኑ መጋረጃዎች ትርፍ ቁመትም፣ ትርፍ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያው ድንኳን ጀርባ ላይ እንዲንጠለጠል ይሁን። 13የድንኳኑ መጋረጃዎች በሁለቱም ጐኖች አንድ ክንድ ርዝመት26፥13 ርዝመቱ 0.5 ሜትር ያህል ነው። ይኖራቸዋል፤ የተረፈውም የማደሪያውን ድንኳን ጐኖች እንዲሸፍን ሆኖ ይንጠለጠላል፤ 14ለድንኳኑ በቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ ልብስ አብጅ፤ በላዩም ላይ የአቆስጣ ቈዳ ይሁን26፥14 ይህ የባሕር አውሬ ነው።

15“ለማደሪያው ድንኳን ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን አብጅ። 16እያንዳንዱም ወጋግራ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል26፥16 ርዝመቱ 4.5 ሜትር፣ ወርዱ 0.7 ሜትር ያህል ነው። ይሁን፤ 17ሁለት ጕጦችም ጐን ለጐን ይሁኑለት፤ የማደሪያውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚሁ መልክ አብጅ። 18ለማደሪያው ድንኳን ክፍል ሃያ ወጋግራዎችን ሥራ። 19ከሥራቸው የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ፤ በእያንዳንዱ ጕጠት ሥር አንድ መቆሚያ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ። 20በሌላው ጐን፣ ከማደሪያው ድንኳን በስተ ሰሜን በኩል ሃያ ወጋግራዎችን አብጅ፤ 21በእያንዳንዱም ወጋግራ ሥር ሁለት ሁለት መቆሚያ ሆኖ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ። 22በዳር በኩል ለሚገኘው ይኸውም በምዕራብ ጠርዝ ላለው የማደሪያው ድንኳን ስድስት ወጋግራዎች አብጅ። 23ዳርና ዳር ላሉት ማእዘኖች ሁለት ወጋግራዎች አብጅ። 24በእነዚህ ሁለት ማእዘኖች ላይ ከታች እስከ ላይ ድረስ ድርብ ሲሆኑ፣ በአንድ ቀለበት ውስጥ የሚገጥሙ መሆን አለባቸው፤ በሁለቱም ወገን እንዲሁ መሆን አለበት። 25ስለዚህ ስምንት ወጋግራዎች አሉ፤ እንዲሁም ዐሥራ ስድስት የብር መቆሚያዎች ሲኖሩ፣ ለእያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት መቆሚያ ይሆናል።

26“ደግሞም ከግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን አብጅ፤ በአንድ በኩል ላሉት የማደሪያው ድንኳን ወጋግራዎች አምስት፣ 27በሌላው ጐን ላሉት አምስት፣ በማደሪያው ድንኳን ዳር በምዕራብ በኩል ባሉት ወጋግራዎች አምስት አብጅ። 28መካከለኛው አግዳሚ በወጋግራዎቹ መካከል ከጫፍ እስከ ጫፍ ይተላለፍ። 29ወጋግራዎቹን በወርቅ ለብጣቸው፤ አግዳሚዎቹን ለመያዝ የወርቅ ቀለበቶች አብጅ፤ አግዳሚዎቹንም በወርቅ ለብጣቸው።

30“ማደሪያ ድንኳኑንም በተራራው ላይ ባየኸው ዕቅድ መሠረት ትከለው።

31“ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ መጋረጃ አብጅ፤ እጀ ብልኅ ሠራተኛም ኪሩቤልን ይጥለፍበት። 32በወርቅ በተለበጡ ከግራር ዕንጨት በተሠሩና በአራቱ የብር መቆሚያዎች ላይ በቆሙት በአራቱ ምሰሶዎች፣ በወርቅ ኵላቦች ላይ አንጠልጥለው። 33መጋረጃውን በማያያዣዎቹ ላይ ስቀለው፤ የምስክሩንም ታቦት ከመጋረጃው በስተ ኋላ አስቀምጠው፤ መጋረጃውም መቅደሱን ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል። 34በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ የማስተስረያውን ክዳን አስቀምጥ። 35ጠረጴዛውን ከመገናኛው ድንኳን በሰሜን በኩል ከመጋረጃው ውስጥ አስቀምጠው፤ መቅረዙንም ከእርሱ ትይዩ በማድረግ በደቡብ በኩል አድርገው።

36“ለድንኳኑ ደጃፍ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ዐዋቂ የተጠለፈ መጋረጃ አብጅ። 37ለዚህም መጋረጃ የወርቅ ኵላቦችንና ከግራር ዕንጨት የተሠሩ፣ በወርቅ የተለበጡ አምስት ምሰሶዎችን አብጅ፤ አምስት የናስ መቆሚያዎችንም አብጅላቸው።

Thai New Contemporary Bible

อพยพ 26:1-37

พลับพลา

(อพย.36:8-38)

1“จงทำพลับพลาด้วยม่านผ้าลินินเนื้อดีสิบผืน ให้ช่างฝีมือผู้ชำนาญคนหนึ่งปักลวดลายด้วยด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดงเป็นภาพเหล่าเครูบไว้บนม่านเหล่านั้น 2ม่านทุกผืนมีขนาดเดียวกันคือกว้าง 4 ศอก ยาว 28 ศอก26:2 คือ กว้างประมาณ 1.8 เมตร ยาวประมาณ 12.5 เมตร 3ต่อม่านเป็นสองแถบ แถบละห้าผืน 4จงใช้ผ้าสีน้ำเงินทำหูที่ขอบของผ้าม่านทั้งสองแถบ 5แถบละห้าสิบหูตรงกัน 6แล้วทำตะขอทองคำห้าสิบอันเกี่ยวหูของแถบม่านทั้งสองเข้าด้วยกันเพื่อให้เป็นพลับพลาเดียวกัน

7“ให้ทำม่านขนแพะสิบเอ็ดผืนสำหรับทำเป็นเต็นท์เพื่อคลุมพลับพลาไว้ 8ม่านทุกผืนมีขนาดเดียวกัน คือ กว้าง 4 ศอก ยาว 30 ศอก26:8 คือ กว้างประมาณ 1.8 เมตร ยาวประมาณ 13.5 เมตร 9ต่อม่านเป็นสองแถบ แถบหนึ่งใช้ห้าผืน อีกแถบหนึ่งใช้หกผืน ให้พับผืนที่หกทบไว้ด้านหน้าเต็นท์ 10จงทำหูห้าสิบหูติดที่ขอบของแถบผ้าม่านทั้งสองแถบ 11แล้วใช้ตะขอทองสัมฤทธิ์เกี่ยวหูเต็นท์ให้เข้าเป็นเต็นท์เดียวกัน 12ส่วนความยาวที่เหลือ ครึ่งหนึ่งของผ้าเต็นท์ให้ห้อยไว้ทางด้านหลังของพลับพลา 13ผ้าเต็นท์นี้จะมีความยาวยื่นออกมาข้างละ 1 ศอก26:13 คือ ประมาณ 0.5 เมตรเพื่อคลุมพลับพลาไว้ 14จงคลุมเต็นท์ด้วยหนังแกะตัวผู้ย้อมสีแดงและใช้หนังพะยูนคลุมทับไว้อีกชั้นหนึ่ง

15“จงตั้งฝาผนังพลับพลาซึ่งทำจากไม้กระถินเทศ 16ไม้ฝาแต่ละแผ่นกว้าง 1.5 ศอก สูง 10 ศอก26:16 คือ กว้างประมาณ 0.7 เมตร สูงประมาณ 4.5 เมตร 17ไม้ฝาแต่ละแผ่นมีสลักสองชุดขนานกันสำหรับประกบเข้าด้วยกัน จงทำฝาผนังพลับพลาทั้งหมดแบบนี้ 18จงทำไม้ฝายี่สิบแผ่นสำหรับด้านทิศใต้ของพลับพลา 19และทำฐานของไม้ฝาแต่ละแผ่นด้วยเงินแผ่นละสองฐาน รวมสี่สิบฐาน แต่ละฐานรองรับสลักแต่ละอัน 20ทางด้านทิศเหนือของพลับพลาให้ตั้งไม้ฝาขึ้นยี่สิบแผ่น 21และมีฐานเงินรองรับไม้ฝาแผ่นละสองฐาน รวมสี่สิบฐาน 22จงทำไม้ฝาหกแผ่นสำหรับด้านทิศตะวันตกซึ่งเป็นส่วนหลังของพลับพลา 23และทำไม้ฝาอีกสองแผ่นสำหรับมุมทั้งสองข้างของส่วนหลัง 24ไม้ฝาหัวมุมทั้งสองด้านต้องประกบกันสนิทตั้งแต่บนจรดล่าง และด้านบนสุดยึดด้วยห่วงหนึ่งวง ไม้ฝาหัวมุมทั้งสองด้านจะต้องทำอย่างนี้ 25ฉะนั้นที่ส่วนหลังของพลับพลาจะมีไม้ฝาทั้งหมดแปดแผ่น และมีฐานเงินรองรับสิบหกฐาน แผ่นละสองฐาน

26“จงทำคานขวางด้วยไม้กระถินเทศ พาดขวางฝาผนังพลับพลาด้านทิศเหนือห้าเส้น 27ด้านทิศใต้ห้าเส้นและอีกห้าเส้นสำหรับด้านทิศตะวันตกซึ่งเป็นส่วนหลังของพลับพลา 28คานขวางอันกลางพาดผ่านตรงกลางฝาผนังตลอดแนว 29จงหุ้มไม้ฝาทุกแผ่นด้วยทองคำและทำห่วงทองคำยึดคานขวางเหล่านั้นไว้ ไม้คานเหล่านั้นให้หุ้มด้วยทองคำเช่นกัน

30“จงตั้งพลับพลาขึ้นตามแบบที่เราได้แจ้งแก่เจ้าบนภูเขา

31“จงทำม่านด้วยผ้าลินินเนื้อดี ให้ช่างฝีมือผู้ชำนาญปักลวดลายจากด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดงเป็นภาพเหล่าเครูบไว้บนม่านนั้น 32จงแขวนม่านนี้ด้วยตะขอซึ่งทำจากทองคำบนเสาไม้กระถินเทศสี่ต้นหุ้มทองคำ เสาเหล่านี้ตั้งอยู่บนฐานรองรับทำด้วยเงินสี่ฐาน 33หลังม่านซึ่งแขวนบนตะขอทองคำนี้เป็นที่ตั้งหีบพันธสัญญา ม่านนี้จะกั้นระหว่างวิสุทธิสถานและอภิสุทธิสถาน 34แล้วจงตั้งพระที่นั่งกรุณาไว้บนหีบพันธสัญญาในอภิสุทธิสถาน 35โต๊ะและคันประทีปให้วางแยกกันคนละด้านอยู่นอกม่าน คันประทีปจะอยู่ทางด้านทิศใต้ของพลับพลา ส่วนโต๊ะนั้นจะอยู่ทางด้านทิศเหนือ

36“จงทำม่านอีกผืนจากผ้าลินินเนื้อดี ปักอย่างวิจิตรด้วยด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดงสำหรับกั้นทางเข้าเต็นท์ 37จงทำตะขอทองคำสำหรับแขวนม่านผืนนี้บนเสาไม้กระถินเทศห้าต้นหุ้มด้วยทองคำ มีตะขอทองคำและมีฐานรองรับห้าฐานทำด้วยทองสัมฤทธิ์